messages
listlengths
2
2
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nአብዱልራዛቅ እ.ኤ.አ. በ1994 ላይ ያሳተሙት ‹ፓራዳይዝ› የተሰኘው ልብ ወለድ ታንዛኒያ ውስጥ በ20ኛው ምዕት ዓመት የልጅ አስተዳደግ ምን እንደሚመስል ፍንትው አድርገው ያሳዩበት ነው። በዚህ ልብ ወለድም ዓለም አቀፉን የ‹ቡከር› ሽልማት ለማግኘት መቻላቸውን ቢቢሲ ዘግቦታል፡፡ እንደ የኖቤል ኮሚቴ የሥነ ጽሑፍ ክፍል አገላለጽም፣ ‹‹[የእሳቸው] ገጸ ባህርያት ሁሌም ቢሆን በባህልና አኅጉራት መካከል የሚሽከረከሩ፣ በአሁን ሕይወትና በመጪው ሕይወት መካከል የሚመላለሱ ናቸው። በቀላሉ ሊያልፉት የማይችሉት ከባድ እውነታ ውስጥ ናቸው፡፡›› እ.ኤ.አ. በ1948 በዛንዚባር የተወለዱት አብዱልራዛቅ፣ እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ መገባደጃ አገረ እንግሊዝ የገቡት ስደተኛ ሆነው ነው። በቅርቡ ጡረታ እስከወጡበት ዕለት ድረስ በካንተርበሪው የኬንት ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛና የድኅረ ቅኝ ግዛት ሥነ ጽሑፎች ፕሮፌሰር ነበሩ። ሽልማቱ፣ ደራሲው ያለፉበትን የስደተኞች ቀውስንና ቅኝ አገዛዝን በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዲደረግባቸው ያስችላል ብለዋል፡፡ ‹‹እነዚህ በየዕለቱ ከእኛ ዘንድ ያሉ ነገሮች ናቸው። ሰዎች እየሞቱ ነው፣ ሰዎች በዓለም ዙርያ አሁንም እየተጎዱ ነው፡፡ በእነዚህን ጉዳዮች ላይ በፍፁም ቀናነትና አስተውሎት መንገድ መነጋገር መላ መምታት አለብን፤›› ብለዋል የኖቤል ተሸላሚው አብዱልራዛቅ። ዓምና በሥነ ጽሑፍ ያሸነፉት አሜሪካዊው ገጣሚ ሊዊስ ግሉክ መሆናቸው ይታወሳል። የስዊድኑ አካዴሚ በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ከሸለማቸው ታላላቅ ደራስያን መካከል ከአፍሪካ አኅጉር ስድስት ደራስያን ይገኙበታል፡፡ እነርሱም ዎሌ ሾንካ (ናይጀሪያ)፣ ነጂብ ማኅፉዝ (ግብፅ)፣ ናዲን ጎርዲመር (ደቡብ አፍሪካ)፣ ጄ.ኤም ኮትዚ (ደቡብ አፍሪካ)፣ እና ዶሪስ ሌሲንግ (ዚምባቡዌ -እንግሊዝ) ይገኙበታል፡፡ \n \nጥያቄ: ባለፈው ዓመት የኖቤል የሥነ ጽሑፍ ተሸላሚ ማናቸው?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ሊዊስ ግሉክ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nደቡብ አፍሪካ በደቡብ አፍሪቃ ሕገ መንግሥት መሠረት 11 ልሳናት በእኩልነት ይፋዊ ኹኔታ አላቸው። ከነዚህ መካከል ኳዙሉ ከሁሉ ብዙዎች ተናጋሪዎቹ በአገሩ ውስጥ አሉት፤ ቆሣ በቁጥር ብዛት 2ኛው ነው። ከነዚያ በኋላ በተናጋሪዎች ብዛት አፍሪካንስ 3ኛው፣ ስሜን ሶጦ 4ኛው፣ እንግሊዝኛም 5ኛው፣ ጿና 6ኛው፣ ደቡብ ሶጦ 7ኛው፣ ጾንጋ 8ኛው፣ ሷቲ 9ኛው፣ ቬንዳ 10ኛው፣ ንዴቤሌም 11ኛው ነው። ብዙ ሰዎች እስከ 6 ቋንቋዎች ድረስ የመናገር ዕውቀት አላቸው፤ ከነጭም ዜጋዎች አብዛኛው አፍሪካንስና እንግሊዝኛ ሁለቱን ይችላሉ። ትልቁ ከተማ ጆሃንስበርግ ሲሆን ዋና ከተሞቹ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም ኬፕ ታውን፣ ብሉምፎንቴንና ፕሪቶሪያ ናቸው። ይህ ፓርላሜንቱ በኬፕ ታውን፣ ላዕላይ ችሎቱ በብሉምፎንቴን፣ ቤተ መንግሥቱ በፕሪቶሪያ ስለ ሆነ ነው። ስመ ጥሩ የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች ሂው ማሴኬላ እና ሌዲስሚስ ብላክ ማምባዞ ናቸው። የደቡብ አፍሪካ ሙዚቀኞች አሁን የራሳቸውን ዘመናዊ ሙዚቃ ዓይነት «ኳይቶ» አላቸው። የአገሩ አበሳሰል የተለያየ ነው። ብዙ ኗሪዎች የተቀመመ በሬ ቋሊማ ጥብስ (ቡረቮርስ)፣ የበቆሎ አጥሚት (ኡምጝቁሾ)፣ የተቀመመ ዶሮ፣ እና የተቀመመ ወጥ (ካሪ) ይወድዳሉ። የተወደዱ እስፖርቶች እግር ኳስ፣ ክሪኬት እና ራግቢ ናቸው። \n \nጥያቄ: በደቡብ አፍሪካ የአፍሪካንስ ቋንቋ በተናጋሪ ብዛት ስንተኛው ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ 3ኛው ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nኢትዮጵያ በዓለም ዉስጥ ክሚገኙ ጥንታዊ አገሮች ኢትዮጵያ ቀዳሚ በመሆን ከሁሉም የበለጠ ረጅም እድሜ አስቆጥራለች፡፡ በግእዝ/ዓማርኛ እና በመጽሀፍ ቅዱስ ከተመዘገቡት ተጨባጭ መረጃዎች በተጨማሪ አምስት ሚሊዮን አመት የሚሆነውና በጣም ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የሰው ቅሪት የተገኘው በኢትዮጵያ አዋሽ ሸለቆ አካባቢ ሲሆን ይህም፣ 3.2 ሚሊዮን አመት የሆነውን እዛው አካባቢ የተገኘውን የሉሲን (ድንቅነሽን) አጽም በእድሜ ይበልጣል፡፡ ግብጽን ሲገዛ የነበረው ሄሮደስ የሚባለው ንጉስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ታሪክ ፀሀፊ የጥንቷን ኢትዮጵያ በጽሁፎቹ ላይ ይገልፃታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይም ብዙ ግዜ የምትወሳ ስትሖን በተለይም ብሉይ ኪዳን ላይም የንግስት ሳባ (መከዳ) ኢየሩሳሌም መሄድና ለንጉስ ሰለሞን ከባድ የሆኑ ጥያቄዎች ማንሳቷ ተጽፏል፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬ ያላትን መልክ እንድትይዝ ያደረጋት ንጉስ ሚኒሊክ የንግስት ሳባና የንጉስ ሰለሞን ዘር ናቸው፡፡ የንግስት ሳባ ቤተ መንግስት ፍርስራሽ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በአክሱም አካባቢ ይገኛል፡፡ ክርስትናን ኢትዮጵያዉያን ከመቀበላቸዉ በፊት (ኣስቅድመዉ) የኦሪትን ህግ ሰለሚያዉቁ ኣመተ ዓለምን ወደታች እየቆጠሩ የጌታን መወለድ ይጠብቁ ሰለነበረ ክርስትናን ለመቀበል ኣላስቸገራቸዉም፡፡ ነገር ግን በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በእስልምና መስፋፋት ምክንያት ኢትዮጵያ ከአውሮፖውያኑ ክርስትያን ርቃ ቆይታለች፡፡ \n \nጥያቄ: የንግሥት ሳባ ቤተ መንግስት የት ይገኛል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በአክሱም ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nሊቢያ ኦይል ከኢትዮጵያ የተሰናበተውን ሼል ኢትዮጵያ ሊሚትድ በመግዛት የኢትዮጵያን የነዳጅ ገበያ የተቀላቀለው በ2000 ዓ.ም. ነበር፡፡ ኩባንያው ኢትዮጵያ ውስጥ 143 የነዳጅ ማደያዎች ሲኖሩት፣ 24 በመቶ የገበያ ድርሻ አለው፡፡ ኩባንያው በየዓመቱ ዘጠኝ ማደያዎች በመክፈት እ.ኤ.አ. በ2020 የነዳጅ ማደያዎቹን ቁጥር 185 ለማድረስ፣ የገበያ ድርሻውን ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ አቅዷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የኩባንያው ዓመታዊ ሽያጭ 13 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡ ሊቢያ ኦይል 50 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ የአቪዬሽን ነዳጅ ዲፖ ማስፋፊያና በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ በሚገኘው የነዳጅ ዲፖ የኤታኖል ማደባለቂያ ገንብቷል፡፡ ኩባንያው እስከዛሬ እንደ አዲስ የገነባቸው ስምንት የነዳጅ ኩባንያዎችን ብቻ ነው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ለግንባታ የሚሆን ቦታ የማግኘት ችግር በመኖሩ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ዘካሪያስ፣ ከሼል ኩባንያ ግዢ ጋር የተፈጠረው የታክስ ክርክር የኩባንያውን ዕድገት እንደጎተተው ያስረዳሉ፡፡ የታክስ ክርክሩ እልባት ያገኘ በመሆኑ ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማስፋፋት ቆርጦ መነሳቱን አስታውቋል፡፡ ሊቢያ ኦይል ባለፈው ሐሙስ ነሐሴ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ አዳዲስ የሞተር ዘይትና ቅባቶችን አስተዋውቋል፡፡ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ የሊቢያ ኦይል የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፣ የሊቢያ ኦይል ምርቶች አከፋፋዮችና የትራንስፖርት ኩባንያዎች የሊቢያ ኦይል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ሙስባሕ ኤልቤሽቲ ሽልማቶች አበርክተዋል፡፡ \n \nጥያቄ: ሊቢያ ኦይል በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ሆኖ ሥራ የጀመረው ከመቼ ጀምሮ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ በ2000 ዓ.ም. ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት ቀረቡ። በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ኢትዮጵያን በመወከል ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸው ነው የተነገረው። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሂሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋና የቋንቋ ጥናት ክፍል ለረጅም ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል። \n \nጥያቄ: ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም የጠቅላይ ሚንሰትሩ የምን አማካሪ ሆነው ሰርተዋል?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ የማህበራዊ ጉዳዮች ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር ሊኦፖልድ ሴዳር ሴንጎር (1906-2001) የሴኔጋል የመጀመሪያው መራሄ መንግስት በመሆን ከ1960 እስከ 1980 ድረስ ያገለገሉ፣ ኔግሪቲዩድ የሚባለው ፍልስፍና ዋነኛ አቀንቃኝ የነበሩ እና በግጥሞቹም አድናቆትን ያተረፉ አፍሪካዊ የሥነጽሁፍ ሰው ናቸው። ሴንጎር የሴኔጋል ዋና ከተማ ከሆነችው ዳካር 70 ማይልስ ያህል በምትርቅ እና ጆአል ላ ፖርቱጊዝ (ጆአል ፖርቱጊዛዊቱዋ) በምትባል ትንሽ የአሳ አጥማጆች መንደር በ1906 ተወለዱ። አባታችው ነጋዴ ከሆኑ ሴሬር ከሚባሉ ጎሳ የተወለዱ ሲሆን እናታቸው ግን ፔውል ከተባለ የሙስሊም ዘላን አርብቶአደሮች ጎሳ የተወለዱ ሴት ናቸው። ሴንጎር ኋላ ላይ ሲጽፉ «ተወልጄ ያደኩት በአፍሪካ መኸል፣ የጎሳዎች እና ዘሮች መገናኛ ላይ ነው» ብለዋል። በ12 ዓመታችው የካቶሊክ ሚሲዮን ትምህርት ቤት ተመዝግበው ትምህርታቸውን የጀመሩ ሲሆን ከዛ በኋላ በሌሎች ትምህርት ቤቶችም በመማር በ1928 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። ከዚያም ፓሪስ ከሚገኘው ሊሴ ፓሪ ለግራንድ ከተባለው ትምህርት ቤት በ1931 ተመርቀዋል። \n \nጥያቄ: የሴኔጋል ዋና ከተማ ምን ትባላላች?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ ዳካር ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nቻይና በማርስ ላይ የምታካሂደውን የመጀመሪያ ሳይንሳዊ ጥናት የፊታችን ሃምሌ ወር እንደምትጀምር ይፋ አድርጋለች። ጥናቱን የምታከናውነው ሳተላይት ሎንግ ማርች 5-ዋይ 4 በተሰኘ ሮኬት ወደ ህዋ እንደምትላክም የቻይና የጠፈር ምርምር ተቋም አስታውቋል። ሮኬቱ ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቅ የሚያሰችል አቅም እንዳለው በሙከራ ተረጋግጧልም ነው የተባለው። ከሃይድሮጅን እና ኦክስጅን ጋዞች የተሰራ ሞተር ያለው ሮኬት በተያዘው ዓመት በርካታ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ያደርሳል ተብሎ ታምኖበታል። ወደ ህዋ የምትላከው ሳተላይትም በማርስ ፕላኔት ዙሪያ በርካታ አዳዲስ ግኝቶች እና መረጃዎችን ለምርምር ተቋሙ ታደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል። \n \nጥያቄ: ቻይና የምትልከው ሳተላይት ምን በሚባል ሮኬት ወደ ህዋ ይላካል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ ሎንግ ማርች 5-ዋይ 4 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nመስከረም 24 ቀን 2012 የደቡብ ክልልን ሁለንተናዊ መረጃ የያዘ አትላስ እና የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ሥርአት ተመርቀው ለአገልግለት ተዘጋጁ፡፡ በደቡብ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አማካይነት በአዲስ መልክ ተዘጋጅቶ ትናንት የተመረቀው አትላስ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ዲሞግራፊያዊና መልክአ-ምድራዊ መረጃዎችን አካቶ መያዙ ተገልጿል። የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአቱም (የመረጃ ቋቱ) ላለፉት 10 ተከታታይ ዓመታት የነበሩ ሁለንተናዊ መረጃዎችን በድህረ-ገጽ አማካይነት ለማሰራጨት የሚያስችል ነው፡፡ በምርቃ ሥነ-ሥርዐቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሄለን ደበበ የስታቲስቲክስና መልክዐ-ምድር መረጃ ሥርዐት አስተዳደር የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ከያዛቸው የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የደቡብ ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ዲላ ከዚህ በፊት የነበረው የክልሉን አኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ዲሞግራፊያዊና መልክዐ ምድራዊ መረጃዎችን የያዘ አትላስ ላለፉት 15 ዓመታት ማገልግሉንና በአሁኑ ወቅት ያለውን ሁለንተናዊ የክልሉን እድገት ያካተተ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ዛሬ ይፋ የተደረገው አትላስ አስከ 2009 ዓ.ም ያለውን ክልላዊ መረጃ የያዘ እንደሆነ ገልጸው አጠቃላይ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የተመዘገቡትን ውጤቶች፣ የመሰረተልማት ስርጭቶችን፣ ዴሞግራፊያዊ፣ መልክዐ-ምድራዊና ሌሎች መረጃዎችን ማካተቱን ተናግረዋል ፡፡ የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በበኩላቸው ከዚህ በፊት ለዕቅድ መነሻ የሚሆኑ መረጃዎች ታች ካሉ መዋቅሮች ብቻ እንደሚሰበሰቡ ገልፀው ይህም ተአማኒ መረጃ ለማግኘት የሚስቸግር አሰራር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ይፋ የተደረጉት አትላስና የመረጃ ቋት ይህንን የመረጃ ክፍተት የሚሸፍኑና በቀላሉም ተደራሽ የሚሆኑ በመሆናቸው በፍትሀዊነት ላይ የተመሰረቱ ዕቅዶችን ለማዘጋጀት ትልቅ እገዛ ያደርጋሉ ብለዋል ፡፡ በምረቃ ሥነ-ሥርዐቱ ላይ የደቡብ ክልል፣ የዞኖችና የልዩ ወረዳዎች አመራሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ አስተዳደር አካላት ተገኝተዋል፡፡ \n \nጥያቄ: የመረጃ አያያዝ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙ አካላት እነማን ናቸው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ የደቡብ ክልል፣ የዞኖችና የልዩ ወረዳዎች አመራሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nአዶልፍ ሂትለር አዶልፍ ሂትለር (ጀርመንኛ Adolf Hitler አዶልፍ ሂትለ) እ.