messages
listlengths
2
2
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nየዲጂታል ኢኮኖሚውን የሚያጠናክር ሬድፎክስ የተሰኘ የመረጃ ቋት ማዕከል ይፋ ሆነ፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ መረጃ አዲሱ ነዳጅ መሆኑን ገልጸው፣ የዲጂታል መሰረተ ልማቱ መጠናከር በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና እና በሌሎች መስኮች ላይ አስተዋጽኦን ያሳርፋል ብለዋል፡፡ ሬድፎክስ ለረጅም ዓመታት በቴሌኮም ዘርፍና በመረጃ ቴክኖሎጂ ልምድ ባካበቱ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች የተቋቋመ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ሚኒስትር ዲኤታው ዳያስፖራዎቸ በዘርፉ ላይ በመሰማራታቸው ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ \n \nጥያቄ: በኢትዮጰጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ያጠናክራል ተብሎ የተቋቋመው የመረጃ ቁዋት ማዕከል ምን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ ሬድፎክስ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nአፄ ይስሐቅ ቀዳማዊ አጼ ይሥሓቅ በዙፋን ስማቸው \"ዳግማዊ ገብረ መስቀል\" ሲባሉ እ.ኤ.አ ከ1414-1429 የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ናቸው። የቀዳማዊ አጼ ዳዊት ሁለተኛ ወንድ ልጅ ሲሆኑ የቀዳማዊ ቴዎድሮስ ታናሽ ወንድም ናቸው። ከአክሱም ነገሥታት በኋላ የመጀመሪያውን ከአውሮጳውያን መሪወች ጋር ግንኙነት ያደረገው ይሄው ንጉስ ነበር። ለምሳሌ ለአራጎን መሪ ለነበርው አልፎንሶ አምስተኛ በ1428 ዓ.ም. በእስላሞች ላይ የተባበረ ሃይልን ለመመስረት ደብዳቤ ልኳል። በዚሁ ደብዳቤ የጋብቻን ነገር ያወሳ ሲሆን ህጻኑ ዶን ፔድሮ ከእጅ ጥበብ አዋቂወች ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የይስሓቅን ሴት ልጅ እንዲያገባ ያትታል። አልፎንሶ ለይስሓቅ የመለሰለት ደብዳቤ ባይገኝም ለይስሓቅ ተከታ ለአጼ ዘርዓ ያዕቆብ በ1450 በደረሰ ደብዳቤ ደህንነታቸው እስከተጥበቀ ድረስ እጅ ጥበበኞችን በደስታ ወደኢትዮጵያ እንደሚልክና ከአሁን በፊት የላካቸው 13 ጥበበኞቹ በመንገድ ላይ እንደጠፉ ሳይጠቅስ አላለፈም። በኒሁ ንጉስ ዘመን በፈላሾች በተነሳ አመጽ ምክንያት ንጉሱ ወደወገራ ዘምተው አመጸኞቹን ኮሶጌ ላይ በማሸነፍ አመጹን አረገቡ። በዚያውም ደብረ ይሥሓቅ የተሰኘውን ቤተክርስቲያን ለድሉ ማስታወሻ ኮሶጌ ላይ አሰሩ። . ንጉሱ ተመልሰው ከአገው ምድር ባሻገር ያለውን የሻንቅላ ምድር ላይ ዘመቻ አካሂደዋል። በደቡብ ምስራቅ ደግሞ ከአረብ አገር የተመለሱትን የሳድ አዲን ፪ኛ ልጆች ወግተዋል። ታሪክ አጥኝው ታደሰ ታምራት ይስሓቅ ከመስሊሞች ጋር ሲዋጋ ወደቀ ይበል እንጂ ዋሊስ በድጅ በርግጥም በወንጀል እንደተገደለና በተድባባ ማርያም እንደተቀበረ ይናገራል። \n \nጥያቄ: አፄ ይስሐቅ የዙፋን ስማቸው ማን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ዳግማዊ ገብረ መስቀል ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nንግድ ንግድ በመሰረቱ እጅግ በጣም ጥንታዊ የሰው ልጆች እንቅስቃሴ ነው። ሰው ማንኛውንም የፈለገውን ቁሳቁስ ማሙዋላት የማይችል ስለሆነ የግድ በተሰማራበት ሙያ የሚያገኘውን የስራ ውጤት ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ነገር ግን እሱ ራሱ ማምረት የማይችላቸውን ነገሮች ለማግኘት ሲል የሚያካሄደው የምርቶች ልውውጥ ሂደት ነው። \n \nጥያቄ: ሰው ራሱ ማምረት የማይችለውን ነገር ለማግኘት የሚያደርገው የምርቶች ልውውጥ ስርዓት ሂደት ምን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ ንግድ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nመጋቢት ፪ ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በልሚ ወቼ ሞሹ የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎ ፩ሺ፭፻ ወታደሮች በመማረክ አሶሳን ያዘ። ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት (በኋላ ፕሬዚዳንት) ሪቻርድ ኒክሰን ኢትዮጵያን ጎበኙ ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበራቸውን የሚወስን የጋራ ጉባዔ ለመመሥረት መወሰናቸውን አስታወቁ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል። ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ሊትዌኒያ እራሷን ከሶቭየት ኅብረት አስተዳደር ውጭ ነጻ መሆኗን አወጀች። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ በልብ ምታት አረፈ። \n \nጥያቄ: ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው መቼ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ፲፱፻፵፯ ዓ/ም ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል። \n \nጥያቄ: የአሁኑ የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ማን ይባላሉ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ዮወሪ ሙሴቪኒ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nአፈወርቅ ተክሌ የዓለም ሊቀ ሊቃውንት፣ የኪነ ጥበብ ምሑር የተከበሩ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በዓለም የታወቁና የተከበሩት ኢትዮጵያዊ ሰዓሊ አፈወርቅ ተክሌ በሰሜን ሸዋ በምትገኘው የሸዋ ነገሥታት ከተማ አንኮበር ላይ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፲፱፻፳፭ ዓ/ም ከአባታቸው አቶ ተክሌ ማሞ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ፈለቀች የማታወርቅ ተወለዱ። ገና በጨቅላ ዕድሜያቸው ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በግፍ ሲወራት፣ የልጅነት ትዝታቸውም ይሄው የግፍ ወረራ እና ጦርነት የሚያስከትለው የሰው፣ የንብረት እና የባህል ጥፋት ፤ ከነጻነትም በኋላ ዐቢዩ ሥራ በወረራ የተበላሸችውን ሀገራቸውን እንደገና መገንባት እንደሆነ ነው። ለዚህም የሀገር ግንባታ አስፈላጊውን እውቀት መሸመት የፈለጉት በ ማዕድን ምሕንድስና ዘርፍ ነበር። ወላጆቻቸውና ዘመድ አዝማዶች ግን የኪነ ጥበብ ስጦታቸውን በቤታቸውና በከተማው ዙሪያ በሚስሏቸው ስዕሎች ተገንዝበውት ነበር። ገና በአሥራ አምስት ዓመታቸው በ፲፱፻፵ ዓ/ም ለከፍተኛ ትምህርት ተመርጠው የምሕንድስና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ እንግሊዝ አገር ይላካሉ። አፈወርቅ ተክሌ በእንግሊዝ አገር የአዳሪ ተማሪ ቤትን ኑሮ ሲያስታውሱ የባዕድ ባህላት፣ የአየር ለውጥ እና የተለመደው የተማሪ ቤት ዝንጠላ እንዳስቸገራቸው ያወሳሉ። ቢሆንም ትምሕርታቸውን በትጋት ሲከታተሉ ቆዩ። በተለይም በሒሣብ፣ በኬሚስትሪ እና በታሪክ ትምሕርቶች ጥሩ ውጤት በማምጣት ሰለጠኑ። ነገር ግን አስተማሪዎቻቸው የተፈጥሮ ስጦታቸው ኪነ ጥበብ እንደሆነ ለመገንዘብ ብዙ ጊዜም አልወሰደባቸውም። በነሱም አበረታችነት በእዚህ ስጦታቸው ላይ የበለጠ ለማተኮር ወስነው በሎንዶን የኪነ ጥበብ ማእከላዊ ትምሕርት ቤት ተመዝግበው ገቡ እዚህ ትምህርት ቤት ጥምሕርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለከፍተኛ ጥናት በስመ ጥሩው የሎንዶን ዩኒቨርሲቲ የስሌድ ኪነ ጥበብ ማዕከል የመጀመሪያው አፍሪቃዊ ተማሪ (ከተከተሏቸው አፍሪቃውያን አንዱ የሱዳን ተወላጁ ኢብራሂም ኤል ሳላሂ ናቸው) በመሆን ገቡ። እዚህ በስዕል፣ ቅርጽ እና በአርክቴክቸር ጥናቶች ላይ አተኩረው ተመረቁ። ትምሕርታቸውን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ፣ በየጥቅላይ ግዛቶቹ እየተዘዋወሩ፣ በየቦታው እስከ ሦስት ወራት በመቀመጥ የኢትዮጵያን ታሪክ እና የብሔረሰቦቿን ባህልና ወግ በሚገባ አጥንተዋል። \n \nጥያቄ: በስሌድ የኪነጥበብ ማዕከል ከአፈወርቅ ተክሌ ጋር የገቡት ሌላኛው አፍሪቃዊ ማን ነበሩ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ኢብራሂም ኤል ሳላሂ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nበ ፰፻ (800) ዓመተ-ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ (400) ዓመተ-ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር። የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ-ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ፮ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ፮ኛው እና በ ፰ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ (1262) ዓ. ም. ጨበጡ ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ። ከዚያም ለብዙ ዘመናት የሰለሞናዊው መንግስት ከጠለ። \n \nጥያቄ: ይኵኖ አምላክ ወደ ስልጣን የወጡት መቼ ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ በ ፲፪፻፷፪ (1262) ዓ. ም. ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nቢል ክሊንተን ያደጉት በሆት ስፕሪንግስ፣ አርካንሳው ነው። የቢል ክሊንተን አባት ዊሊያም ጄፈርሰን ብላይዝ ጁኚየር፣ ቢል ክሊንተን ከመወለዱ ሶስት ወር በፊት በመኪና አደጋ ሞተዋል። የቢል ክሊንተን እናት ቨርጂኒያ ክሊንተን ኬሊ፣ በ1950 እ.ኤ.ኣ. ሮጀር ክሊንተን የሚባል ሰዉ አገባች። 14 ዓመቱ ሲሆን ቢል ክሊንተን የመጨረሻ ስሙን ወደ ክሊንተን ለወጠ። ክሊንተን በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ፥ ዋሽንግተን ዲ.ሲ.፣ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ፥ ኢንግላንድ፣ እና ዬል ዩኒቨርሲቲ፥ ኮነቲኬት ተምረዋል። በ1975 እ.ኤ.ኣ. ሂለሪ ሮድሃምን አገቡና በሊትል ሮክ፥ አርካንሳው መኖር ጀመሩ። ከዚያም በዩኒቨርሲቴ ኦፍ አርካንሳው የሕግ ፐሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል። ቢል ክሊንተን የአርካንሳው አስተዳዳሪ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት በ1978 እ.ኤ.ኣ. ነው። በዛ ጊዜ ከአሜሪካ በዕድሜ ትንሹ አስተዳዳሪ ነበሩ። በ1980 እ.ኤ.ኣ. በፍራንክ ዲ ዋይት ከተሸነፉ በኋላ በ1982 እ.ኤ.ኣ. እንደገና ተመረጡ። ከዛ ጀምሮ እስከ 1992 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ለአራት ጊዜ አስተዳዳሪ ሆነው መርተዋል። በ1984 እ.ኤ.ኣ. የአስተዳዳሪ የስልጣን ዕድሜ ከ2 ዓመት ወደ 4 ዓመት አራዝመዋል። በ1992 እ.ኤ.ኣ. ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድርው አሸንፈዋል። በ1996 እንደገና ተወዳድረው አሸንፈዋል። \n \nጥያቄ: ቢል ክሊንተን የአርካንሳው አስተዳዳሪ ኃላፊነትን ለመጀመሪያ ጊዜ የያዙት መቼ ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ በ1978 እ.ኤ.ኣ. ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ተፈሪ መኰንን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ከአባታቸው ከልዑል ራስ መኰንን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ የሺ እመቤት ኤጀርሳ ጎሮ በተባለ የገጠር ቀበሌ ሐረርጌ ውስጥ ተወለዱ። በ፲፰፻፺፱ የሲዳሞ አውራጃ አገረ ገዥ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. የሐረርጌ አገረ ገዥ ሆኑ። የሐረርጌ አገረ ገዥ ሲሆኑ ፣ በጣም ብዙ ሺህ ተከታዮች ነበሩዋቸውና ልጅ እያሱን ከእንደራሴነት በኅይል እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ተፈሪን ከሐረር አገረ ገዥነት እንዳይሽሯቸው የሚል ስምምነት ተዋዋሉ። ዳሩ ግን እያሱ ሃይማኖታቸውን ከክርስትና ወደ እስልምና እንደቀየሩ የሚል ማስረጃ ቀረበና ብዙ መኳንንትና ቀሳውስት ስለዚህ ኢያሱን አልወደዱዋቸውም ነበር። ከዚህም በላይ እያሱ ተፈሪን ከሐረር ከአገረ ገዥነታቸው ለመሻር በሞከሩበት ወቅት ስምምነታቸው እንግዲህ ተሠርዞ ተፈሪ ደግሞ ለወገናቸው ከስምምነቱ ተለቅቀው በዚያን ጊዜ እሳቸው እያሱን ከእንደራሴነት አስወጡ። እንግዲህ በ፲፱፻፱ ዓ.ም. መኳንንቱ ዘውዲቱን ንግሥተ ነገሥት ሆነው አድርገዋቸው ተፈሪ ደግሞ እንደራሴ ሆኑ። ከዚህ ወቅት ጀምሮ ተፈሪ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለሙሉ ሥልጣን ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም. የንጉሥነት ማዕረግ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ አርፈው ንጉሠ ነገሥት ሆኑና ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ብዙ የውጭ ልዑካን በተገኙበት ታላቅ ሥነ-ሥርዓት ቅብዓ ቅዱስ ተቀብተው እሳቸውና ሚስታቸው እቴጌ መነን ዘውድ ጫኑ። በንግሥ በዓሉ ዋዜማ ጥቅምት ፳፪ ቀን የትልቁ ንጉሠ-ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለዘውድ በዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት ፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ ተመረቀ። ለንግሥ ስርዐቱ ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ አገር ልኡካን ከየአገራቸው ጋዜጠኞች ጋር ከጥቅምት ፰ ቀን ጀምሮ በየተራ ወደ አዲስ አበባ ገብተው ስለነበር ሥርዓቱ በዓለም ዜና ማሰራጫ በየአገሩ ታይቶ ነበር። በተለይም በብሪታንያ ቅኝ ግዛት በጃማይካ አንዳንድ ድሀ ጥቁር ሕዝቦች ስለ ማዕረጋቸው ተረድተው የተመለሰ መሢህ ነው ብለው ይሰብኩ ጀመር። እንደዚህ የሚሉት ሰዎች እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ፊተኛው ስማቸው «ራስ ተፈሪ» ትዝታ ራሳቸውን «ራስታፋራይ» (ራሰተፈሪያውያን) ብለዋል። \n \nጥያቄ: በ፲፱፻፱ ንግስና ለእቴጌ ዘውዲቱ ሲሰጥ እንደራሴ ሆነው የተሾሙት ማን ነበሩ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ ተፈሪ መኰንን ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nሰቆጣ ሰቆጣ ከ1956 ጀምሮ የዋግ አውራጃ ማዕከል እና የሰቆጣ ወረዳ ዋና ከተማ ነው። ከሰቆጣ 6 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የውቅሮ መስቀል ክርስቶስ አለት ውቅር ቤ.ክ. ይገኛል። በዚሁ ቤተ ክርስቲያን ላስታን ከሰቆጣ ሆነው ያስተዳደሩ ዋግሹሞች ደረቅ ቅሪቶች ይገኛሉ። ከአክሱም መዳከም በኋላ በአረብ ጸሐፊዎች ዘንድ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማነት ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰውኩባር የተሰኘው የጥንቱ የኢትዮጵያ ገናና ማዕከል ሰቆጣ እንደነበር በታሪክ ግንዛቤ አለ። ስለሆነም ይመስላል፣ ላስታን በዋግ ሹም ማዕረግ ያስተዳደሩ ገዢዎች መቀመጫቸው ሰቆጣ ነበር። ከጥፋት በተረፉ መዝገቦች ዘንድ ሰቆጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቅሶ የምናገኘው በ1738ዓ.