አ.አ. ከ1933 ጀምሮ የጀርመን ቻንስለር እንዲሁም ከ1934 ጀምሮ ደግሞ የጀርመን መሪም (Führer) ጭምር የነበረ ሰው ነው። ሂትለር በሚያዝያ 13 ቀን 1881 ዓ.ም. (20 አፕሪይል 1889 እ.ኤ.አ.) በዛሬይቷ ኦስትሪያ ተወለደ። በሚያዝያ 22 ቀን 1937 ዓ.ም. (30 አፕሪይል 1945 እ.ኤ.አ.) በርሊን ውስጥ ከአንድ ቀን በፊት ካገባት ሚስቱ ኤቫ ብራውን ጋር የራሱን ህይወት አጠፋ። በ1925 ዓ.ም. መጀመርያ የሂትለር ናዚ ወገን ከጓደኞቹ ወገን ጋር በራይክስታግ ምክር ቤት ትብብር መንግሥት ለመሥራት በቂ መንበሮች አልነበራቸውም። ተቃራኒዎቻቸው የኰሙኒስት ወገን 17% መንበሮች ስለ ነበራቸው የሂትለር ወገኖች የድምጽ ብዛት ሊያገኙ አልተቻላቸውም ነበር። በዚያው ዓመት ግን ከምርጫው ትንሽ በፊት የራይክስታግ ሕንጻ በእሳት ተቃጠለ። ይህ የኰሙኒስቶች ሥራ ነው ብለው የሂትለር ወገን ኰሙኒስት ፓርቲ ቶሎ እንዲከለከል አደረጉ። ስለዚህ ከምርጫው በኋላ የኰሙኒስትን መንበሮች ስለ አጡ የሂትለርም ወገኖች አሁን ከ50% መንበሮች በላይ ስላገኙ፣ የትብብር መንግሥት ሠሩና ወዲያው በድንጋጌ አቶ ሂትለር ባለሙሉ ሥልጣን አደረጉት። ሂትለር የጻፈው የርዮተ አለሙ ጽሑፍ «የኔ ትግል» (Mein Kampf) ሟርት ብቻ ነው። ለመጥቀስ ያህል፦ «ትኩረቴ ወደ አይሁዶች ስለ ተሳበ፣ ቪየናን ከበፊት በሌላ ብርሃን ለማየት ጀመርኩ። በሄድኩበት ሁሉ አይሁዶችን አየሁዋቸው፤ በብዛትም እያየኋቸው፣ ከሌሎች ሰዎች ፈጽሞ እንድለያቸው ጀመርኩ።»... «የግዛቱ (ኦስትሪያ-ሀንጋሪ) ዋና ከተማ የከሠተውን የዘሮች ውሑድ ጠላሁት፤ የዚህን ሁሉ የቼኮች፣ ፖሎች፣ ሀንጋርዮች፣ ሩጤኖች፣ ሰርቦች፣ ክሮዋቶች ወዘተ. የዘሮች ድብልቀት፤ በሁላቸውም መካከል፣ እንደ ሰው ልጅ መከፋፈል ሻገቶ፣ አይሁዶችና ተጨማሪ አይሁዶች።» በነበረው ዘረኛ አስተዳደሩ 6 ሚሊዮን የአውሮፓ አይሁዶችን እና 5 ሚሊዮን ሌሎች የተለያዩ ሀገራት ህዝቦችን (በተለይም ስላቮችን) በገፍ (በሆሎኮስት) አስጨርሷል። በሂትለር ሥር የናዚዎች ፍልስፍና በሂንዱኢዝም እንደሚገኘው በዘር የተከፋፈለ ካስት ሲስተም መመሥረት አይነተኛ ነበር። «አርያኖች» የተባሉት ዘሮች በተለይም የጀርመናውያን ብሔሮች ከሁሉ ላዕላይነት እንዲገኙ አሠቡ። ይህ ዝብረት የተነሣ በርግ ቬዳ ዘንድ በ1500 ዓክልበ. ያህል ወደ ሕንድ የወረሩት ነገዶች «አርያን» ስለ ተባሉ ነው፤ በጥንትም «አሪያና» የአፍጋኒስታን አካባቢ ስም የዘመናዊው ኢራንም ሞክሼ ነበር። በናዚዎቹ እንደ ተዛበው ግን ታሪካዊ ባይሆንም የ«አርያኖች» ትርጓሜ ጀርመናውያን ብቻ ነበሩ፤ ስላቮች (በተለይ የሩስያና የፖሎኝ ሕዝቦች) ግን አርያኖች ሳይሆኑ እንደ ዝቅተኞች ተቆጠሩ። የሂትለር እብደት እየተራመደ በ1926 ዓም የሀንጋሪ ሕዝብ ደግሞ «አርያኖች» ተደረጉ፣ በ1928 ዓም የጃፓን ሕዝብ እንኳን በይፋ «አርያኖች» ተደረጉ፤ በ1934 ዓም የፊንላንድ ሕዝብ ወደ «አርያኖች» በሂትለር ዐዋጅ ተጨመሩ። በሙሶሊኒ ሥር የፋሺስት ጣልያኖች እኛም አርያኖች ነን ቢሉም ጣልያኖች አርያን መሆናቸው በናዚዎች ዘንድ መቸም አልተቀበለም ነበር። \n \nጥያቄ: የአዶልፍ ሂትለር የትውልድ ቦታ የት ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ ኦስትሪያ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nአዲስ አበባ አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ (1879) ዓ.ም. ፍልውሃ ፊን-ፊን ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተ ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 በላይ ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት። ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አምስት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ-ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር። \n \nጥያቄ: አዲስ አበባ ከተማ ከባህር ጠለል በምን ያህል ከፍታ ትገኛለች?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ በ2500 ሜትር ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nዓረብኛ ዓረብኛ የሴማዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ አባል ሆኖ የዕብራይስጥ የአረማያ እንዲሁም የአማርኛ ቅርብ ዘመድ ነው። ፪፻፶ (250) ሚሊዮን የሚያሕሉ ሰዎች እንደ እናት ቋንቋ ይናገሩታል። ከዚህም በላይ በጣም ብዙ ሰዎች እንደ ፪ኛ ቋንቋ ተምረውታል። የሚጻፈው በዓረብኛ ፊደል ነው። በዓረብ አለም ውስጥ አያሌ ቀበሌኞች ይገኛሉ። ቋንቋው በእስልምና ታላቅ ሚና አጫውቷል። እስላሞች አላህ ለሙሐማድ ቁርዓንን ሲገልጽ በዓረብኛ እንደ ሆነ ስለሚያምኑ እንደ ቅዱስ ቋንቋ ይቆጥሩታል። አብዛኛው ዓረብኛ ተናጋሪዎች ሙስሊሞች ናቸው። ዛሬ በምዕራብ ዓለም ደግሞ ብዙ ሰዎች አረብኛ እያጠኑ ነው። በታሪክ ከፍተኛ ሚና በማጫወቱ መጠን ፤ ብዙ የዓረብኛ ቃላት ወደ ሌሎች ቋንቋዎች ገብተዋል። \n \nጥያቄ: ለዓረብኛ ቋንቋ የቅርብ ዘመድ ተብለው ከሚጠቀሱት ቋንቋዎች መካከል መን ይገኛል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ የአማርኛ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nየላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል። ውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ። ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል። ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል። \n \nጥያቄ: ውለታ ለማ (ዶ/ር) ያሸነፉበት አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ የሥራ ፈጠራቸው በህክምናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ ምን ፋይዳ አለው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nኤንመርካር ኤንመርካር በሱመር (ሳንጋር) ነገስታት ዝርዝር ዘንድ የኡሩክ (ኦሬክ) ከተማ መስራች ነበረ። በዚያ ዝርዝር ጽህፈት 420 (ወይም በሌላ ቅጂ 900) ዓመታት እንደ ነገሰ ይላል። ደግሞ አባቱ የኡቱ ልጅ መስኪያጝካሸር ወደ ባሕር ገብቶ ኤንመርካር መንግስቱን ከኤአና ከተማ እንዳመጣ ይጨምራል። የኤንመርካር ስም በሌላ የሱመር ጽሑፍ ደግሞ ተገኝቷል። «ኤንመርካርና የአራታ ንጉስ» በተባለው ተረት እሱ የኡቱ ልጅ ይባላል። (ኡቱ በሱመር እምነት የጸሓይ አምላክ ነበር።) ይህ ተረት የሰው ልጅ ልሳናት መደባለቁን ይናገራል። ኡሩክን ከመመስረቱ በላይ ታላቅ መስጊድ በኤሪዱም እንዳሰራ ይተረታል። ለመሆኑም፣ አራታ እንዲገዛለት የሚለው መልእክት በአፍ መናገር ስለሚከብድ፣ ኤንመርካር ጽሕፈት በሸክላ ጽላት ላይ መጻፍ እንደ ፈጠረ ይላል። በተጨማሪ በዚሁ ጽሑፍ ኤንመርካር የዙሪያው አገሮች ልዩ ልዩ ልሳናት እንደገና አንድ እንዲሆኑ ይጸልያል። እነዚህ አገራት ሹቡር፣ ሐማዚ፣ ሱመር፣ ኡሪ-ኪ (የአካድ ዙርያ) እና የማርቱ አገር ናቸው። ከዚህ በላይ የኤንመርካርን መንግሥት የሚገልጹ ሦስት ተጨማሪ ጽሑፎች አሉ። «ኤንመርካርና ኤንሱሕጊርዓና» የሚባል ተረት የኤንመርካርና የአራታ መቀያየም ሲገልጽ፣ ሐማዚ ተሸንፎ እንደ ነበር ይጠቅሳል። በ«ሉጋልባንዳ በተራራ ዋሻ»፣ ኤንመርካር በአራታ ላይ ዘመቻ ሲመራ ይታያል። አራተኛውና መጨረሻውም ጽላት፣ «ሉጋልባንዳና የአንዙድ ወፍ» ኤንመርካርና ሠራዊቱ በአራታ ዙሪያ ለ1 አመት እንደ ከበቡት ይላል። ለመሆኑ ኤንመርካር 50 አመት ከነገሰ በኋላ፣ የማርቱ ሕዝብ (አሞራውያን) በሱመርና በአካድ ሁሉ ተነሥተው ኡሩክን ለመጠብቅ ግድግዳ በበረሃ መስራት እንደ ነበረበት ይጠቅሳል። በነዚህ መጨረሻ 2 ጽላቶች፣ ከኤንመርካር ጦር አለቆች አንድ የሚሆን ሉጋልባንዳ የሚባል ሰው ይተረታል። በሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ ይህ ሉጋልባንዳ «እረኛው» ኤንመርካርን ወደ ኡሩክ ዙፋን ተከተለው። ይህ ሉጋልባንዳ ደግሞ በጊልጋመሽ ትውፊት በተባለው ግጥም ዘንድ የኋለኛው ኡሩክ ንጉሥ የጊልጋመሽ አባት ነበረ። ዴቪድ ሮኅል የሚባል አንድ የታሪክ ሊቅ የኤንመርካርና የናምሩድ ተመሳሳይነት አመልክቷል። «-ካር» የሚለው ክፍለ-ቃል በሱመር ቋንቋ ማለት «አዳኝ» ነው። ኡሩክ ከተማ የተመሠረተ በኤንመር-ካር ነበር ሲባል፣ ደግሞ ናምሩድ፣ አዳኝ፣ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 10 ዘንድ ኦሬክን ሰራ። በሌላ ትውፊቶች ዘንድ ይህ ናምሩድ የባቢሎን ግንብ መሪ የሆነ ነበር። በተጨማሪም አቶ ሮህል የኤሪዱ መጀመርያ ስም «ባቤል» እንደ ነበር ያምናል፤ እዚያም የሚገኘው የግንብ ፍረስራሽ የባቢሎን ግንብ ፍርስራሽ መሆኑን ገመተ። «ባቢሎን» ማለት የኤሪዱ መጠሪያ እንደ ነበር የሚል ማስረጃ በሌሎችም ጥናቶች አለ። ሮማዊው ጸሐፊ ክላውዲዩስ አይሊያኑስ በጻፈ አንድ ትውፊት ዘንድ (200 ዓ.ም. ግድም)፣ የባቢሎን ንጉስ «ኤወኮሮስ» የተከታዩን «ጊልጋሞስ» አያት ይባላል። ይህ «ጊልጋሞስ» ማለት የኡሩክ ንጉስ ጊልጋመሽ መሆኑን የአሁኑ ሊቃውንት ስለ ገነዘቡ፣ እንዲሁም «ኤወኮሮስ» ማለት ኤንመርካር ሳይሆን አይቀርም የሚል አስተሳሰብ ያቀርባሉ። ከዚህ በላይ የከላውዴዎን ታሪክ ጸሐፊ ቤሮሶስ በጻፈው ዝርዝር መሰረት፣ ከማየ አይህ ቀጥሎ የከላውዴዎንና የአሦር መጀመርያው ንጉስ «ኤወኮዮስ» ይባላል፤ ስለዚህ የዚሁ «ኤወኮዮስ»ና የናምሩድ መታወቂያ አንድ ናቸው የሚለው አሳብ ለረጅም ዘመን የቆየ ነው። \n \nጥያቄ: በሱመር እምነት መሰረት ኡቱ ምንድን ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ የጸሓይ አምላክ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nበ ፰፻ (800) ዓመተ-ዓለም አካባቢ ደአማት የሚባል መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያና ኤርትራ ተቋቋመ። በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘው የሀ የደአማት ዋና ከተማ ነበረች። በየመን የሚኖሩት ሳባውያን በደአማት ላይ ተፅዕኖ እንደነበራቸው የሚታመን ሲሆን ይህ ተፅዕኖ ምን ያህል እንደሆነ ግን በእርግጥ አይታወቅም። ወደ ፬፻ (400) ዓመተ-ዓለም አካባቢ የደአማት መንግስት ከስልጣን ሲወድቅ በትናንሽ መንግስቶች ተተካ። ከነዚህ ትናንሽ መንግስቶች አንዱ አክሱም ሲሆን አካባቢውን እንደገና በአንድነት ለመግዛት ችሎ ነበር። የአክሱማውያን ስፈን በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ጠንካራ መንግሥታዊ ማኅበረሰብ ነበር። በፋርስ ፣ ሮማ እና ቻይና ይገኙ ከነበሩ ታላላቅ መንግሥታት በወደረኛነት የሚቆጠር ትልቅ ኅይል ነበር። በ4ኛው ምእተ-ዓመት አክሱም ወደ ክርስትና ተለወጠ። በ፮ኛው ምእት ዓመት የአክሱማውያን ግዛታዊ ቁጥጥር የዛሬዋን የመን ግዛት ይጨምር ነበር። ግን በ፮ኛው እና በ ፰ኛው አምኣት የአክሱም ሥልጣኔ በእስልምና መነሣት እና መስፋፋት ተዳክሞ ለውድቀት በቃ ። ተከታዩ የዛጔ ሥርወ-መንግሥት ልክ በድንገት እንደተነሳ በድንገት ሲያበቃ ፣ ይኵኖ አምላክ ሥልጣን በ ፲፪፻፷፪ (1262) ዓ. ም. ጨበጡ ፤ እንዲያም ሲል የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥትን መለሱ። ከዚያም ለብዙ ዘመናት የሰለሞናዊው መንግስት ከጠለ። \n \nጥያቄ: የአክሱም መንግስት ወደ ስልጣን የመጣው መቼ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ በ4ኛው ምእተ-ዓመት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nአዲስ አበባ መስከረም 23/2012 የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽህፈት ቤት በኢንስፔክሽን አክሬዲቴሽን አይኤስኦ/አይኢሲ 17020 /2012 ዓለም ዓቀፍ እውቅና ማግኘቱን ገለፀ፡፡ ይህ እውቅና በህክምና ላቦራቶሪ አይ ኤስ ኦ (ISO) 15189፡2012 እና የፍተሻ ላቦራቶሪ አይ ኤስ ኦ/አይ ኢ ሲ 170252017 ካገኘው ዓለም አቀፍ እውቅና በተጨማሪ የተገኘ ነው። በመሆኑም በኢንስፔክሽን አክሬዲቴሽን አይ ኤስ ኦ/አይ ኢ ሲ 17020 /2012 ዓለም ዓቀፍ እውቅና ማግኘቱን ፅህፈት ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመልክቷል። ያገኘውን ዓለም ዓቀፍ እውቅና በማስጠበቅ በሰርቲፍኬሽንና በካሊብሬሽን ዘርፎች የዓለም ዓቀፍ እውቅና ለማግኘት እየሰራ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ በኢንስፔክሽን ዘርፍ ዓለም ዓቀፍ እውቅና ለማግኘት በአፍሪካ አክሬዲቴሽንና በዓለም አቀፍ የላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ትብብር ከግንቦት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በተከታታይ ለአምስት ቀናት ግምገማ ተደርጎበት ነበር፡፡ በግምገማው የተገኙ ክፍተቶችን አስተካክሎ ለገምጋሚ ቡድኑ በማቅረቡ በኢንስፔክሽን አይኤስኦ/አይኢሲ 17020 / 2012 ዘርፉ ዓለም ዓቀፍ እውቅና ማግኘት ችሏል፡፡ ዘርፉ ዓለም ዓቀፍ እውቅና ማግኘቱ በተለይ ሃገሪቱ ወደ ውጭ የምትልካቸው ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎችና ሌሎች ምርቶች የኢንስፔክሽን ሼል እየሰሩ ሰርተፍኬት ለሚሰጡ ተቋማት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም መግለጫው ጠቅሷል፡፡     \n \nጥያቄ: በአዲስ አበባ መስከረም 23/2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤት ምን አይነት እውቅና ነው ያገኘው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ አይኤስኦ/አይኢሲ 17020 /2012 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nበኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ላይ ከባድ የሳይበር ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል። የሳይበር ጥቃቱ በሌላ ሀገር አማካኝነት የተቀነባበረ ሳይሆን እንዳልቀረ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት አስታውቋል። ጥቃቱ የተፈፀመውም አረንጓዴ የተሰኘው የኦስትሪያ ፓርቲ ከወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት ለመመስረት የቀረበው ሃሳብ በደገፈበት ቀን ነው ተብሏል። የሳይበር ጥቃቱ ትናንት ማታ የተጀመረ ሲሆን፥ በቀጣይ ቀናት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች አሳስበዋል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጠው መግለጫ፥ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ ክስተቱን በፍጥነት በመረዳት አስፈላጊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውቋል። ይን እንጂ መስሪያ ቤቱ በተፈጸመው የሳይበር ጥቃት ምን ያህል ጉዳት ስለመድረሱ ያለው ነገር የለም። በሌላ በኩል አሁን ላይ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ከማድረግ ባለፈ ወደ ፊት ሊፈጸም የሚችልን የሳይበር ጥቃት መቶ በመቶ መቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑ ተመላክቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጀምሮ የአውሮፓ ሀገራት በርካታ የሳይበር ጥቃቶችን እያስተናገዱ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። ምንጭ ፦ቢቢሲ   \n \nጥያቄ: በኦስትሪያ በየትኛም የመንግስት መስሪያ ቤት ላይ ነው ከባድ የሳይበር ጥቃት የተፈጸመው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nበ628 ዓክልበ.፣ ድራኮ የሚባል ጸሃፊ የአቴና ከተማ ሕግጋት ጻፈ፤ ይህም ሕግ እጅግ ጨካኝ ሆኖ ይሙት በቃ ለማንኛውም ጥፋት ወሰነ። በ600 ዓክልበ.፣ የአቴና አለቃ ሶሎን አዲስ ሕገ መንግሥት ፈጠረ። የሰራተኞች ሸክም አቀለለ፣ ነገር ግን ባላባትነት በልደት ሳይሆን በንብረት ብዛት እንዲቈጠር አስደረገ። ክሊስቴኔስ እንደገና በ516 ዓክልበ. በዴሞክራሲያዊ መሠረት የተሻሸለ ለአቴና ሕገ መንግሥት አወጣ። የግሪክ ፈላስፋ አሪስጣጣሊስ በ350 ዓክልበ. ግድም የሕገ መንግሥት ሀሣብ ለይቶ ዐወቀ። በጽሑፎቹ የአቴና፣ የስፓርታና የካርታግና ሕገ መንግሥቶች ያነጻጽራል። በመደምደሚያው የተሻለው ሕገ መንግሥት ከንጉሣዊ፣ ከመኳንንታዊና ከሕዝባዊ ወገኖች የተደባለቀ መሆኑን ገመተ። በሀሣቡ በመንግሥት የሚከፋፈሉ ዜጎች ከማይከፋፈሉ ከባርዮችና ዜጎች ካልሆኑ ሰዎች ልዩነት አደረገ። ሮማውያን መጀመርያ «12ቱ ሰንተረዦች» የተባለውን ሕገ መንግሥት ያወጡ በ457 ዓክልበ. ነበር። ከዚያ በኋላ አንዳንዴ የተለያዩ ሕጎችና ትእዛዛት ይጨምሩበት ነበር እንጂ እስከ መጽሐፈ ቴዎዶስዮስ ድረስ (430 ዓ.ም.) ሌላ ክምቹ ሕገ መንግሥት አልኖረም ነበር። በኋላም በምሥራቁ መንግሥት (ቢዛንታይን) በኩል መጽሐፈ ዩስጢኒያኖስ (526 ዓ.ም.) ለአውሮፓ ከፍ ያለ ተጽእኖ ነበረው። ይህም በምስራቁ ነገሥታት 3ኛ ሌዎን ኢሳውራዊ «ኤክሎጋ» (732 ዓ.ም.) እና በ1ኛ ባሲሌዎስ «ባሲሊካ» (870 ዓ.ም.) በተባሉት ሕገ ፍትሐን ተከተለ። \n \nጥያቄ: 12ቱ ሰንተረዦች የተባለ ሕገ መንግስት በ457 ዓክልበ. ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጁት እነማን ነበሩ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ ሮማውያን ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ። \n \nጥያቄ: በዚምባቡዌ የሚገኙ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የምን ስልጣኔ እንደ ነበር ያሳያሉ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ የባንቱ ስልጣኔ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nአልፍሬድ ኢልግ ቢትወደድ አልፍሬድ ኢልግበዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ኑሮውን ኢትዮጵያ ውስጥ የመሠረተ፤ የስዊትዘርላንድ ዜጋ ነበር። ኢልግ በምሕንድስና ሙያው ባቡር እና የቧንቧ ውሐ ለአገራችን ካስተዋወቃቸው ብዙ ዘመናዊ የሥልጣኔ መስመሮች ሁለቱ ሲሆኑ በንጉሠ ነገሥቱ ፊት ታላቅ ታማኝነትን በማፍራቱ የዘውድ አማካሪ እና የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ እስከመምራትም የበቃ ሰው ነበር። ቢትወደድ ኢልግ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ሚና ከተጫወቱ አውሮፓውያን መሃል ባገሪቱ ባሳለፋቸው ሃያ ሰባት ዓመታት እና ባስቀመጣቸው የልማት አሻራዎቹ የታሪክ ሥፍራው በጣም የጎላ ሆኖ እናገኘዋለን። ኢልግ በስዊትዘርላንድ፣ ፍራውንፌልድ በሚባል ከዙሪክ ከተማ በሰሜን-ምሥራቅ አቅጣጫ በሚገኝ ሥፍራ በ መጋቢት ወር ፲፰፻፵፮ ዓ/ም ተወልዶ በስድሳ ሁለት ዓመቱ የገና ዕለት (ታሕሣሥ ፳፱ ቀን) ፲፱፻፰ ዓ/ም ዙሪክ ላይ በልብ ምታት ምክንያት አረፈ። ታዋቂው የታሪክ ምሁር ሪቻርድ ፓንክኸርስት ዳግማዊ ምኒልክ ገና በልጅነታቸው የዓፄ ተዎድሮስ እስረኛ በነበሩ ጊዜ ቴዎድሮስ አጠገባቸው የነበሩትን አውሮፓዊ ወንጌላያን መድፍና መሣሪያዎች እንዲሠሩላቸው ማግባባታቸውን ልብ አድርገው ነበርና የሸዋ ንጉሥ ሲሆኑ በ ኤደን ላይ የነበረ አንድ የስዊትዘርላንድ ዜጋ ነጋዴ ምሕንድስና የሚያውቁ አውሮፓውያን ባለሙያዎችን እንዲፈልግላቸው ጠይቀውት ነበር ይላል። ኢልግ እና ሁለት የአገሩ ሰዎች በ፲፰፻፸ ዓ/ም አካባቢ ጉዞዋቸውን ወደኢትዮጵያ አምርተው ሸዋ ሲገቡ ንጉሥ ምኒልክ መጫሚያ እንዲሠራላቸው ያዙትና ሠርቶ ባበረከተላቸውም መጫሚያ እጅግ እንደተደሰቱ ይነገራል። በሌላ ዘገባ ደግሞ ንጉሡ ኢልግን ጠመንጃ እንዲሠራላቸው አዘዙት። ኢልግ ጠመንጃ ለመሥራት ሙያ እንደሌለውና ከውጭ የሚመጣ መሣሪያ እሱ ከሚሠራው እጅግ የላቀ እንደሚሆን ቢያስረዳም፤ ምኒልክ ኃሳባቸውን የማይለውጡ ሆኑ። እሱም እንደተጠየቀው የሙከራውን ውጤት ሲያሳቸው ንጉሡ ተደስተው ይሄንኑ ጠመንጃ በግምጃ ቤታቸው የክብር ቦታ ሰጡት። ያም ሆነ ይህ ኢልግ በንጉሡ በኩል ዘለቄታ የነበረው የበጎ አስተያየትን እንዳተረፈ ግልጽ ነው። ወዲያው በምሕንድስና ሥራ በደሞዘኝነት ቀጥረውት በየወሩ ሰባት ወይም ስምንት ፓውንድ በጠገራ ብር ይከፍሉት እንደነበር ፓንክኸርስት ዘግቧል። \n \nጥያቄ: አልፍሬድ ኢልግ ለሞት ያበቃው ምን ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ልብ ምታት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nዝናሽ ማሞ በኢትዮጵያ ሬድዮ በእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ከ1979 ጀምሮ በመስራት ትታወቃለች፡፡ በኢትዮጵያ ሬድዮ ለ 16 አመት ያገለገለችው ዝናሽ ከእነ ታደሰ ሙሉነህ ፤ ታምራት አሰፋ ጋር በትጋት የሰራች ሲሆን ከ20 አመት በፊት ከእነ ቤተሰቦችዋ ወደ ምድረ አሜሪካ አቅንታለች፡፡ እምብዛም ልደት መከበር ባልተለመደበት በዚያን ዘመን ከተወለደች ከአንድ አመቷ ጀምሮ እስከ 16 አመቷ ድረስ ቤተሰቦቿ የልደት በዐልዋን እያከበሩላት ያደገችው ዝናሽ ማሞ አብዲበአዲስ አበባ ከተማ ግንቦት 21 ቀን 1954 አ.ም መወለድዋን ለማስታወስ አልተቸገረችም:: ትውልዷም እድገቷም ጠብመንጃ ያዥ ወይም በቅሎ ቤትበሚባለው አካባቢ ነበርእናትና አባቷ ወ/ሮ ሽብሬ ወ/ሃናና አቶ ማሞ አብዲ ይባላሉ:: ዝናሽ ማሞ መጀመሪያ በቄስ ትምህርት ቤት ከፊደል እስከ መልእክተ ዮሀንስ ተምራ ፊደላትን ከለየች በኋላ በበቅሎ ቤት አካባቢ በነበረው አስቀድሞ ኤስ አይ ኤም የልጃገረዶች ክርስቲያን አካዳሚ ተብሎ ይታወቅ በነበረው ጂሲኤ የልጃገረዶች ት/ቤት ከ አንደኛ እስከ ስድስተኛቀጥሎም ይኸው ት/ቤት የፀጋ ክርስቲያን አካዳሚ በመባል ስሙ ተቀይሮ ወንዶችም አብረው መማር በጀመሩበት ት/ቤት ከሰባተኛ እስከ አስረኛበመጨረሻም በጊዜው የነበረው የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ት/ቤቱን ወደ መንግስት ንብረትነት በማዘዋወር የአብዬት ቅርስ ተብሎ ከሰየመው በኋላ አስራ አንደኛና አስራ ሁለተኛ ክፍልን እዚያው ተምራለች:: \n \nጥያቄ: የዝናሽ እናት እና አባት ማን ይባላሉ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ አባቷ ወ/ሮ ሽብሬ ወ/ሃናና አቶ ማሞ አብዲ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nበአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ኢንደስትሪያል ኮምፕሌክስ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ስነስርአት ተካሄደ። የፋብሪካው ግንባታ በ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር የሚከናወን ሲሆን በሀገሪቱ ያለውን የሲሚንቶ እጥረት ሊቀርፍ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ \n \nጥያቄ: የለሚ ናሽናል ፋብሪካ ግንባታ የምን እጥረትን ሊቀርፍ ይችላል?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ የሲሚንቶ እጥረት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nየባሕል ጥናት የባህል ጥናት፣ ሥነ ኅብረተሠብ ወይን ሥነ ማኅበረሰብ ሌላ ስሙ ሶሲዮሎጂ የሰው ልጆች በቡድንና በተናጥል ያላቸውን ባሕል፣ ጠባይና አደረጃጀት የሚያጠና ክፍል ነው። በዚህም ውስጥ አንትሮፖሎጂ ወይም የሰው ልጅ ጥናት (ሥነ ሰብእ) አለ። ሶሲዮሎጂ የሚለው ቃል በፈረንሳያዊው ጸሐፊ ኤማኑወል-ዦሰፍ ሲዬ በ1772 ዓ.ም. ከሮማይስጥ ሶኪውስ (ባልንጀራ፣ ጓደኛ) እና ከግሪክ ሎጎስ (ቃል ወይም ጥናት) በማጋጠም ተፈጠረ። የፈረንሳይ ፈላስፋ ኦጉስት ኮምፕት ከ1830 ዓ.ም. ጀምሮ በሰፊ ጠቀመው። የኅብረተሰብ ጥናት ሲሆን የኅብረተሰብ ጽንሰ ሀሣብ በሮማይስጥ ትርጉም ሶኪየታስ ወይም የባልንጀሮች ግንኙነት ያመልከታል። \n \nጥያቄ: ሶሲዮሎጂ የሚለው ቃል ከሮማስጥ እና ከግሪክ በተውጣጡ ቃላት በማጋጠም የፈጠረው ፈረንሳዊው ሰው ማን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ኤማኑወል-ዦሰፍ ሲዬ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nአፋር (ክልል) አፋር ክልል (ክልል 2) በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዘጠኝ ክልሎች አንዱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ዋና ከተማው ሰመራ ሲሆን የቀድሞዋ ከተማ ግን አሳይታ ነበረች። 96,707 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሸፍን በ1999 እ.ኤ.አ. የሕዝብ ብዛቱ 1,188,000 ነው። የድንቅ ነሽ ወይም ሉሲ አጽም በአፋር ክልል ውስጥ በ, 1967 (Nov. 24, 1974 እ.ኤ.አ.) ነው የተገኘው። በማርች 5, 2005 ደግሞ ሌላ 3.8 ሚሊዮን ዓመት የሚገመት አጽምም በዚሁ ክልል ተገኝቷል። \n \nጥያቄ: አፋር ክልል በ1999 እ.ኤ.አ. በተደረገ ቆጠራ ምን ያህል ሰው ይኖራል?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ 1,188,000 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nማርኮ ፖሎ ማርኮ ፖሎ (1254 - ጥር 8፣ 1324) ጥንታዊው የጣሊያን ተጓዥ እና ነጋዴ ነበር። ታዋቂነትም ያተረፈው በተለይ ወደቻይና እና ሞንጎሊያ ከተጓዙት አውሮጳውያን ቀደምትነት ስለነበረው ነው። በዚህ ምክንያት ከሱ በኋላ ዘግይተው የተነሱት እነ ክርስቶፎር ኮሎምበስ ሳይቀር ለሱ ከፍተኛ ግምት እና አድንቆት እንደነበራቸው ታሪክ ይዘክራል። 17 አመት ሲሞላው ከጣሊያን ቬኒስ ከተማ በመነሳት፣ መጀመሪያ በጀልባ ከዚያም በእግሩና በግመል ተራሮችን በርሃን አቆራርጦ ቤይቺንግ ቻይና (በድሮ ስሟ ካቴ) ለመድረስ ችሏል። በጊዜው ቻይና ትመራ የነበረው በሞንጎሉ መሪ ኩብላ ካህን የሚባለው የጌንጊዝ ካህን ልጅ ነበር። ስርዓቱም የዩዋን ሥርወ መንግስት ይባል ነበር። ለሚቀጥሉት 17 ዓመታት በኩብላ ካህን ቤተመንግስት አስተዳደር ተሰጥቶት መንግስቱን አገልግሏል። ከዚያም ወደ ጣሊያን በውቅያኖሶች አቋርጦ ተመልሷል። ወደ 600 የሚሆኑ አብሮ ተጓዦች ግን በበሽታና በጥቃት ሞተዋል። ይህ ተጓዥ ኑድል የተባለውን የቻይኖች የምግብ አይነት ወደ አገሩ ጣልያን በማምጣት የፓስታ ስራ አሰራርን ለጣሊያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ አስተዋውቋል። በጣሊያኖች እርስ በርስ ጦርነት ተማርኮ እስር ቤት ከገባ በኋላ ለእስር ጓደኛው ርስቲቸሎ የነገረውን ታሪክ ረስቲቸሎ ጽፎ በማሳተም ለማርኮ ፖሎ በአውሮጳ ዙርያ ታላቅ መታወቅን አስገኝቶለታል። \n \nጥያቄ: ማርኮ ፖሎ የእድሜ ዘመኑ ከመቼ እስከ መቼ ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ 1254 - ጥር 8፣ 1324 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nአዲስ አበባ መስከረም 23/2012 ዕውቁና አንጋፋው ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ በውጭ አገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ሳይንቲስቶች ወጣቶችን በሳይንስ በማነጽ ተግባር እንዲሰማሩ፤ መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቀረቡ። ፕሮፌሰር ጥላሁን በቻይና ከሚገኙ የምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የአፍሪካ ሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል ሊያቋቁሙ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የአሜሪካው ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት ዕውቁ ሳይንቲስት ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በሚዘጋጀው ወርኃዊ የሳይንስ ገለጻ መድረክ ወጣቱን ትውልድ ማስተማርና ማነጽ ለኢትዮጵያ ተስፋ፤ የቻይና ተምሳሌትነት በሚል ትናንት ምሽት ገለጻ አድርገዋል። በአውሮጳዊያኑ ዘመን አቆጣጠር 1943 በኢትዮጵያ የተወለዱት ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ጥላሁን ይልማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ የግብርና ቴክኒካል ትምህርት ቤቶች አጠናቀው በቀድሞው የአለማያ እርሻ ኮሌጅ ለሁለት ዓመት ተከታትለዋል። ከዛሬ 55 ዓመታት በፊት በኮሌጅ ቆይታቸው ባሳዩት የላቀ ውጤትም አሜሪካን አገር በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ትምህር ቤት ተልከው ትምህርታቸውን በማጥናት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በቢሾፍቱ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት አስተምረዋል። ከሁለት ዓመታት በኋላም ወደ ካሊፎርኒያ ዳቪስ ዩኒቨርሲቲ በመመለስ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በደቂቀ ሥነ ሕይወት መስክ በማጥናት በአውሮጳዊያኑ አቆጣጠር ከ1980-2006 በተማሩበት ካሊፎርኒያ በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከረዳት እስከ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አስተምረዋል፤ ተመራምረዋል። እ.