ም. ሲሆን፣ ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ ወደ ላስታ ባደረጉት ዘመቻ ሰቆጣ ውስጥ በዋግ ሹም ነዓኩቶ ለአብ (የዋግ ሹም ቴዎድሮስ አባት) ቤት ለ5ቀን እንዳረፉ ዜና መዋዕላቸው በማተቱ ነው ። ከዚያም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ የአውሮጳ ተጓዦች ሰቆጣን ሲጎበኙ፣ ዋልተር ፕላውዴን ለምሳሌ በኢትዮጵያ ከሚገኙ 5 ብቻ ነጋድራሶች አንዱ በሰቆጣ ይገኝ እንደነበር መዝግቧል። ከዚያም በ1800ዎቹ መጨረሻ ሰቆጣን የጎበኘው ኤ.ቢ.ዋይልድ ሰቆጣን የላስታ ዋና ከተማ አድርጎ ሲጠቅስ፣ የሰቆጣ ቤተ መንግስት ባለ ሶስት ፎቅና በ1650ዎቹ የተገነባ እንደነበር ያትታል። ቤተ መንግስቱን የሰሩት የፋሲል ግቢን አናጺዎ እደሆኑም መላምት ያቀርባል። ይሄው የአውሮጳ ተጓዝ፣ በ1880ዎቹ የሰቆጣ ገበያ ከአካባቢው ካሉት ሁሉ ግዙፉ እንደነበር ፣ የዝሆን ጥርስ እና በቅሎ ገበያው የደራ እንደነበር፣ እንዲሁም 21፣000 በሬዎች፣ 2፣900 ላሞች፣ 10ሺህ ፍየሎች፣ 1፣500 በጎች በየአመቱ ለግብይት ይቀርቡበት እንደነበር ሳይጠቅስ አላለፈም። ጥር 2፣ 1929 ጣሊያኖች በሰቆጣ ላይ የመርዝ ጋዝ ቦምብ እንደጣሉ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል። \n \nጥያቄ: ሰቆጣ የማን መቀመጫ ነበረች?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ላስታን በዋግ ሹም ማዕረግ ያስተዳደሩ ገዢዎች ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nየአሜሪካ ታላቅ ማኅተም የአሜሪካ ብሔራዊ ምልክት የአሜሪካ ታላቅ ማኅተም ይባላል። መጀመርያው የተገለጸው በ1774 ዓ.ም. ነበር። እንዲያውም በይፋ 'አርማ' ሳይሆን 'ማኅተም' ነው። ነገር ግን ይፋዊ አርማ ስለማይኖር በዘልማድ ይህ ማኅተም እንደ አርማ ይጠቀማል። በአሜሪካ ዶላር ላይ (ከ1927 ዓ.ም. ጀምሮ) እንዲሁም በአሜሪካ ፓስፖርት ላይ ይታያል። በማኅተሙ ፊት ላይ ክንፎቹን የሚዘረጋ የመላጣ ንሥር ስዕል እሱም የአሜሪካ ምልክት ይታያል። በግራው ጥፍሩ (ከንሥሩ አንጻር) ውስጥ አሥራ ሦስት ፍላጻ ይዟል። እነርሱም ከእንግሊዝ ያመጹ የመጀመርያ 13 ክፍላገሮች ያመልክታሉ። በቀኙም ጥፍር የወይራ ቅርንጫፍ ይይዛል። ይህ 13 ቅጠልና 13 ፍሬዎች አሉበት። ፍላጻ የጦር ምልክትና ወይራ የሰላም ምልክት በመሆኑ የንሥሩ ራስ ወደሱ ቀኝ ሲዞር ስላምን ይመርጣል እንደ ማለት ነው። በመንቁራው ውስጥ ደግሞ E PLURIBUS UNUM የሚለውን መፈክር ይይዛል። ይህም በሮማይስጥ ማለት 'አንድ ከብዙ' ነው። ከራሱ በላይ 13 ከዋክብት በሰማያዊ በስተኋላ መደብ አለ። እኚህ ከዋክብት የዳዊት ኮከብ ይሠራሉ። በፍርምባው ላይ የሚሸክመው ጋሻ እንደ አሜሪካ ሰንደቅ አለማ ዝንጉርጉር ነው። በማኅተሙ ጀርባ ላይ ያልተጨረሰ ሀረም (ፒራሚድ) ይታያል። ይህ 13 ደረጃዎች ሲኖሩት በመሠረቱ ላይ MDCCLXXVI ይላል። ይህ በሮማይስጥ ቁጥሮች ማለት '፼፯፻፸፮' ወይም 1776 ሲሆን በአውሮጳውያን አቆጣጠር የአሜሪካ ነጻነት አዋጅ የተፈረመበት አመት (1768 ዓ.ም.) ለማመልከት ነው። በሀረሙ ጫፍ ፈንታ 'የእግዚአብሔር ጥበቃ ዓይን' የሚባል ምልክት ይታያል። በዚሁ ዙሪያ «ANNUIT CŒPTIS» የሚለው መፈክር አለ፤ ይህም በሮማይስጥ 'የተጀመረው ተስማምቶታል' ለማለት ነው። በግርጌው ደግሞ «NOVUS ORDO SECLORUM» የሚል መፈክር እያለ ይህ ትርጉም 'የዘመናት አዲስ ሥርዓት' ነው። \n \nጥያቄ: የአሜሪካ ብሔራዊ ምልክት በማኅተሙ ጀርባ ላይ የሚገኘው ምስል ምንድን ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ያልተጨረሰ ሀረም (ፒራሚድ) ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nኢንስታግራም እና ፌስቡክ በአሜሪካ የተገደሉትን የኢራኑ ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒን ሃሳብ የሚደግፉ መረጃዎችን ከገጻቸው እያስወገዱ ነው። የማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ መተግበሪያዎቹ መረጃዎቹን ከገጸቸው