አ.አ ከ2017 ጀምሮ ደግሞ የዲስቲንጉሽድ ፕሮፌሰር ኤሜሪተስ ማዕረግ ያገኙ ሲሆን እ.አ.አ ከ1990 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ዓለም አቀፍ የሃሩራማ አካባቢ በሽታዎች የሞሌኪዩራል ባዮሎጂ ላብራቶሪ ማዕከል በማቋቋም በዳይሬክተርነት እየመሩ ይገኛሉ። \n \nጥያቄ: ፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ 3ኛ ዲግሪያቸውን የሰሩት በምን ላይ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ በደቂቀ ሥነ ሕይወት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nቢል ክሊንተን ያደጉት በሆት ስፕሪንግስ፣ አርካንሳው ነው። የቢል ክሊንተን አባት ዊሊያም ጄፈርሰን ብላይዝ ጁኚየር፣ ቢል ክሊንተን ከመወለዱ ሶስት ወር በፊት በመኪና አደጋ ሞተዋል። የቢል ክሊንተን እናት ቨርጂኒያ ክሊንተን ኬሊ፣ በ1950 እ.ኤ.ኣ. ሮጀር ክሊንተን የሚባል ሰዉ አገባች። 14 ዓመቱ ሲሆን ቢል ክሊንተን የመጨረሻ ስሙን ወደ ክሊንተን ለወጠ። ክሊንተን በጆርጅታውን ዩኒቨርሲቲ፥ ዋሽንግተን ዲ.ሲ.፣ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ፥ ኢንግላንድ፣ እና ዬል ዩኒቨርሲቲ፥ ኮነቲኬት ተምረዋል። በ1975 እ.ኤ.ኣ. ሂለሪ ሮድሃምን አገቡና በሊትል ሮክ፥ አርካንሳው መኖር ጀመሩ። ከዚያም በዩኒቨርሲቴ ኦፍ አርካንሳው የሕግ ፐሮፌሰር ሆነው አገልግለዋል። ቢል ክሊንተን የአርካንሳው አስተዳዳሪ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረጡት በ1978 እ.ኤ.ኣ. ነው። በዛ ጊዜ ከአሜሪካ በዕድሜ ትንሹ አስተዳዳሪ ነበሩ። በ1980 እ.ኤ.ኣ. በፍራንክ ዲ ዋይት ከተሸነፉ በኋላ በ1982 እ.ኤ.ኣ. እንደገና ተመረጡ። ከዛ ጀምሮ እስከ 1992 እ.ኤ.ኣ. ድረስ ለአራት ጊዜ አስተዳዳሪ ሆነው መርተዋል። በ1984 እ.ኤ.ኣ. የአስተዳዳሪ የስልጣን ዕድሜ ከ2 ዓመት ወደ 4 ዓመት አራዝመዋል። በ1992 እ.ኤ.ኣ. ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድርው አሸንፈዋል። በ1996 እንደገና ተወዳድረው አሸንፈዋል። \n \nጥያቄ: ቢል ክሊንተን ለሁለተኛ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ያሸነፉት መች ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ በ1996 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nበደቡብ ሱዳን መከላከያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ጆንሰን ጁማ ኡኮት የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ ልዑኩ አዲስ አበባ ሲገባ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ እና በሌሎች ከፍተኛ የመከላከያ አዛዦች አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ በቆይታቸውም በሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡ \n \nጥያቄ: የደቡብ ሱዳን ጠቅላይ ኤታማዦር ለምን ኢትዮጵያ መጡ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ በሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ እንግሊዝ ሀገር አንደደረሰም የወቅቱ የእንግሊዝ ንግስት ከነበረችው ንግስት ቪክቶሪያ ጋር ተገናኘ፡፡ ንግስቲቱም ልዑሉ የፈለገው እና ያሻው ይደረግለት ዘንድ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡ ልዑሉ በመቅደላ የነበረውን እልቂት በመጠኑም ቢሆን በማየቱ እና የአባቱ እና የእናቱ ተከታታይ ሞትም በልጅ አዕምሮው ሊቀበለው ከሚችለው በላይ ስለነበር እጅግ ታውኮ እንደነበር በተደጋጋሚ ተፅፎ እናገኛለን፡፡ በ1861 ዓ.ም ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ አንዲት ከተማ አዛዥ ሆኖ ስለተሾመ የ8 ዓመቱን አለማየሁን እና ሚስቱን ይዞ ወደዛው አቀና፡፡ በሄዱበት ሀገርም አለማየሁ ትምህርቱን መከታተሉን ቀጥሎ የነበረ ሲሆን ከመደበኛው ትምህርት በዘለለም ፈረስ ግልቢያ እና ሌሎች ስፖርቶችንም ያዘወትር ነበር፡፡ 1867 ዓ.ም አለማየሁ ወደ ራግቢ ትምህርት ቤት ተዛወረ፡፡ በዚህም ከቄስ ብሌክ ቤት ወጥቶ ወደ ሊው ዋርነር ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በዚህ ግን ደስተኛ ስላልነበር በቀጣዩ አመት ሚስተር ድራፐር ቤት እንዲኖር ተደረገ፡፡ ቄስ ብሌክም ካዩት የልዑሉ ባህሪ በመነሳት ልዑሉ ወታደርነት ላይ ቢያተኩር የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ተናገሩ፡፡ በዚህም ንግግር መሰረት የወታደር ትምህርት ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በአንድ ወቅት አለማየሁ ወደ ሊድስ በመሄድ በሰር ራምሰን ቤት ተቀምጦ በነበረበት ወቅት በመርዝ ተመረዘ። መርዙ ህዳር 5 ቀን 1872 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3 ሰዓት ከሩብ በተወለደ በ19 ዓመቱ ከዚህ አለም እንዲሰናበት አደረገው፡፡ አስከሬኑም ዊንድሶር ባለው የነገስታት መቀበርያ በክብር አረፈ፡፡ በመቃብሩም ላይ “የሀበሻው ልዑል አለማየሁ” የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበት እስካሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል፡፡ \n \nጥያቄ: በስንት አመተ ምህረት ነው ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ ከተማ አዛዥ ሆና የተሾመው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ በ1861 ዓ.ም ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nየእስክንድርያ ማስተማርያ ቤት የእስክንድርያ ማስተማርያ ቤት በእስክንድርያ፣ ግብጽ በጥንት (54-373 ዓም ያህል) የተገኘ የክርስትና ሥነ መለኮት ትምህርት ተቋም ነበረ። ተቋሙን የመሠረተው የኢየሱስ ሐዋርያ እና መጀመርያው የእስክንድርያ ጳጳስ፣ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ በ54 ዓም እንደ ሆነ ተጽፏል። የተቋሙ መጀመርያው መሪ በኋላ የእስክንድያ ፮ኛው ጳጳስ የሆነው ዩስቱስ እንደ ተሾመ ይታመናል። ተቋሙ ያስተማረው ከሥነ መለኮት፣ መጽሐፍ ቅዱስና ክርስትናን ጭምር፣ የግሪክኛና የሮማይስጥ ስነ ጽሁፍ፣ ሥነ ጥበብ፣ ስነ አመክንዮ፣ ሥነ ቁጥርና ስነ-ተፈጥሮ ጥናቶች ነበሩ። ለዕውሮችም ማስተማርያ አገልግሎት አቀረቡ። በፓንታይኖስ መሪነት (173-182 ዓም) ተቋሙ ስለ ትምህርቱ ዝነኛ ሆነ። ፓንታይኖስ በክርስትና ከመጠመቁ በፊት፣ የግሪኮች «ስቶዊሲሲም» ፍልስፍና ተከታይ ሆኖ ነበር። ፓንታይኖስ የግሪክ ፍልስፍና ከክርስትና ርዕዮተ አለም ጋር እንዳዋሐደ ይታስባል። ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ ከ182-194 ዓም በተቋሙ መሪነት ተከተለው። ብዙ አረመኔዎች በዚያን ጊዜ ለትምህርት ስለመጡ ከፍልስፍና መሠረት ጀምሮ የክርስትናን ትምህርት ያሳውቃቸው ነበር። በ194 ዓም የሮሜ መንግሥት ቄሣር በክርስቲያኖች ላይ ስላዘረጋው ማሳደድ፣ ቀሌምንጦስ ለጊዜው ከእስክንድርያ ሸሸ። እሱም የጻፋቻው ትልቅ መጻሕፍት ተርፈውልናል። የቀሌምንጦስ ተከታይ ኦሪገኔስ በመከራ ጊዜ ቢሆንም ተቋሙን በ195 ዓም ዳግመኛ አቆመ። ኦሪገኔስ ደግሞ ብሉይ ኪዳን በስድስት ትይዩ ዕብራይስጥና ግሪክኛ ትርጉሞች (ሄክሳፕላ) ያሳተመው እና ብዙ አንድምታ የጻፈው ዝነኛ መምህር ነው። በ373 ዓም በተካሄደው በቁስጥንጥንያ ጉባኤ፣ የጵጵሳት ቅድምንትነት ለሮሜ ፓፓ፣ ከርሱም ቀጥሎ ለአንጾኪያ ጳጳስ እንዲሰጥ የሚል ብያኔ ወረደ። ስለሆነም፣ የእስክንድርያ ጳጳስ የቀድሞ ቀድምትነቱን በማጣቱ፣ በእስክንድርያ ከተማ ውስጥ ትልቅ ሁከት ደረሰ። በዚያም ጊዜ በተደረገው ጉዳት የማስተማርያ ተቋሙ ጠፋ። \n \nጥያቄ: ከቀሌምንጦስ በኋላ ማን ተቋሙን ተረከበ?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ኦሪገኔስ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nእንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው የአውስትራሊያ የእንቁራሪት ዝርያ (ጋስትሪክ ብሩዲንግ ፍሮግ) ያልተለመደ ዓይነት የመራቢያ ሥርዓት አላት፤ የዚህች እንቁራሪት ዝርያ ከ2002 ጀምሮ እንደጠፋ ይታሰባል የሚለው ጄደብሊው ዶት ኦርግ ድረ ገጽ ነው። \n \nጥያቄ: እንቁላሏን በሆዷ የምትታቀፈው የእንቁራሪት ዝርያ የየት ሀገር ነች?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ የአውስትራሊያ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nሮማንሽ ሮማንሽ ወይም ሩማንች (Rumantsch) ከስዊስ አገር 4 ብሔራዊ ቋንቋዎች 1ዱ ሆኖ ሌሎቹ 3 ጀርመንኛ ጣልኛና ፈረንሳይኛ ናቸው። ከሮማይስጥ የታደገ ቋንቋ በመሆኑ የሮማንስ ቋንቋ ቤተሠብ አባል ነውና በተለይ የሚመስለው ፈረንሳይኛ ወይም እጣልኛ ነው። የሚናገረው በግራውብውንደን (ግሪዞን) ካንቶን ስዊስ በሚኖሩ 60,000 ሰዎች ነው። ይህ ከስዊስ አገር ሕዝብ ብዛት 1% ብቻ ሲሆን ከስዊስ አገር ብሔራዊ ቋንቋዎች ሁሉ ትንሹ ነው። እንኳን በስዊስ አገር ከሚኖሩት ስርቦ-ክሮዌሽኛ ተናጋሪዎች ቁጥር ብዛት (111,000) በግማሽ ያንሳል። በስሜን እጣልያ አገር ዛሬ ለሚናገሩ ቋንቋዎች ለፍሪዩልያንና ለላዲን ቅርብ ዘመድ ነው። \n \nጥያቄ: ከስዊስ አገር ብሔራዊ ቋንቋዎች ሁሉ ትንሽ ተናጋሪ ያለው ቋንቋ የቱ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ ሮማንሽ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nማሊ የማሊ ሪፐብሊክ (ማሊ) በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ የለሽ ሀገር ናት። ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች በስፋት ሁለተኛ ናት። ከአልጄሪያ፣ ኒጄር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጊኔ፣ ሴኔጋል እና ሞሪታኒያ ጋር ድንበር ትዋሰናለች። ማንዴ ሕዝቦች አውራጃውን ሠፍረው ተከታታይ መንግሥታት አጸኑ። እነዚህም የጋና መንግሥት፣ የማሊ መንግሥትና የሶንግሃይ መንግሥት ያጠቅልላሉ። በነዚህ መንግሥታት ውስጥ ቲምቡክቱ ለትምርትና ለመገበያየት ቁልፍ ከተማ ነበረች። በ1583 ዓ.ም. በሞሮኮ በተካሄደ ወረራ የሶንግሃይ መንግሥት ኃይል ለማነስ ጀመር። ማሊ በ1880 እ.ኤ.አ. በፈረንሣይ ቅኝ ተገዝታ «ፈረንሳያዊ ሱዳን» ወይም «የሱዳን ሪፐብሊክ» ትባል ነበር። ፈረንሳያዊ ሱዳን በኅዳር 16 ቀን 1951 ዓ.ም. በፈረንሳያዊ ማሕበረሠብ ውስጥ 'ራስ-ገዥ ሁኔታ' አገኝታ በመጋቢት 26 1951 ዓ.ም. ከሴኔጋል ጋር አንድላይ የማሊ ፌደሬሽን ሆኑ። ይህ የማሊ ፌዴሬሽን በሰኔ 13 ቀን 1952 ነጻነት አገኘ። ነገር ግን በነሐሴ 14 ቀን ሴኔጋል ከፌዴሬሽኑ ወጣች። በመስከረም 12 ቀን 1953 ዓ.ም. ፈረንሳያዊ ሱዳን በሞዲቦ ኪየታ ስር ራሷን 'የማሊ ሬፑብሊክ' አዋጀችና ከማሕበረሰቡ ወጣች። ሞዲቦ ኪየታ በ1968 እ.ኤ.ኣ. በተደረገው መፈንቅለ መንግሥት ከወረደ በኋላ እስከ 1991 እ.ኤ.አ. ድረስ ማሊ በማውሳ ትራዎሬ ተመራች። በ1991 እ.ኤ.አ. የተካሄዱ ተቃውሞች ወደ መፈንቅለ-መንግሥት አመሩ። ከዚያም የተሸጋጋሪ መንግሥት ተቋቋመና አዲስ ሥነ-መንግሥት ተጻፈ። በ1992 እ.ኤ.አ. አልፋ ዑመር ኮናሬ የማሊን የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን አሸነፉ። ማሊ ከባሕር ጋር ግንኙነት የላትም። የሀገሩ አብዛኛው ክፍል በሰሐራ በረሃ ውስጥ ይገኛል። ከተፈጥሮ ሀብቶች ውስጥ ወርቅ፣ ዩራኒየም፣ ፎስፌት፣ ካዎሊን፣ ጨው፣ ኖራ (ላይምስቶን) ይጠቀሳሉ። የማሊ ፓርላማ 147 ሰዎች ሲኖረው እነዚህ ተወካዮች በህዝብ ብዛት ነው የሚመረጡት። ማሊ ከዓለም ደሀ ሀገሮች አንዷ ስትሆን 65 ከመቶ የሚሆነው መሬት በረሃ ነው። አብዛኛው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ በኒጅር ወንዝ አካባቢ ነው የሚካሄደው። 10 ከመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሰ የሚኖር ሲሆን 80 ከመቶ የሚሆነው የሥራ ሃይል በእርሻና ዓሣ ማጥመድ ተሰማርቷል። የኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኩራል። የሸክላ ሥራ በሴቶች የሚከናወን ሲሆን በነጋዴዎች በገበያዎች ይሸጣል። ሸክላዎቹ የሚሰሩበት ባሕላዊ ሂደት የቱሪስት መሳቢያ ነው። \n \nጥያቄ: ማሊ የምትገኘው የት አህጉር ውስጥ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ አፍሪካ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nበኢትዮጵያ ካሉ የኢንተርኔት አገልግሎቶች ተጠቃሚዎች ውስጥ 59 ነጥብ 5 ከመቶ የሚሆኑት ስልክ ቁጥርን እንደ ይለፍ-ቃል /password/ እንደሚጠቀሙ ጥናት አመለከተ። ተጠቃሚዎች የስልክ ቁጥርን መጠቀማቸው ጠንካራ የይለፍ-ቃል እንደተጠቀሙ እንደሚሰማቸውም በጥናቱ ተመላክቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ጥቃት በከፍተኛ መጠን እያደገ መምጣቱም ነው የተነገረው። በኢትዮጵያ ያለው በሳይበር ደህንነት የግንዛቤ መጠንም ዝቅተኛ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብና ደህንነት ኤጀንሲ ጥናት ያመለክታለል። ኤጀንሲው በ2011 ዓ.ም 1 ሺህ 635 የሚሆኑ ግለሰቦች ላይ ሀገር-አቀፍ የሳይበር ደህንነት ምዘና ጥናት አከናውኗል። በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል 975 (59 ነጥብ 5 በመቶ) ያክሉ ስልክ ቁጥርን እንደ ይለፍ-ቃል/password/ በመጠቀም ጠንካራ የይለፍ-ቃል እንደተጠቀሙ እንደሚሰማቸው ጥናቱ ያመለክታል። በተጨማሪም 59 ነጥብ 1 በመቶ ያክሉ የጥናቱ ተሳታፊዎች የይለፍ ቃሎቻቸውን የሚታይ ቦታ ላይ ጽፈው ማስቀመጥን እንደ ማስታወሻ መንገድ እንደሚጠቀሙበት ገልጸዋል። 67 ነጥብ 6 ከመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎች ትክክለኛ ናቸው ብለው እንደሚያምኑም ነው የተነገረው። በመሆኑም የሳይበር ደህንነት ጉዳይ በቸልታ ሊታለፍ የማይገባውና የለት ተለት የህይወታችን አካል እየሆነ በመምጣቱ ተገቢውን ትኩረትና ጥናቃቄ ልናደርግ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብና ደህንነት ኤጀንሲ የሰራውን ጥናት አስመልክቶ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። \n \nጥያቄ: የኢንፎርሜሽን መረብና ደህንነት ኤጀንሲ በ2011 ባደረገው ጥናት በመቶኛ ምን ያህል ሰዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎች እውነት እንደሆኑ ያመናሉ ብሏል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ 67 ነጥብ 6 ከመቶ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nበእንግሊዝ የተሰራውና የመንገድ ላይ ምልክት ማድረጊያው ሮቦት ሙከራውን አድርጓል። ሮቦቱ የተለያዩ የመንገድ ምልክቶችን በማስመር ወጪና ጊዜን ይቆጥባል ተብሏል። የሙከራ ስራውን ባደረገበት ወቅት ውጤታማነት ታይቶበታል የተባለውቅ ሮቦት፥ በአራት ሰዓት በ12 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር መንገድ ላይ ምልክቶችን ማድረጉ ተነግሯል። ይህ ቴክኖሎጂ ጊዜን በመቆጠብ ስራውን የሚሰሩ ሰራተኞች ያጋጥማቸው የነበረውን ድካም፣ የሚደርሰውን የወገብ ጉዳት እና ምልክት በሚያደርጉበት ወቅት የሚከሰተውን የመኪና አደጋ ይቀንሳል ነው የተባለው። ይህን ቴክኖሎጂ የተቀበሉት ዋይ ጂ የመንገድ ተቋራጭ ቡድን ሥራ አስኪያጅ ዌን ጆንስተን፥ ቴክኖሎጂው መጨናነቅን ለመቀነስ፣ ጊዜን እና ገንዘብን ለመቆጠብ እንዲሁም ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው ነው ያሉት። እንዲሁም ለተሻለ እና ጥራት ላለው የመንገድ ላይ ምልክት ያገለግላልም ብለዋል። ምንጭ፡- traffictechnologytoday.com ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision \n \nጥያቄ: የመንገድ ላይ ምልክት ማድረጊያው ሮቦት የሚያስገኛቸው ጥቅሞች ምን ምን ናቸው?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ሰራተኞች ያጋጥማቸው የነበረውን ድካም፣ የሚደርሰውን የወገብ ጉዳት እና ምልክት በሚያደርጉበት ወቅት የሚከሰተውን የመኪና አደጋ ይቀንሳል ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nአብርሀም ሊንከን (የካቲት ፮ ቀን ፲፰፻፩ ዓ.ም. - ሚያዝያ ፰ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም.) ድረስ የኖሩ ከ፲፰፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ድረስ ፲፮ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ነበሩ። ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ከአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ጆን ዊልክስ ቡዝ በተባለ ነፍሰ ገዳይ እጅ በጥይት ተመትተው ተገደሉ። የአብርሀም አባት ማሀይም ገበሬ ቢሆንም፣ አብርሀም ከልጅነት ጀምሮ እራሱን በትጋት ያስተምር ነበር። በ፲፰፻፳፮ ዓ.ም. ለኢሊኖይ ክፍለ ሀገር ምክር ቤት መቀመጫ ተመረጡ። የሕግ ትምህርት በጠንካራ ትጉነት አጥንቶ የሕግ ባለሙያ ሆነ። ከ፲፰፻፳፱ ዓ.ም. ጀምሮ የባርነት ተቃዋሚ ሆነ። ከአፍሪካ የተወሰዱት ጥቁር ሕዝቦች በግብርና መሥራት እንዲገደዱ ትክክለኛ ወይም ጥሩ ሀሣብ አይደለም ብለው አመኑ። ዳሩ ግን በ1834 ብዙ ባርያዎች ባገለገሉበት ቤተሠብ ውስጥ ያደገችውን ሚስታቸውን ሜሪ ቶድን አገቡ። ሜሪ ያለ ባርያዎች ከባልዋ ጋር መኖር ትንሽ የተቸገሩ ቢሆነም ከጊዜ ብዛት ግን ለምደዉ 4 ወንድ ልጆችን በተከተሉት አመታት ወለዱ። በ፲፰፻፵፮ ዓ.ም. የባርነት ተቃዋሚዎች ወገን ሪፐብሊካን ፓርቲ መሥርተው አብርሀም ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ። በ፲፰፻፶፪ ዓ.ም. የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ዘመቻ፣ እሳቸው የሪፐብሊካን ዕጩ ሆኑ። ምርጫው በተደረገበት ቀን በጥቅምት ፳፰ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.፣ ሊንከን አሸነፉ። በጦርነቱ የስሜን ሠራዊት ከብዛታቸው የተነሣ በአራት ዓመት ውስጥ አሸነፉ። በዚህ ጊዜ ላይ ሊንከን ለአመጸኖቹ ባርዮች ነጻነት አዋጁ። ያላመጹ ዜጎች ባርያዎች ግን በዚያን ጊዜ ነጻ አልወጡም። በ፲፰፻፶፮ዓ.ም.ምርጫ ሊንከን በቀላል ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ተመረጡ። በሚያዝያ ፪ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. የኮንፌደራት ሠራዊት እጁን ሰጠ። ነገር ግን ሚያዝያ ፯ ቀን የመድረክ ትርዒት ሲያዩ በነፍሰ ገዳዩ በጆን ዊልክስ ቡዝ እጅ በጥይት ተመትተው በማግሥቱ ሞቱ። ከዚህም ትንሽ በኋላ ባርነት በሕግ በሙሉ ተክለክሎ የተረፉት ባርያዎች ነጻነት አገኙ። \n \nጥያቄ: አብርሃም ሊንከን መቼ ሞተ?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nየ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፲፱ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የነበረ ሲሆን ከሰኔ ፬ እስከ ሐምሌ ፬ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ተካሄዷል። ውድድሩን ለማቅረብ የተካሄደው ዕጣ ውስጥ የአፍሪካ ሀገሮች ብቻ እንዲሳተፉ ነበር የተፈቀደው። ደቡብ አፍሪካ ግብፅና ሞሮኮን በማሸነፍ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫን ያቀረበች አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች። ፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $420 ሚሊዮን ነው። ይህም ከ2006 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የስልሳ ከመቶ ዕድገት አለው። ከዚህ ውስጥ $40 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1 ሚሊዮን ተረከበ። ግጥሚያዎቹ በዘጠኝ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አስር ስታዲየሞች ውስጥ ነው የተካሄዱት። የዋንጫ ጨዋታው በጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኘው ሶከር ሲቲ ስታዲየም ነው የተከናወነው። የምድብ ድልድል ሥነ ስርዓቱ በኬፕ ታውን፣ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ኬፕ ታውን ዓለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል በኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ተከናወነ። ሥነ ስርዓቱ የቀረበው በደቡብ አፍሪካዊቷ ተዋናይ ሻርሊዝ ቴሮን እና የፊፋ ዋና ጸሐፊ ዠሮም ቫልክ ነው። የዕጣ ኳሶቹን ያወጡት ዴቪድ ቤክሃም፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ጆን ስሚት፣ መካያ ንቲኒ፣ ማቲው ቡዝ እና ሲምፊዌ ድሉድሉ ናቸው። የፊፋ ዳኛዎች ኮሚቴ ፳፱ ዳኛዎችን ለዓለም ዋንጫ መርጧል። እነዚህም ከኤ.ኤፍ.ሲ. አራት፣ ከካፍ አስር፣ ከኮንሜቦል ስድስት፣ ከኮንካካፍ አራት፣ ከኦ.ኤፍ.ሲ. ሁለት እና ከዩኤፋ አስር ዳኛዎችን ያጠቃልላል። እንግሊዛዊው ዳኛ ሀዋርድ ዌብ የዋንጫ ጨዋታውን እንዲዳኝ ተመርጧል። \n \nጥያቄ: ደቡብ አፍሪካ ስንተኛውን የፊፋ የዓለም ዋንጫ አዘጋጀች?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ፲፱ኛው ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nሴኔጋል ከ፹ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሏት። ፓርላማዋ ሁለት ምክር ቤቶች አሉት። አንዱ ፻፳ መቀመጫዎች ያሉት የብሔራዊ ስብሰባ (እንግሊዝኛ፦ National Assembly) ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ፻ መቀመጫዎች ያሉት ሴኔት ነው። ሴኔጋል ራሱን የቻለ ህግ ተርጓሚ አካል አላት። ዳኛዎቹ የሚሾሙት በፕሬዝዳንቱ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሴኔጋል የዴሞክራሲ ሂደት ስኬታማ ነው ከሚባሉት የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ናት። የአካባቢ አስተዳዳሪዎች በፕሬዝዳንቱ ነው የሚሾሙት። ማራባውት የሚባሉ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎችም በሴኔጋል ጠንካራ የፖለቲካ ተፅእኖ አላቸው፡ ከ፪ ሚሊዮን ነዋሪዎች ያሉበት የሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የሀገሩ ትልቁ ከተማ ነው። ሁለተኛው ፭፻ ሺህ ሰዎች የሚኖሩበት ቱባ ከተማ ነው። ሴኔጋል ከ12.5 ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ አላት። ከዚህ ውስጥም ወደ ፵፪ ከመቶ በገጠር ነው የሚኖረው። የአሜሪካ የስደተኖች ኮሚቴ ባቀረበው የ2008 እ.ኤ.አ. የዓለም ስደተኞች አጠቃላይ ቅኝት መሠረት ሴኔጋል በ2007 እ.ኤ.አ. ወደ 23,800 የሚገመቱ ስደተኞች ይኖሩባታል። ከዚህ አብዛኛዎቹ የመጡት ከሞሪታኒያ ነው። ስደተኞቹ በንድዮም፣ ዶዴል እና በሴኔጋል ወንዝ አቅራቢያ በሚገኙ ሠፈሮች ይኖራሉ። የአገር ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከብዙ ኗሪ ቋንቋዎች 11ዱ በተለይም ዎሎፍኛ አገራዊ ዕውቅና አላቸው። ሌሎቹ ባላንታኛ፣ ማንዲንክኛ፣ ፑላርኛ (ፉላኒኛ)፣ ሰረርኛ፣ ሶኒንክኛ፣ ኖንኛ፣ ማንካኛኛ፣ ማንጃክኛ፣ ጆላኛ እና ሀሣኒያ አረብኛ ናቸው። ፖርቱጊዝኛም በትምህርት ቤት ይማራል፣ የካቦ ቨርዴ እና የጊኔ-ቢሳው ኅብረተሠቦችም ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል ይናገራሉ። ከሴኔጋል ሕዝብ 94% የእስልምና አማኞች፣ 5% ክርስትና (ባብዛኛው ካቶሊክ)፣ 1% የኗሪ አርመኔነት ተከታዮች ናቸው። የመንግሥት ሃይማኖት የለውም። በሴኔጋል ልማዳዊ ባሕል ግሪዮት የተባሉ ሽማግሎች ታሪኮቻቸውን በአፍ ቃል ይደግማሉ። ሴኔጋል ለሙዚቃዊ ስልቶቹ ይታወቃል፤ በተለይ የሚወድደው ዘመናዊው ስልት ምባላክስ ተብሏል። በሴኔጋል አበሳሰል በተለይ አሣ፣ ዶሮ፣ በግ፣ አተር፣ ዕንቁላል፣ በሬ ይጠቀማሉ፤ እስላም አገር እንደ ሆነው መጠን ግን አሳማ አይበላም። ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ስኳር ድንች፣ ምስር፣ ጥቁር-ዐይን አተር ደግሞ በሴኔጋል አበሳሰል በሰፊ ይገኛሉ። በእስፖርት በኩል፣ ከሁሉ የሚወደደው ባህላዊው የሴኔጋል ትግል ግጥሚያ ሲሆን፣ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ ደግሞ እጅግ ይወደዳሉ። \n \nጥያቄ: የሴኔጋል ፓርላማ ስንት ምክር ቤት አለው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ሁለት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nባህር ዛፍ ባህር ዛፍ በተፈጥሮው ከአውስትራሊያ የሚገኝ አበባ ሚያብብ የዛፍ ወገን ነው። በአለም ላይ 700 አይነት የባህር ዛፍ ዝርያዎች አሉ፣ ከነዚህ ውስጥ 15ቱ ከአዉስትራሊያ ውጭ በተፈጥሮ ሲገኙ ከ700ው 9ኙ ዘር ብቻ አውስትራሊያ ውስጥ በተፈጥሮ አይገኝም። በኢትዮጵያ በተለይ የታወቁት፦ ነጭ ባሕር ዛፍ ቀይ ባሕር ዛፍ ናቸው። በአዲስ አበባ ከተማ ዳግማዊ ምኒልክ የባህር ዛፍ ፍሬ አስመጥተው ካስተከሉ በኋላ ይሄ አዲስ ዕጽ ዓየሩ ተስማምቶት ለከተማዋ የአረንጓዴ መቀነት ይመስል በጥቂት ዓመታት አሸበረቃት። በ፲፱፻፵ ዎቹ ይሄ መቀነት እስከ አርባ ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት በመያዙ ከተማዋን በሰፊው የባህር ዛፍ ከተማ የተባለ ቅጽል ስምን አትርፎላት ነበር። በአሁኑ ወቅት ባህር ዛፍ አለም አቀፍ ተፈላጊነት አግኝቷል። ይህም የሆነበት ምክንያት ቶሎ በማደግ አስፈላጊ እንጨት ይሰጣል የዛፉ ዘይት ለጽዳት እና እንዲሁም በራሪ ትንኞችን ለማባረር እንዲሁም ለመግደል ይረዳል:: አልፎ አልፎ ለወባ ትንኝ ማደግ ምቹ የሆኑ አረንቋወችን ለማድረቅ ይረዳል። ሆኖም ግን ባህር ዛፍ ከላይ ለተጠቀሱት አላማወች ቢያገለግልም ትልቁ ችግሩ ውሃ በጣም ይወዳል። ስለሆንም እርሱ በተተከለበት ሌሎች አትክልቶች የማደግ እድላቸው ዝቅተኛ ነው። ኢትዮጵያም ውስጥ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ምንጮችን እንዳደረቀ መረጃ አለ። \n \nጥያቄ: በዓለም ላይ ምን ያህል የባሕር ዛፍ ዝርያዎች አሉ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ 700 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nዩጋንዳ ዩጋንዳ ሪፐብሊክ (ወይም ዑጋንዳ) በምስራቅ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። በኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ይዋሰናል። የዩጋንዳ ሰም የመጣው ከቡጋንዳ መንግሥት ነው። ከአረቦችና አውሮፓውያን በ1800ቹ ከመድረሳቸው በፊት ብዙ የሚታወቅ ነገር አልነበረም። በ15ተኛ መቶ ክፍለ-ዘመን ችዌዚ የተባለውን መንግስት በአፈ ታሪክ ይገኛል። አረቦችና አውሮፓውያን በ19ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሲደርሱ ብዙ መንግሥቶች በቦታው ነበሩ። እነዚህም በንዮሮ ፣ ቡሶጋ ፣ ቡጋንዳ ፣ ቶሮ እና አንኮልን ያጠቃልላሉ። ከ1894 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በታላቁ ብሪታን ስትመራ ነበር። የተለያዩ ቦታዎች ከተዋሃዱ በኋላ ዩጋንዳ በ1914 እ.ኤ.አ. ቅርጿን ያዘች። በ1966 እ.ኤ.አ. ጠቅላይ ሚኒስትር ሚልተን ኦቦቴ ሕገ-መንግሥቱን አፍርሰው እራሳቸውን ፕሬዝዳንት አደረጉ። በ1971 እ.ኤ.አ. ኢዲ አሚን ሀገሩን መምራት ጀመሩ። የኢዲ አሚን አመራር 300,000 የሚገመቱ ዩጋንዳውያንን አስጨርሷል። በ1979 እ.