የሚያስወገዱት አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ተከትሎ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ መሰረት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ደንበኞች የጀኔራል ሱለይማኒን ሃሳብ ደግፈው በመተግበሪያዎቹ የሚያሰራጯቸውን መረጃዎች እያስወገዱ መሆኑ ተመላክቷል። በተለይም በኢራን የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ጄኔራሉን ደግፈው የሚያሰራጩትን መረጃ ከገጻቸው እያስወገዱ መሆኑንም አስታውቀዋል። ይህን ተከትሎም ኢራናውያን ኢንስታግራም እና ፌስ ቡክ በፈፀሙት ህገ ወጥ ተግባር እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። የኢራን መንግስት ቃል አቀባይ አሊ ሬቤይ በበኩላቸው፥ ድርጊቱን ዴሞክራሲያዊ አሰራርን ያልተከተለ እና ሃላፊነት የጎደለው ሲሉ ኮንነውታል። የኢራኑ ጀኔራል ቃሲም ሱለይማኒ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ትዕዛዝ በኢራቅ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ በሀገራቱ መካከል ውጥረት መንገሱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም አሜሪካ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው ባለቻቸው በተለያዩ ኢራናያውያን ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጥላለች። ኢንስታግራም እና ፌስ ቡክም አሜሪካ ማዕቀብ በጣለችባቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ሲተዳደሩ የነበሩ ገጾችን ከመተግበሪያቸው ማስወገዳቸውን አስታውቀዋል። ምንጭ ፥ ሲ ኤን ኤን \n \nጥያቄ: የኢራኑ ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒን የተገደሉት የት ሀገር እያሉ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ በኢራቅ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nአብርሀም ሊንከን (የካቲት ፮ ቀን ፲፰፻፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፰ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም.) ድረስ የኖሩ ከ፲፰፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ ፲፮ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ከአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ጆን ዊልክስ ቡዝ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ በጥይት ተመትተው ተገደሉ። የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በትጋት ያስተምር ነበር። በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ለኢሊኖይ ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጠንካራ ትጉነት አጥንቶ የሕግ ባለሙያ ሆነ። ከ፲፰፻፳፱ ዓ.ም. ጀምሮ የባርነት ተቃዋሚ ሆነ። ከአፍሪካ የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በግብርና መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛ ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ1834 ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን ሜሪ ቶድን አገቡ። ሜሪ ያለ ባርያዎች ከባልዋ ጋር መኖር ትንሽ የተቸገሩ ቢሆነም ከጊዜ ብዛት ግን ለምደዉ 4 ወንድ ልጆችን በተከተሉት አመታት ወለዱ። በ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. የባርነት ተቃዋሚዎች ወገን ሪፐብሊካን ፓርቲ መሥርተው አብርሀም ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም. የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ዘመቻ፣ እሳቸው የሪፐብሊካን ዕጩ ሆኑ። ምርጫው በተደረገበት ቀን በጥቅምት ፳፰ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.