ኤ.አ. የታንዛንያ ኃይሎች ኢዲ አሚንን ከሥልጣን ያስወግዳሉ። ሚልተን ኦቦቴ ወደ ሥልጣን ይመለሳሉ ግን በ1985 እ.ኤ.አ. እንደገና ይወርዳሉ። ያሁኑ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሙሴቪኒ ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በሥልጣን ላይ ናቸው። ፕሬዝዳነንቱ አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይመርጣሉ። ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሎ ሲባምቢ ናቸው። ዩጋንዳ በመሬት የተቆለፈች ብትሆንም ታላላቅ የውሃ አካላት አሉ። ከነዚህ ውስጥም ቪክቶሪያ ሐይቅ፣ አልበርት ሐይቅ፣ ክዮጋ ሐይቅ እና ኤድዋርድ ሐይቅ ይዘረዘራሉ። ታላላቅ ከተማዎች በቪክቶሪያ ሐይቅ አቅራቢያ ይገኛሉ። እነዚህም ካምፓላንና እንትቤን ያጠቃልላል። ዩጋንዳ በ70 ወረዳዎች የተከፋፈለች ስትሆን እነዚህም በአራት አመራር ክልሎች ውስጥ ናቸው። አራቱ አመራር ክልሎች ሰሜናዊ ፣ ምሥራቃዊ ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራባዊ ይባላሉ። ወረዳዎቹ በዋና ከተማዎቻቸው ነው የሚሰየሙት። በዩጋንዳ ውስጥ የመዳብ እና ነጭ ብረት ክምችቶት አሉ። ግብርና ዋናው የኤኮኖሚ ሴክተር ነው። ከ80 በመቶ በላዩ የስራ ኃይል በግብርና ነው የተሰማራው። ቡና ዋናው የኤክስፖርት ትርፍ ምንጭ ነው። ከ1986 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መንግሥቱ ከሌሎች ሀገሮችና ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመሆን በኢዲ አሚን ጊዜ የወደቀውን ኤኮኖሚ ለማንሳት ተጣጥሯል። ዩጋንዳ ለብዙ ብሔረሰቦች ቤት ነው። ከነዚህ ውስጥ ግን አንድ ትልቁን ሕዝብ ብዛት የሚወክል የለም። 40 አካባቢ የሚሆኑ ቋንቋዎች ባሁኑ ጊዜ ይነገራሉ። ከነጻነት በኋላ እንግሊዝኛ ብሔራዊ ቋንቋ ተደርጓል። ብዙ ተናጋሪዎች ያሉት ቋንቋ ሉጋንዳ ሲሆን የአቴሶ ቋንቋ በሁለተኛነት ይከተላል። ኪስዋሂሊ ዋናው የንግድ ቋንቋ ነው። የዩጋንዳ የትምህርት ስርዐት የሰባት ዓመት መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት፣ ስድስት ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እና ከ3 እስከ 5 ዓመት ከሁለተኛ ደረጃ በኃላ ትምህርት ያጠቃልላል። \n \nጥያቄ: በዩጋንዳ በሁለተኛነት ደረጃ የሚነገረው ቋንቋ ምንድን ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ የአቴሶ ቋንቋ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nሳህሌ ደጋጎ ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ከእናታቸው ከወይዘሮ ደጊቱ ፈይሣ እና ከባላንባራስ ደጋጎ አለቤ አብራክ በ1923 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ልዩ ስሙ ነጆ ከተባለው ሥፍራ ተወለዱ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በነቀምት አንደኛ ደረጃ እና በአዲስ አበባ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ዘመናዊ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በነበረው ልዩ የውትድርና ፍቅር በቀድሞ 1ኛ ክፍለ ጦር በኋላም ማዕከላዊ ዕዝ ተብሎ በተጠራው የክ/ዘበኛ የጦር ክፍል ውስጥ በ1942 ዓ/ም ተቀጥሯል። በነበረው ሙያዊ ብቃትና ወታደራዊ ሥነ ሥርዓት አክባሪነት ከተራ ወታደርነት በአንድ ጊዜ የሃምሳ አለቅነት ማዕረግ ማግኘት የቻለው ሣህሌ፤ በሂደት እስከ ኮሎኔል ደረጃ ደርሷል። ወደ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት እንደዚሁም ወደ የማዕከላዊ ዕዝ የሙዚቃ ባንድ ኃላፊነት ከመሸጋገሩ በፊት በእግረኛ ባንድ ውስጥ “ክላርኔት” የተሰኘው የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዎች የነበረው ሣህሌ ደጋጎ፣ የሙዚቃን ትምህርት የቀሰመው ከፈረንሣዊው መምህሩ ሙሴ ኒኮ መሆኑን የሕይወት ታሪኩ ላይ ተጠቅሷል። ከክላርኔት በተጨማሪ “አኮርዲዮን፣ አልቶ-ሳክስ፣ ፒያኖ” የተሰኙትን የሙዚቃ መሣሪያዎችንም በብቃት ይጫወት ነበር። በጠቅል ራዲዮ ጣቢያ (በተቋቋመ ጊዜ ) በአኮርዲዮን ጥዑም ዜማ ለጣቢያው አድማጮች ሲያንቆረቁር ከነበሩት የሙዚቃ ሰዎች መካከል ሣህሌ ደጋጎ የመጀመሪያው ነበር። ከእነ ሻለቃ ግርማ ይህደጎ፣ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ እና ከሻለቃ ባሻ ገብረዓብ ተፈሪ ጋር በመሆን የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራን ስም እፁብ ድንቅ በማድረጉ በኩል የበኩሉን ሚና ተጫውቷል። ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑም ባሻገር የአጫጭር እና ረዣዥም ድራማዎች ፀሐፊ የነበረው ሣህሌ፣ «ሁለገብ የታሪክ ማኅደር» ያሰኘውን ተግባር በሕይወት ዘመኑ አከናውኗል። \n \nጥያቄ: ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ በየትኛው የሙዚቃ ዘርፎች ይሰሩ ነብር?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ሙዚቃ ቀማሪነት፣ ዜማና ግጥም ደራሲነት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nባሕር-ዳር ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች። ባሕር-ዳር ከአዲስ አበባ 565 ኪ.ሜ ወደ ሰሜን-ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ባህር ዳር ከጢስ አባይ በ30 ኪሎሜትር ስለምትርቅ ለጎብኚዎች አመቺ ቦታ ላይ ናት። ባህር ዳር የአንድ የአስፋልት ንጣፍ ያለው ኤርፖርት የሰፊ ገበያና የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች እና ታሪካዊ እና ጥንታዊ ግዳማት መግኛ ቦታ ናት። ባሕርዳር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ \"ከባሕሩ-ዳር\" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል። ባሕር-ዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡ ባሕር-ዳር በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤ የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡ የተቆረቆረችበትን ዓመት፣ የቆረቆሩትን ቀደምት ሠዎች፣ የሠፈሮችን ስሞች፣ ለባሕር-ዳር የተገጠሙትና የተዘፈኑ ታሪካዊ ግጥሞችና ስነ ቃሎች፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጎጆ ቤት ወደ አሁኑ ይዞታው አመጣጥ (ባሕር-ዳርን ስናስብ ጊዮርጊስን ሚካኤልን እና ገበያውን ከገበያው አካባቢ የነበረውን ፍርድ ቤት ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚል አስተያየት ስላለ ነው)፣ ባሕር-ዳር እንደባሕር ዳርነቱ ከመቆርቆሩ በፊት በሚካኤል እና በሽመምብጥ ሠፈር አካባቢ ስለነበረው አሰፋፈር፣ ስለማዘጋጃቤቱ፣ ስለ አውቶቡስ ተራው፣ ስለ ድባነቄ ተራራ፣ እና ስለ መሳሉት፣ ስለፖሊቴክኒክ፣ ስለዓባይ ወንዝና ድልድዩ፣ ስለዓባይ ወንዝና ስለጣና ሐይቅ መገናኛ እና ስለሌሎችም ቁልፍ ነገሮችን ማቅረብ የሚችሉ አፈታሪኮች አሉ። \n \nጥያቄ: ባሕር ዳር ስንት ክፍለ ከተሞች አሏት?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ 3 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nአዳማ /ኢዜአ/መስከረም 23/2012 የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ስምንት የምርምርና የልህቀት ማእከላት እያደራጀ መሆኑን ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተሾመ አብዶ ለኢዜአ እንደገለጹት ግንባታቸው ከ90 በመቶ በላይ የተጠናቀቀው የምርምር ፓርኮችንና የልህቀት ማዕከላትን በመሳሪያ ለማደራጀት 86 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በጀት ተመድቦ እየተሰራ ነው ብለዋል። በዚህም ሁለት ሊትል ስታር የተባሉ ሳተላይቶች በደቡብ ኮሪያና ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች በመገጣጠም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የፋርማቲካል የልህቀት ማእከሉ የባህል መድኋኒቶችን በመቀመምና በምርምር በማዘጋጀት ወደ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ምርት እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ተሾመ በተለይም በባህላዊ መድኋኒቶች ዙሪያ በትኩረት የምርምር ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ነው ብለዋል። የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በ19 የትምህርት ፕሮግራሞች ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመደበኛና በኤክስቴሽን ፕሮግራም ተቀብሎ ማስተማር ላይ ይገኛል። \n \nጥያቄ: የአዳማ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በስንት ትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እያስተማረ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ በ19 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nአፄ ዘርአ ያዕቆብ አጼ ዘርአ ያዕቆብ በዘውድ ስማቸው ቆስጠንጥንዮስ ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግስት ክብረ እግዚእ በ1399 እ.ኤ.አ. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር የድሮውፈተገር ክፍለ ሐገር ተወለዱ(ከቀኝ ያለውን ካርታ ይመልከቱ) ። የነገሡበትም ዘመን 1434 - 1468 እ.ኤ.አ. ነበር። ያረፉትም በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው። የዘርዓ ያዕቆብ አባት ቀዳማዊ ዳዊት ባረፉ ጊዜ፣ እንደ ጥንቱ የኢትዮጵያ ባህል ወግ መሰረት፣ ታላቅ ወንድማቸው የነበሩት ቀዳማዊ ቴወድሮስ በ1414 ሲነግሱ ታናሽ ወንድማቸውን በግዞት ወደ አምባ ግሽን እንዲሄድ አደረጉ። አጼ ዘርዓ ያእቆብ ቆየት ብለው በጻፉት መጽሀፈ ብርሃን በተሰኘው ድርሰታቸው መሰረት እስከ ነገሱበት ሰኔ 20 ፣ 1434 ዓ.ም. ድረስ በግዞት ግሸን ተራራ (አምባ ግሸን) ላይ ለሚቀጥሉት 20 አመታት በእስር ኖሩ። ሆኖም ግን በግዞት እያሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊያቸው መጠን እየበዛ ሄደ። በነዚህ አመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከዓመት ወደ ዓመት እይተበላሸ ሂዶ በመጨረሻ ከአምባው ላይ ለሹመት ሲወርዱ አገሪቱ በእርስበርስ ሽኩቻ እየታመሰች፣ በሃይማኖት በኩልም መከፋፈል ተፈጥሮ የውጭ ሀይሎችም ከነገ ዛሬ አጠቁን እየተባለ ይሚፈራበት ሁኔታ ገጠመው። የወደፊቱ ንጉስ ብዙ እድሜውን ያሳለፈው ከሰው ተለይቶ አምባ ላይ ስለነበር፣ የዲፕሎማሲ ጥቅሙ አልተረዳውም ነበር። ይልቁኑ ፊት ለፊት የተጋረጡትን የሃገሪቱን ችግሮች በሚያስፈራ ድፍረት እና ምንም በማያወላዳ ጽናት ተጋፈጠው። ዓፄ ዘርአ ያእቆብ ንጉስ ከሆኑ በኋላ ንግስት እሌኒን በ1434 አገቡ፣ ከዚያም በ1436 ዘውዳቸውን ጫኑ። በ1442 በሰንበት ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤተክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲሰክን ቆይቱ በደብረ ምጥማቅ ጉባኤ (ተጉለት) ፣ የግብጾቹ ጳጳሳተ በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል ። ሌላው በዘመናቸው የተከሰተው ሃይማኖታዊ ንቅናቄ የደቀ እስጢፋ ወገኖች እምነት ነው። እነዚህ እስጢፋኖስ የተባለ መነኩሴ ባስተማራቸው መሰረት ለመስቀል መስገድና ለስእል አድኅኖ ለድንግል ማርያም መስገድ አይገባም የሚሉ ነበሩ።ተከራክረው አጼ ዘርዓ ያዕቆብ አሸንፈዋል። በ1445 እና ከዚያ በኋላ በተነሱ ጦርነቶች ላይ በመሳተፍ ሁሉን በድል በማጠናቀው ግዛታቸውን ያሁኒቷን ሶማልያን ሁሉ ያቅፍ ነበር። በ1456 ዓ.ም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ በነበሩበት ቦታ ታላቅ ብርሃን ስለታየ የነበሩበትን ቦታ ደብረ ብርሃን በማለት የሃገሪቱ ዋና ከተማ አድርገው ቆርቁረዋል። እስከ እለት ህልፈታቸውም ደብረ ብርሃን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበረች።ኢትዮጵያዊ መንፈሳዊ ፈላስፋ። አጼ ዘርአ ያዕቆብ በጦር ውሎአቸው ብቻ ሳይሆን የሚታወቁት፣ ከ 20 በላይ መጻህፍትንም በመድረስና ለትውልድ በማቅረብ ጭምርም ነው። \n \nጥያቄ: አጼ ዘርአ ያዕቆብ ያረፉት በየት ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nየፀሓይ አካል ለፍጹም ሉል የቀረበ ቅርጽ አለው፤ ዋልታዎቿን የሚያገናኘው ዳያሜትር ከወገቧ ዳያሜትር የሚያንሰው በ10 ኪሎ ሜትር ብቻ ነውና። ኮከባችን ፀሓይ በሥነ ፈለክ ሊቃውንት እጅግ ብዙ ጥናት ተደርጎባታል። ኾኖም ኮከቢቱን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ገና አልተመለሱም። ለምሳሌ በገሃድ የሚታየው የፀሓይ ገጽ ስኂን 6,000 ኬ (ኬልቪን) ኾኖ ሳለ፣ የዳርቻ ከባቢ አየሯ ስኂን ከሚሊዮን ኬ በላይ እንዴት ሊኾን እንደቻለ አይታወቅም። የፀሓይ ዕድሜ በአንዳንድ ሊቃውንት እሳቤ 4.6 ቢሊዮን ዓመት ገደማ ነውና በዕድሜ እኩሌታዋ ላይ የምትገኝ ኮከብ ተደርጋ ትታያለች። የኮከቢቱ መጠነ-ቁስ ጥንቅር 74% ሃይድሮጂን፣ 25% ሂሊየም ሲኾን፣ ቀሪው 1% ደግሞ ክብደት ያላቸው ርዝራዥ የብረቴ ንጥረ-ነገሮች ጥርቅም ነው። ስለ ፀሓይ የሰው ልጅ ቀዳሚ መሠረታዊ ግንዛቤ ብርሃን-ሰጭ ሰማያዊ ጻሕል መኾኗን፣ ደግሞም ከአድማስ በላይ እና በታች በመኾን ለመዓልትና ሌሊት መኖር ምክንያት መኾኗን መረዳት ነበር። በብዙ የቅድመ-ታሪክ እና የጥንት ዘመን ባህሎች ፀሓይ እንደ ብርሃናዊ አምላክ ወይም እንደ ዲበ-ተፈጥሯዊ ክሥተት ትታይ ነበር። የፀሓይ አምልኮ ለምሳሌ የ-ኢንካ (ደቡብ አሜሪካ) እና አዝቴክ (የዛሬዋ ሜክሲኮ) ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ዐይነተኛ ገጽታ ነበር። ከፀሓያዊ ክሥትቶች ጋር የተያያዙ ብዙ ጥንታዊ ሐውልቶች ተገንብተው እንደነበር ለማሰብ የሐጋይ ሶልስቲስን ለማስታወቅ የተገነቡትን የድንጋይ ሜጋሊት በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። ከችንክር ከዋክብት አንጻር ስትታይ ፀሓይ የግርዶሽ መስመርን ተከትላ በዞዲያክ ውስጥ በዓመት አንድ ዑደት የምታደርግ ትመስላለች። ስለዚህ በጥንት የግሪክ የሥነ-ከዋክብት ሊቃውንት ዘንድ ፀሓይ ታዋቂ ከነበሩ ሰባት ፈለኮች እንደ አንዱ ትቈጠር ነበር። በአንዳንድ ቋንቋዎች ሰባቱ የሳምንት ዕለታት በነዚህ ፈለኮች ይጠራሉ። \n \nጥያቄ: ከፀሀይ የመጠነ ቁስ ጥንቅር ነገሮች መካከል የሂሊየም መጠን ምን ያህል ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ 25% ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nከ1936 ጀምሮ ኤርትራ የኢኮኖሚ እድገት ማሳየት ችሏል። በ30ዎቹ መጨረሻ 2፣198 የኢንደስትሪ ተቋሞች በአገሪቱ ተመስርተዋል። ይሁንና ጣሊያኖች አገሪቱ እራሷን እንድትችል ሳይሆን የነርሱ ጥገኛ እንድትሆን ነበር ያደረጉት፣ ለዚህ ሲሉ አብዛኛው ምርት ከውጭ ያስመጡ ነበር። ከ10-15% የሚሆነው የአገሬው ወንድ ሃይል በኢንደስትሪ፣ በእርሻና በጥቃቅን የተላላኪ ስራወች ተቀጥርው ይሰሩ ነበር። ከ1936-41 ድረስ አብዛኛውን የአግሬውን ወንድ ቀጥሮ ያሰራ የነበረው የቅኝ ገዥው ውትድርና ተቋም ነበር (40% ወይም 60፣000 ለአቅመ አዳም የደርሱ ወንዶችን)። እኒህ ወታደሮች ኢትዮጵያን ለመውረር ያገለገሉ ሲሆን ለዚህ ታማኝነታቸው ምክንያቱ ቅኝ ገዥወች በኤርትራ ላይ ያሰፈኑት ፖለቲካዊ መረጋጋት እንደምክንያት ይጠቀሳል። የጤና፣ የገበያ ኢኮኖሚ እንዲሁም ቁሳዊ ፍጆታ መስፋፋት በ1905ዓ.