፣ ሊንከን አሸነፉ። በጦርነቱ የስሜን ሠራዊት ከብዛታቸው የተነሣ በአራት ዓመት ውስጥ አሸነፉ። በዚህ ጊዜ ላይ ሊንከን ለአመጸኖቹ ባርዮች ነጻነት አዋጁ። ያላመጹ ዜጎች ባርያዎች ግን በዚያን ጊዜ ነጻ አልወጡም። በ፲፰፻፶፮ዓ.ም.ምርጫ ሊንከን በቀላል ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ተመረጡ። በሚያዝያ ፪ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. የኮንፌደራት ሠራዊት እጁን ሰጠ። ነገር ግን ሚያዝያ ፯ ቀን የመድረክ ትርዒት ሲያዩ በነፍሰ ገዳዩ በጆን ዊልክስ ቡዝ እጅ በጥይት ተመትተው በማግሥቱ ሞቱ። ከዚህም ትንሽ በኋላ ባርነት በሕግ በሙሉ ተክለክሎ የተረፉት ባርያዎች ነጻነት አገኙ። \n \nጥያቄ: አብርሃም ሊንከንን ማን ገደላቸው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ ጆን ዊልክስ ቡዝ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nከተጠመቀ በኋላ ባስሊዮስ በ፫፻፵፱ ዓ ም ወደ ፍልስጤም ፣ ግብፅ ፣ ሶርያ እንዲሁም ሜዞፖታሚያ የመመንኮስንና የገዳማዊነት ትምህርት ለማጥናት ሄደ ። ያለውን ሐብት በሙሉ ለድሆች አድሎ እንደጨረሰ ወደ ምነና በፖንተስ ኒዎሢዛርያ (በዘመኑ አጠራር ኒክሳር ቱርክ) ቤተክርስቲያን ገባ ። ባስልዮስ ይህን የገዳማዊ ኑሮ ቢያከብረውም ለሱ እንዳልተጠራ ተረዳ ። የሴባስቴው እዩስታቴየስ እጅግ የታወቀ መኖክሴ በፖንተስ አካባቢ ባስሊዮስን ያስተምረው ነበር ። በዶግማ ላይ ግን ይለያዩ ነበር ። ይልቁን ባስሊዮስ በመንፈሳዊ ማኅበራዊ ኑሮ ተሳበና በ፫፻፶ በአስተሳሰብ ከእሱ ጋር የሚመሳሰሉትን የክርስትና ደቀመዝሙሮች ወንድሙን ጴጥሮስን ጨምሮ ማሰባሰብ ጀመረ ። አንድላይ ሆነው በቤተሰቡ ርስት ላይ አኔዚ አጠገብ ገዳም መሠረቱ ። በጣም ግልፅ ለማረግ (በዘመኑ አጠራር ሶኑዛ ወይም ኡሉኮይ የዬሲሊርማክ ባሕርና የኬልኪት ባሕር የሚገናኙበት ቦታ ላይ ማለት ነው ።). ባልተቤትዋ እናቱ ኤሚልያ ፣ እህቱ ማክሪናና ሌሎች ሴቶችም ራሳቸውን ለቅዱስ ተግባር መጽዋት በማድረግ ከባስሊዮስ ጋር ተባበሩ ። (ይህን ማኅበረሰብ የመሠረተችው እህቱ ማክሪና ናት የሚሉም አሉ) ። ቅዱስ ባስሊዮስ እዚህ ባታ ላይ ስለ ገዳማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ጽፎ ነበር ። ጽሁፉ ግን ለምሥራቃዊ ክርስትና ዕድገት ከፍተኛ ምክኒያት ሆንዋል. በ፫፻፶ዓ ም ባስሊዮስ ጉዋደኛውን ጎርጎሪ (ግሬጎሪ) የናዚያነስን በአኔዚ እዲቀላቀል ጋበዘው። ጎርጎሪዮም (ግሬጎሪ) እንደመጣ በኦሪጄን ፊሎካሊያ የኦሪጄን ሥራዎች ስብስብ ላይ ጥናት ማድረግ ጀመሩ ። ከዚህም በኋላ ግሬጎሪ ወደ ናዚያነስ ወደ ቤተሰቦቹ ለመመለስ ወሰነ ። ባስሊዮስ የቁንስጥጢናውን የሊቃውንት ጉባዔን ፫፻፶፪ ዓ ም ተሳተፈ ። በመጀመሪ ከኤዩስታቲየስና ከሆሞወሲያንስ ወገነ ፣ ግማሽ አራዊያን የሆነ የመናፍቅ ቡድን ፣ ወልድ ከአብ ጋር ተመሳሳይ እንጂ አንድ ባሕርዪ ወይም አካል አይደለም ብለው ከሚያስተምሩ ጋር ማለት ነው። ሆሞወሲየንስ የአውኖሚየስን አርያኒዝም ይቃወማሉ ግን ደግሞ ከኒቂያ ጉባዔ ተከታዮች ጋር የሥላሴን አንድነት \"ሆሞወሲዮስ\" ከሚያስተምሩት ጋር መተባበር አይፈቅዱም ። በዚህም ቢሆን በዚያ የባስሊዮስ ጳጳስ ዲያኒየስ የቄሣሪያው የሚከተሉት የቀድሞውን ንቂያ ስምምነት ነበረ ። ባስሊዮስም ወዲያውኑ ሆሞወሲያንስን ጥሎ እንዲየውም ጠንካራ የኒቂያ ጉባዔ ውሳኔን ተከታይ ሆነ። \n \nጥያቄ: ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ የምንኩስናን ትምህርት ለመማር ወደ የትኞቹ ሀገራት ሄደዋል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ ወደ ፍልስጤም ፣ ግብፅ ፣ ሶርያ እንዲሁም ሜዞፖታሚያ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nበ ፰፻ (800) ዓመተ-ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ (400) ዓመተ-ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር። የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ-ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ፮ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ፮ኛው እና በ ፰ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ (1262) ዓ. ም. ጨበጡ ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ። ከዚያም ለብዙ ዘመናት የሰለሞናዊው መንግስት ከጠለ። \n \nጥያቄ: በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ደአማት የሚባል መንግስት የተቋቋመው መቼ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ በ ፰፻ (800) ዓመተ-ዓለም ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nራስ መኮንን ልዑል ራስ መኮንን ወልደሚካኤል የሸዋ ንጉሥ የነበሩት የሣህለ ሥላሴ ልጅ የልዕልት ተናኘወርቅ እና የደጃዝማች ወልደሚካኤል ልጅ ናቸው። ግንቦት ፩ ቀን ፲፰፻፵፬ ዓ.ም ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወልደው፤ እስከ ፲፬ ዓመት ዕድሜያቸው ከአባታቸው ጋር ከኖሩ በኋላ ያጐታቸው የንጉሥ ኃይለ መለኮት ልጅ ዳግማዊ ምኒልክ ገና የሸዋ ንጉሥ እንደነበሩ፡ ወደርሳቸው ቤተ መንግሥት መጥተው፡ ባለሟል ሆኑ። በ፲፰፻፷፰ ዓ.ም ዕድሜያቸው ሀያ አራት ዓመት ሲሆን ከወይዘሮ የሺ እመቤት ጋር ተጋብተው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፰፻፹፬ ዓ.ም የወደፊቱን ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ወለዱ። \n \nጥያቄ: ልዑል ራስ መኮንን እናታቸው ማን ይባላሉ?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ልዕልት ተናኘወርቅ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nኩባንያው በ124 ሚሊዮን ብር የሞተር ዘይቶችና ቅባቶች ማምረቻ ለማቋቋም፣ የቡታ ጋዝ ማከፋፈል ሥራ ለመጀመር፣ የሬንጅ አቅርቦት ሥራውን ለማሳደግና የኢንዱስትሪ ኬሚካሎች ለማቅረብ ማቀዱንም ገልጸዋል፡፡ ሊቢያ ኦይል በአውሮፕላን ነዳጅ አቅርቦት ላይ በስፋት እየሠራ እንደሆነ አቶ ዘካሪያስ ተናግረዋል፡፡ በአውሮፕላን ነዳጅ ገበያ የ42 በመቶ የገበያ ድርሻ እንዳለው ጠቁመው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ለ30 ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ አየር መንገዶች የአውሮፕላን ነዳጅ እንደሚያቀርብ ገልጸዋል፡፡ ኩባንያው በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚገኘውን የአውሮፕላን ነዳጅ ዴፖ ማስፋፋቱን፣ አምስት ዘመናዊ የአውሮፕላን ነዳጅ መሙያ ማሽኖች ገዝቶ ጥቅም ላይ ማዋሉን ተናግረዋል፡፡ ሊቢያ ኦይል ለቀለምና ፕላስቲክ ፋብሪካዎች በግብዓትነት የሚያገለግሉ ኬሚካሎች ለማቅረብ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ‹‹ለጊዜው ኬሚካሎቹን ከውጭ በማስገባት የምናከፋፍል ሲሆን፣ በሒደት አገር ውስጥ የማምረት ዕቅድ አለን፤›› ብለዋል አቶ ዘካሪያስ፡፡ \n \nጥያቄ: ሊቢያ ኦይል በምን ያህል ካፒታል የሞተር ዘይትና ቅባት ማምረቻ ለመገንባት አቅዷል?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ በ124 ሚሊዮን ብር ነው።", "role": "assistant" } ]