ም. 250 ሺህ ብቻ የነበረው የኤርትራ ህዝብ ወደ 614 ሺሕ በ1935 ዓ.ም. እንዲያድግ አድርጓል። ትግርኛ ተናጋሪው ክፍል በዚህ ጊዜ 54% የአገሪቱ ክፍል ነበር። እኒህ ለውጦች በአገሬው ላይ የስነ ልቦና ለውጥን አስከተሉ፣ ስለሆነም ከኢትዮጵያውያን ጐረቤቶቻቸው የተለዩ ህዝቦች የመሆን ማንነትን ፈጠረ። ሁለተኛው የአለም ጦርነትን ተከትሎ እንግሊዞች ከአንግሎ ግብጻዊ ሱዳን በመነሳት ጥር 1941 በኤርትራ ላይ ጥቃት አደረሱ። ከሶስት ወር በኋላ የከረን ጦርነትን በማሸነፍ ሚያዝያ 1941 ሙሉ ኤርትራን ተቆጣጠሩ። የእንግሊዝ ወታደራዊ አገዛዝ(BMA) በጣሊያኖች ምትክ አገሪቱን ማስተዳደር ጀመረ። 1947 ጣሊያን በፈረመችው የሰላም ውል መሰረት ኤርትራ ለአራቱ ሃይላት ተሰጠች። ከዚህ በኋላ ኤርትራ የጣሊያን ቅኝ መሆኗ አበቃላት። \n \nጥያቄ: በ1935 የኤርትራ ሕዝብ ብዛት ስንት ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ 614 ሺሕ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ለወጣት ለአዛውንት የሚመቹ ደግ እናት፡፡ በኢትዮጵያ የሚድያ ታሪክ ስም ያተረፉ፡፡ ለምርምር የማይደክሙ፡፡ ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን እነሆ ታሪካቸውን አቀረበ፡፡ ጋዜጠኛዋ በ79 አመታቸው ሀምሌ 14 2013 ህይወታቸው አልፏል፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ በ1934 አመተ ምህረት ከአባታቸው ከአቶ መኩሪያ ወልደስላሴ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ሶስና ወርቅነህ ተወለዱ፡፡ እናታቸው ወይዘሮ ሶስና ወርቅነህ የሀኪም ወርቅነህ እሸቴ ልጅ ናቸው፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሳንፎርድ ተማሪ ቤት ነበር የተከታተሉት፡፡ ወይዘሮ እሌኒ ያደጉት ካዛንቺስ አካባቢ ሲሆን የልጅነት ዘመናቸው በደስታ የተሞላ ነበር፡፡ በተለይ በሳንፎርድ ተማሪ ቤት ጥሩ የእንግሊዝኛ ችሎታቸውን ከማዳበራቸው በላይ ደስ የሚል የመዝናኛ ጊዜን አሳለፈው ነበር፡፡ ቴኒስ መጫወት ፤ ዋና መዋኘት ፣ ቴአትር ማየት እና መተወን ደስ ይላቸው ነበር፡፡ እንዲያውም ለልኡል መኮንን ሆስፒታል ማሰሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ቴአትር መስራታቸውን ወይዘሮ እሌኒ በህይወት በነበሩ ጊዜ ተናግረዋል፡፡ በተለይ አያታቸው ክቡር ሀኪም ወርቅነህ እሸቴ ዳንስ ያለማምዷቸው እንደነበር አይዘነጉትም፡፡ ወይዘሮ እሌኒ መኩሪያ ፣ ማህበራዊ ሳይንስ የማጥናት ግብ ቢኖራቸውም ቤሩት የነጻ የትምህርት እድል አግኝተው ወደዚያ በ1951 ግድም ያቀናሉ፡፡ ነገር ግን የነርስነትን ትምህርት ቢጀምሩም አቋርጠው ወደ እናት ሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡ በመቀጠልም ወደ ብስራተ ወንጌል ሬድዮ በማቅናት በእንግሊዝኛው ክፍል ተቀጠሩ፡፡ ያኔ በሬድዮ ከወይዘሮ እሌኒ ጋር ይሰሩ ከነበሩት ባለሙያዎች መካከልም ጋዜጠኛ ልኡልሰገድ ኩምሳ ይጠቀሳል፡፡ ወይዘሮ እሌኒና ጋዜጠኛ ልኡልሰገድ ዜና ሲያቀርቡ ያለበት ቪድዮ ከዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ዘንድ ይገኛል፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር በግንቦት 18 1955 ሲፈረም ጋዜጠኛ ከነበሩት መካከል ወይዘሮ እሌኒ ይጠቀሳሉ፡፡ በወቅቱ ገና የ21 አመት ወጣት የነበሩት ወይዘሮ እሌኒ መሪዎች ሲመጡ የተደረገውን ታሪካዊ አቀባበል በፍጹም አይዘነጉትም፡፡ \n \nጥያቄ: ወ/ሮ እሌኒ በስንት አመታቸው አረፉ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ በ79 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተገኝተዋል። በሰመዕታት መታሰቢያ ቀን የካቲት 12 ቀን በየአመቱ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፤አባት አርበኞች፤ እና የህብረተሰብ ክፍሉ በስድስት ኪሎ ታስቦ ይውላል፡፡ \n \nጥያቄ: በአዲስ አበባ ለ84ኛ ጊዜ የተከበረው የመቼ ሰማዕታት መታሰቢያ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ የየካቲት 12 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nአዶልፍ ሂትለር አዶልፍ ሂትለር (ጀርመንኛ Adolf Hitler አዶልፍ ሂትለ) እ.አ.አ. ከ1933 ጀምሮ የጀርመን ቻንስለር እንዲሁም ከ1934 ጀምሮ ደግሞ የጀርመን መሪም (Führer) ጭምር የነበረ ሰው ነው። ሂትለር በሚያዝያ 13 ቀን 1881 ዓ.ም. (20 አፕሪይል 1889 እ.ኤ.አ.) በዛሬይቷ ኦስትሪያ ተወለደ። በሚያዝያ 22 ቀን 1937 ዓ.ም. (30 አፕሪይል 1945 እ.ኤ.አ.) በርሊን ውስጥ ከአንድ ቀን በፊት ካገባት ሚስቱ ኤቫ ብራውን ጋር የራሱን ህይወት አጠፋ። በ1925 ዓ.ም. መጀመርያ የሂትለር ናዚ ወገን ከጓደኞቹ ወገን ጋር በራይክስታግ ምክር ቤት ትብብር መንግሥት ለመሥራት በቂ መንበሮች አልነበራቸውም። ተቃራኒዎቻቸው የኰሙኒስት ወገን 17% መንበሮች ስለ ነበራቸው የሂትለር ወገኖች የድምጽ ብዛት ሊያገኙ አልተቻላቸውም ነበር። በዚያው ዓመት ግን ከምርጫው ትንሽ በፊት የራይክስታግ ሕንጻ በእሳት ተቃጠለ። ይህ የኰሙኒስቶች ሥራ ነው ብለው የሂትለር ወገን ኰሙኒስት ፓርቲ ቶሎ እንዲከለከል አደረጉ። ስለዚህ ከምርጫው በኋላ የኰሙኒስትን መንበሮች ስለ አጡ የሂትለርም ወገኖች አሁን ከ50% መንበሮች በላይ ስላገኙ፣ የትብብር መንግሥት ሠሩና ወዲያው በድንጋጌ አቶ ሂትለር ባለሙሉ ሥልጣን አደረጉት። ሂትለር የጻፈው የርዮተ አለሙ ጽሑፍ «የኔ ትግል» (Mein Kampf) ሟርት ብቻ ነው። ለመጥቀስ ያህል፦ «ትኩረቴ ወደ አይሁዶች ስለ ተሳበ፣ ቪየናን ከበፊት በሌላ ብርሃን ለማየት ጀመርኩ። በሄድኩበት ሁሉ አይሁዶችን አየሁዋቸው፤ በብዛትም እያየኋቸው፣ ከሌሎች ሰዎች ፈጽሞ እንድለያቸው ጀመርኩ።»... «የግዛቱ (ኦስትሪያ-ሀንጋሪ) ዋና ከተማ የከሠተውን የዘሮች ውሑድ ጠላሁት፤ የዚህን ሁሉ የቼኮች፣ ፖሎች፣ ሀንጋርዮች፣ ሩጤኖች፣ ሰርቦች፣ ክሮዋቶች ወዘተ. የዘሮች ድብልቀት፤ በሁላቸውም መካከል፣ እንደ ሰው ልጅ መከፋፈል ሻገቶ፣ አይሁዶችና ተጨማሪ አይሁዶች።» በነበረው ዘረኛ አስተዳደሩ 6 ሚሊዮን የአውሮፓ አይሁዶችን እና 5 ሚሊዮን ሌሎች የተለያዩ ሀገራት ህዝቦችን (በተለይም ስላቮችን) በገፍ (በሆሎኮስት) አስጨርሷል። በሂትለር ሥር የናዚዎች ፍልስፍና በሂንዱኢዝም እንደሚገኘው በዘር የተከፋፈለ ካስት ሲስተም መመሥረት አይነተኛ ነበር። «አርያኖች» የተባሉት ዘሮች በተለይም የጀርመናውያን ብሔሮች ከሁሉ ላዕላይነት እንዲገኙ አሠቡ። ይህ ዝብረት የተነሣ በርግ ቬዳ ዘንድ በ1500 ዓክልበ. ያህል ወደ ሕንድ የወረሩት ነገዶች «አርያን» ስለ ተባሉ ነው፤ በጥንትም «አሪያና» የአፍጋኒስታን አካባቢ ስም የዘመናዊው ኢራንም ሞክሼ ነበር። በናዚዎቹ እንደ ተዛበው ግን ታሪካዊ ባይሆንም የ«አርያኖች» ትርጓሜ ጀርመናውያን ብቻ ነበሩ፤ ስላቮች (በተለይ የሩስያና የፖሎኝ ሕዝቦች) ግን አርያኖች ሳይሆኑ እንደ ዝቅተኞች ተቆጠሩ። የሂትለር እብደት እየተራመደ በ1926 ዓም የሀንጋሪ ሕዝብ ደግሞ «አርያኖች» ተደረጉ፣ በ1928 ዓም የጃፓን ሕዝብ እንኳን በይፋ «አርያኖች» ተደረጉ፤ በ1934 ዓም የፊንላንድ ሕዝብ ወደ «አርያኖች» በሂትለር ዐዋጅ ተጨመሩ። በሙሶሊኒ ሥር የፋሺስት ጣልያኖች እኛም አርያኖች ነን ቢሉም ጣልያኖች አርያን መሆናቸው በናዚዎች ዘንድ መቸም አልተቀበለም ነበር። \n \nጥያቄ: የአዶልፍ ሂትለር መንግሥት የጃፓን ሕዝቦችን መቼ ነበር እንደ አርያኖች ዘር የቆጠረው?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ በ1928 ዓም ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nቶክ ፒሲን ቶክ ፒሲን (Tok Pisin) በስሜን ፓፑዋ ኒው ግኒ የሚናገር የእንግሊዝኛ ቋንቋ ዲቃላ ነው። ከእንግሊዝኛ ስዋሰው በጣም ተለውጧልና ዛሬ እንደ ራሱ ቋንቋ ይቆጠራል። የፓፑዋ ኒው ግኒ መደበኛ ቋንቋ ሆኖ በ120,000 ያሕል ተናጋሪዎችና በ4 ሚሊዮን እንደ 2ኛ ቋንቋ ይነገራል። የቶክ ፒሲን አጀማመር በፓሲፊክ ውቅያኖስ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ የተላያዩም ልሣናት የሚችሉ ሰራተኞች አንድላይ ለአትክልት ስፍራዎች ሲሰሩ ነበር። ብዙ ጊዜ የእነዚህ ሰራተኞች የጋራ ቋንቋ ጥቂት ቀላል እንግሊዝኛ ቃሎች ብቻ ነበር። ስለዚህ አዲስ \"የቋንቋ ዲቃላ\" ተወለደ። ከእንግሊዝኛ ብቻ ሳይሆን ብዙ ቃላት የተወሰዱ ከደሴተኞቹ ቋንቋዎች፣ ከጀርመንኛ፣ ወይም ከፖርቱጊዝ ነበር። ይህ ቋንቋ \"ፕጅን\" ተብሎ አሁን ሶስት ተወላጆች አሉት፣ እነሱም ቢስላማ (በቫኑዋቱ) ፒጂን (በሰሎሞን ደሴቶች) እና ቶክ ፒሲን ይባላሉ። ቶክ ፒሲን በአንዳንድ ትምህርት ቤት የትምህርት ቋንቋ ነው። \n \nጥያቄ: የቶክ ፒሲን አጀማመር በየትኛው ውቅያኖስ ላይ ባሉ ደሴቶች የነበሩ ሰዎች ነበሩ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ በፓሲፊክ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በአዲስ አበባ ከተማ በደቡብ-ምሥራቅ አቅጣጫ ከአራዳ በስምንት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የአገሪቱ ዋና አድማሳዊ የንግድና የግንኙነት በር ነው። አውሮፕላን ወደ ኢትዮጵያ መግባት የጀመሩት በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ በጃን ሜዳ እና አቃቂ ያርፉ እንደነበር በታሪክ ተዘግቧል። የመጀመሪያው ቋሚ የአውሮፕላን ጣቢያ ግን የተሠራው በአምሥቱ የፋሺስት ዘመናት ሲሆን የካቲት ፳፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ/ም አክሱም አካባቢ ላይ ከነጥያራው ተከስክሶ በሞተው አብራሪያቸው፣ “ኢቮ ኦሊቬቲ” ስም ሠይመውት የነበረው የልደታ የጥያራ ጣቢያ ነው። በዚሁ በፋሺስት ወረራ ዘመን ‘አላ ሊቶሪያ’ የተሰኘው ኩባንያ በአገር ውስጥ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ነገሌን፤ ሞቃዲሾን፤ ድሬ ዳዋን፤ ጎራኄን፤ ጂቡቲን፤ አሰብን፤ ጂማን፣ ጋምቤላን ደምቢ ዶሎን፤ ጎንደርን አስመራን፤ ደሴን፤ ለቀምትን እና አሶሳን የሚያገለግሉ የበረራ መሥመሮች ሲኖረው ከአድማስ ባሻገር ደግሞ ከተማዋን በካርቱም፣ ዋዲ ሃይፋ፤ ካይሮ፣ ቤንጋዚ እና ሲራኩሳ አድርጎ ከሮማ ጋር የሚያገናኝ የበረራ መሥመርም ነበረው። ከድል ወዲህ ልደታ አውሮፕላን ጣቢያ፤ የብሪታኒያ ጦር ኃይሎች ሲገለገሉበት ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታኅሣሥ ፳፩ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ሲመሠረት ዋና ጣቢያው እዚያው ነበር። ዳሩ ግን የአየር መንገዱ አገልግሎት እየተስፋፋ ሲመጣና ትላልቅ ጄት አውሮፕላኖች እንደሚያስፈልጉት ግልጽ ሲሆን፣ የልደታ አየር ጣቢያ ብቃት እንደሌለው እና ለጄት አየር ዠበቦችም ማሳረፊያ የማይስማማ መሆኑ ታምኖበት የአማራጭ ሥፍራ ፍለጋ ተጀመረ። የአዲሱንም አየር ጣቢያ ዝርዝር ጥናት እንዲያዘጋጅ ውሉ ለአሜሪካዊው ‘አማን እና ዊትኒ’ ኩባንያ ተሰጥቶ፤ ጥናቱ በ፲፱፻፶ ዓ/ም ተገባዶ አማራጩ ሥፍራ ቦሌ እንዲሆን ተወሰነ። የአየር ጣቢያውን የግንባታ ወጪ ከአሜሪካዊው ‘ኤክስፖርት-ኢምፖርት’ ባንክ በተገኘ ብድር ተሸፍኖ ሥራው ተጀመረ። ጠቅላላ ግንባታው ተጠናቆ ሲያልቅ ኅዳር ፲፩ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ/ም ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተብሎ፣ በንጉሠ ነገሥቱ ተመርቆ ተከፈተ። \n \nጥያቄ: ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ከምን ቦታ በስምንት ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ ከአራዳ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nጋና ጋና በአፍሪካ አትላንቲክ ጠረፍ ላይ የተገኘ አገር ሲሆን ከ24 ሚሊዮን ኗሪዎች በላይ አሉት። የጋና ስራ ቋንቋ እንግሊዝኛ ሲሆን፣ ሌሎች ኗሪ ቋንቋዎች በተለይም ትዊኛ (አካንኛ) በሰፊ ይነገራሉ። የ«ጋና» ስያሜ በታሪክ የድሮ «ጋና መንግሥት» ወይም «ዋጋዱጉ መንግሥት» ለማክበር በ1949 ዓም ተመረጠ። እንዲያውም ያው መንግሥት እስከ 1068 ዓም ድረስ ከጋና ወደ ስሜን-ምዕራብ በአሁኑ ማሊ ይገኝ ነበር እንጂ የዛሬውን ጋና መቸም አልገዛም። «ጋና» በትክክል የዋጋዱጉ መንግሥት አለቆች ማዕረግ ሆኖ ነበር። ዋጋዱጉ መንግሥት በ1068 ዓም ግድም ከወደቀ ቀጥሎ፣ የአካን ብሔሮች ከዚያው ፈልሰው በዛሬው ጋና ሠፈሩና መጀመርያ ግዛቶችን መሠረቱ። ከ1662 እስከ 1949 ዓም ድረስ የአሻንቲ መንግሥት ባካባቢው ቆየ፤ በ1894 ዓም ይህ የብሪታንያ አሻንቲ ጥብቅ ግዛት ሆነ። ከ1949 ዓም አስቀድሞ የዩናይትድ ኪንግደም ጥገኛ ግዛት ሲሆን በወርቅ ሀብቱ ምክንያት «የወርቅ ጠረፍ ጥገኛ ግዛት» (ጎልድ ኮስት ፕሮቴክቶሬት) በመባል ይታወቅ ነበር። ከ1984 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ እና ፓርላሜንታዊ መንግሥት ኖሮታል። አብዛኞቹ ኗሪዎች (70%) በተለይ በደቡቡ ክርስቲያን ሲሆኑ፣ በተለይ በስሜኑ 16% የእስልምና ተከታዮች ናቸው። የተረፉትም የኗሪ አረመኔነትን እምነቶች ይከተላሉ። የጋና ዋና ምርቶች ካካዎ፣ ዘይት፣ አልማዝ ናቸው። በአለሙ ከሁሉ ትልቅ የሆነው ሠው ሰራሽ ሐይቅ፣ ቮልታ ሐይቅ፣ በጋና ይገኛል። እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው። የጋና አበሳሰል በተለይ በኮቤ፣ ጐርጠብ፣ የስኳር ድንች፣ ባቄላ፣ በቆሎ፣ ኦቾሎኒ፣ ባሚያና ሩዝ ይሠራል። \n \nጥያቄ: በጋና ከ1662 እስከ 1949 ዓም የቆየው መንግሥት ምን ተብሎ ይጠራ ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ የአሻንቲ መንግሥት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ በሌላ አጠራሩ ታላቁ ቅዱስ ባስሊዮስ በቀጰዶቂያ የቄሣርያ ኤጲስ ቆጶስ ነበር። የንቂያን የሊቃውንት ጉባዔ የሚደግፍና አርያኒዝምንና የአፖሊናረስን ተከታዮችን የክርስትና አመለካከት ተቃውሞ ትክክለኛውን መንገድ ያስተማረ ታላቅ አሳማኝ የሃይማኖት ፈላስፋና መሪ ነበር ። ቅዱስ ባስሊዮስ ከሃይማኖት ፈላስፋነቱ ሌላ ድሆችንና ኑሮን ማሸነፍ ያቃታቸውን በመንከባከብ ይታወቃል ። በተጨማሪም የማኅበራዊ ኑሮ ፣ የሥርዐተ ጸሎትና የጉልበት ሥራ ለገዳማዊ ኑሮ መመሪያን መሥርቷል። ባስሊዮስ ከቅዱስ ጳኩሚስ ጋር የማኅበራዊ ገዳማዊነት አባት ተብሎ በምሥራቃዊ ክርስትና ይታሰባል ። ዳሮግን በምሥራቅም በምዕራብም በቅዱስ ደረጃ ነው የሚከበረው ። እነዚህ ሁለት ጎራዎች ታላቅ የቤተክርስቲያን አባት የሚለውን ስያሜ ከዮሐንስ አፍወርቅና ከግሬጎሪዮ ናዚያንዘስ ጋር ሰተውታል። ባስሊዮስ ከቀዳማዊ ባስሊዮስና ከኤሚልያ የቄሣሪያዋ በ፫፻፳ ዓም አካባቢ በቀጰዶቂያ ተወለደ ። እናትና አባቱ እግዚአአብሔርን በጣም የሚወዱና ጸሎተኞች የነበሩ ሰዎች ነበሩ ። የእናቱ አባት ከቆስጠጢኖስ ፩ኛ በክርስትና ማመን በፊት ሰማዕት ሆኖ ያለፈ ሰው ነበረ። ጸሎተኛ ባልቴቱ ማክሪናም የጎርጎርዮስ ታውማታርገስ (የኒዎ ቄሣርያን ቤተክርስቲያን በአቅራቢያው የመሠረተ) ተከታይ የነበረች ባስሊዎስንና አራቱን ወንድሞቹንና እህቱን ፣ ወጣትዋ ማክሪና ፣ ናውክራቲየስ ፣ ጴጥሮስ የሰባስቴውንና ፣ ጎርጎርዮስ የኒሳውን (ወደፊት ታላቅና የተከበሩ ቅዱሳን የሚሆኑ) በክርስትና ሃይማኖት ሥርዐት አሳደገች ። ባስሊዮስ በቄሣርያ ማዛካ ቀጰዶቂያ በአሁኑ ዘመን አጠራር ካይዜሪ (ቱርክ) ትምህርት ቤት በ፫፻፵፪ ፵፫ ዓ.ም.አካባቢ ተምሩዋል ። እዛም ጎርጎርዮስ ናዚያንዘስን የረጅም ጊዜ ጉዋደኛ የሚሆነውን ተዋውቋል። ባስሊዮስና ጎርጎርዮስ አንድላይ በመሆን ለከፍተኛ ትምህርትና በተጨማሪ የሊባኒየስን ትምህርታዊ ንግግር ለማጥናት ወደ ቁስጥጥኒያ አምርተዋል ። ሁለቱ በአቴንስ በ፫፵፪ ዓ.ም. አካባቢ ጀምሮ ለስድስት ዓመት ተቀምጠዋል። በዛም ቆይታቸው ጁሊያን ዘአፖስቴት ወደፊት ንጉሥ የሚሆን ተማሪ ተዋውቀዋል። ባስሊዮስ አቴንስን በ፫፵፰ ለቆ ወደ ግብፅና ሶርያ ከተጉዋዘ በኋላ አገሩ ቄሣርያ የሕግ ሥራ በመለማመድና የንግግር ችሎታ ሲያስተምር ቆየ። \n \nጥያቄ: የቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሣርያ ጋደኛ ማን ናቸው?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ጎርጎርዮስ ናዚያንዘስን ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nመጋቢት ፪ ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በልሚ ወቼ ሞሹ የኢትዮጵያ አርበኞችና የፋሺስት ኢጣሊያ ወገኖች ጦር ውጊያ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም - ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎ ፩ሺ፭፻ ወታደሮች በመማረክ አሶሳን ያዘ። ፲፱፻፵፱ ዓ/ም - የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት (በኋላ ፕሬዚዳንት) ሪቻርድ ኒክሰን ኢትዮጵያን ጎበኙ ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበራቸውን የሚወስን የጋራ ጉባዔ ለመመሥረት መወሰናቸውን አስታወቁ። ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል። ፲፱፻፹፪ ዓ/ም - ሊትዌኒያ እራሷን ከሶቭየት ኅብረት አስተዳደር ውጭ ነጻ መሆኗን አወጀች። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ በልብ ምታት አረፈ። \n \nጥያቄ: ከኮንጎ የመጣ የቤልጅግ ሠራዊት የጣልያንን ሠራዊት አሸንፎ ፩ሺ፭፻ ወታደሮች በመማረክ አሶሳን የያዘው መቼ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ ፲፱፻፴፫ ዓ/ም ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የዓለም አቀፍ የአስትሮኖሚካል ኅብረት ሲምፖዚየም ልታካሂድ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ። ዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ኅብረት ሲምፖዚየምና የአፍሪካ አስትሮኖሚ ማኅበር የምክክር መድረክ ከመስከረም 26-30 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ይህን አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ እንደተብራራው በሁለቱ መድረኮች ከ30 አገራት ከ200 በላይ ዓለም አቀፍ ሳይንቲስቶች፣ ኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎችና ባለድርሻ ተቋማት ሾለ አስትሮኖሚና ስፔስ ሳይንስ ይመክራሉ። በኢንስቲትዩቱ የአስትሮኖሚና አስትሮፊዚክስ ምርምር ክፍል ኃላፊ ዶክተር ማሪያና ፖቪች እንዳሉት በዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚካል ኅብረት በተለያዩ አገራት በየዓመቱ የሚዘጋጁ ሲምፖዚየሞች አሉ። ኅብረቱ መቶኛ ዓመቱን እያከበረ ይህንንም ክብረ በዓል ያከናወናቸውን ስራዎችና ስኬቶች እየገመገመ በተለያዩ ሁነቶች እያከበረ ነው። እስካሁን 355 ሲምፖዚየሞች የተካሄዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ ሲካሄድ የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ሲምፖዚየሙን የምታካሂድ ሶስተኛዋ የአፍሪካ አገር ስትሆን በደቡብ አፍሪካና ቡርኪናፋሶ መሰል ሲምፖዚየም ተካሂዷል። ሲምፖዚየሙ በዘርፉ ልምድና እውቀት ያካበቱ ተመራማሪዎች ልምዳቸውን የሚያጋሩበትና ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ በሳይንስ ዘርፍ እየከወኗቸው ያሉ ተግባራትን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስገንዘብ የሚያስችል ነው ብለዋል። የምስራቅ አፍሪካ አስትሮኖሚ ለልማት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ አለምዬ ማሞ በበኩላቸው እንደገለጹት የአፍሪካ አስትሮኖሚ ማኅበር የሚያዘጋጀው የአፍሪካ አስትሮኖሚ የሳይንስ ምክክር መድረክ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል። መድረኩ በአፍሪካ አስትሮኖሚ ምን አይነት አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚችል የሚያመላክት ራዕይና ስትራቴጂ ሰነድ የሚነደፍበት ይሆናል ነው ያሉት። የማኅበሩን እንቅስቃሴ ለሳይንስና ለጠቅላላ ማኅበረሰቡ ማስተዋወቅ፣ የአህጉሪቱ ወጣት ተመራማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማስቻል፣ በአፍሪካ በአስትሮኖሚና ስፔስ ሳይንስ ዘርፍ የሚሰሩ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ማጎልበት የመድረኩ ዓላማዎች መሆናቸውን አንስተዋል። መድረኩ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብርና ትስስር መፍጠር ያስችላልም ነው ያሉት። ነገና ከነገ በስቲያ አራት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ በዘርፉ ሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪያቸውን እየሰሩ ላሉ ተማሪዎች የእውቀትና ክህሎት ስልጠናም ይሰጣል። ከሁለቱ መድረኮች ጎን ለጎን በተመረጡ 10 የህዝብ ትምህርት ቤቶች በተግባር የታገዘ አስትሮኖሚን የማስገንዘብ ሾል እንደሚሰራም ተገልጿል። ለበርካታ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሾለ አስትሮኖሚ ሳይንስ ግንዛቤ የመፍጠር እንዲሁም ለሁለተኛ ደረጃ መምህራን የሚሰጥ ስልጠና መኖሩም ተጠቁሟል።     \n \nጥያቄ: በአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ አራት ኪሎ ካምፓስ ለሚገኙ ስንተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነው ስልጠና ለመስጠት የታሰበው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ ሁለተኛና ሶስተኛ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ። \n \nጥያቄ: የኢያን ስሚዝ መንግሥት በዚምባቡዌ ከሦስት መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ የተፈራረመው ስምምነት መቼ ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ በማርች 1978 እ.ኤ.አ. ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nአብዱልራዛቅ እ.ኤ.አ. በ1994 ላይ ያሳተሙት ‹ፓራዳይዝ› የተሰኘው ልብ ወለድ ታንዛኒያ ውስጥ በ20ኛው ምዕት ዓመት የልጅ አስተዳደግ ምን እንደሚመስል ፍንትው አድርገው ያሳዩበት ነው። በዚህ ልብ ወለድም ዓለም አቀፉን የ‹ቡከር› ሽልማት ለማግኘት መቻላቸውን ቢቢሲ ዘግቦታል፡፡ እንደ የኖቤል ኮሚቴ የሥነ ጽሑፍ ክፍል አገላለጽም፣ ‹‹[የእሳቸው] ገጸ ባህርያት ሁሌም ቢሆን በባህልና አኅጉራት መካከል የሚሽከረከሩ፣ በአሁን ሕይወትና በመጪው ሕይወት መካከል የሚመላለሱ ናቸው። በቀላሉ ሊያልፉት የማይችሉት ከባድ እውነታ ውስጥ ናቸው፡፡›› እ.ኤ.አ. በ1948 በዛንዚባር የተወለዱት አብዱልራዛቅ፣ እ.ኤ.አ. በ1960ዎቹ መገባደጃ አገረ እንግሊዝ የገቡት ስደተኛ ሆነው ነው። በቅርቡ ጡረታ እስከወጡበት ዕለት ድረስ በካንተርበሪው የኬንት ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዝኛና የድኅረ ቅኝ ግዛት ሥነ ጽሑፎች ፕሮፌሰር ነበሩ። ሽልማቱ፣ ደራሲው ያለፉበትን የስደተኞች ቀውስንና ቅኝ አገዛዝን በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ውይይት እንዲደረግባቸው ያስችላል ብለዋል፡፡ ‹‹እነዚህ በየዕለቱ ከእኛ ዘንድ ያሉ ነገሮች ናቸው። ሰዎች እየሞቱ ነው፣ ሰዎች በዓለም ዙርያ አሁንም እየተጎዱ ነው፡፡ በእነዚህን ጉዳዮች ላይ በፍፁም ቀናነትና አስተውሎት መንገድ መነጋገር መላ መምታት አለብን፤›› ብለዋል የኖቤል ተሸላሚው አብዱልራዛቅ። ዓምና በሥነ ጽሑፍ ያሸነፉት አሜሪካዊው ገጣሚ ሊዊስ ግሉክ መሆናቸው ይታወሳል። የስዊድኑ አካዴሚ በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት ከሸለማቸው ታላላቅ ደራስያን መካከል ከአፍሪካ አኅጉር ስድስት ደራስያን ይገኙበታል፡፡ እነርሱም ዎሌ ሾንካ (ናይጀሪያ)፣ ነጂብ ማኅፉዝ (ግብፅ)፣ ናዲን ጎርዲመር (ደቡብ አፍሪካ)፣ ጄ.ኤም ኮትዚ (ደቡብ አፍሪካ)፣ እና ዶሪስ ሌሲንግ (ዚምባቡዌ -እንግሊዝ) ይገኙበታል፡፡ \n \nጥያቄ: አብዱልራዛቅ የየት ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ነበሩ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ በካንተርበሪው የኬንት ዩኒቨርሲቲ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nቴክኖ ካሞን 17 በዘጋቢ ፊልም ታግዞ ወደ ገበያ መግባቱን ኩባንያው አስታወቀ :: በዓለም አቀፍ ደረጃ በአዲሱ ትውልድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ቴክኖ ሞባይል ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም በለቀቀው አዲሱ የCAMON 17 ተከታታይ ስልክ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ መቻሉን ኩባንያው አስታውቋል:: ይህ ፈጠራ የታከለበት ቴክኖ ካሞን 17 ስልክ ማጠንጠኛውን በሰልፊ ላይ ባደረገ ዘጋቢ ፊልም የተመረቀ ሲሆን ድርጅቱ ምርቱን ከማስተዋወቅ ባለፈ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና በሰብዓዊነት ዘርፎች ላይ የበለጠ ጥረት ለማድረግ ያለውን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል:: “The Rise of Selfie” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ይህ ዘጋቢ ፊልም ፊልም በማስመረቂያ ፕሮግራሙ ላይ የቀረበ ሲሆን ታዳሚዎቹ በእርግጥም ቴክኖ የዚህን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት በተጨባጭ እና በስሜት እየሰራ መሆኑን ስለመገንዘባቸው ድርጅቱ ገልጿል:: አዲሱ የቴክኖ የንግድ አምባሳደር ክሪስ ኢቫንስ “ሕያው እና በስሜት የተሞላ ምስል ትፈልጉ ይሆናል፣ ነገር ግን መልካም ምስል የሚያደርገው ‘እጅግ ግለሰባዊ’ ስለሆነ ነው። ይህ ደግሞ ሁሌም ቴክኖ በፅኑ ከሚያምንበት እና ከሚታወቅበት ሃሳብ ጋር ይጣጣማል ብለዋል፡፡ የስማርት ስልክ ፅንሰ ሃሳብ ብራንዱ ላይ ሳይሆን ተጠቃሚው ላይ ማውጠንጠን እንዳለበትም ነው የንግድ አምባሳደሯ የጠቆሙት፡፡ የፋሽን ሞዴል የሆኑት ሣል በፊልሙ ላይ እንዳሉት እንደ ቴክኖ ካሞን 17 ያሉ የሰልፊ ስልኮች ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ምስል ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ተወዳጅ ፎቶዎችን በማንሳት ምስላቸውን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል:: በተጨማሪም የተሻለ ማንነት እንዲኖር ለማድረግ እዲሁም በደመነብስ ወደተሻለ እኛነት እንድንመጣ ለራሳችን የምንጠቁምበት መንገድ ነው ብለዋል:: ቴክኖ ካሞን 17 ሁልጊዜ “በልባቸው ወጣት” ለሆኑ እና ለአዳዲስ ነገሮች ራሳቸውን ለሚያነሳሱ ተጠቃሚዎች ምልክት ለመሆን የተሰራ ነው ያለው ድርጅቱ፥ ሰዎች ራሳቸውን በይበልጥ ለመግለጽ እንዲችሉ ያስችላቸዋልም ብሏል፡፡ ኮቪድ19 ባስከተለው ተጽዕኖ ሰዎች ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ለመገናኘት ሰልፊን ማዘውተራቸው የሰልፊን ተግባር ይበልጥ አስፈላጊ ያደረገው በመሆኑ ጉዳዩን ቴክኖ እና ሌሎች የስልክ አምራቾች በአጽንኦት እንዲያጤኑት አድርጓቸዋል:: በቴክኖ ካሞን 17 ስልክ ሰዎች ህይወት ያላቸው የሚመስሉ ፎቶዎችን ማጣጣም ብቻ ሳይሆን በFHD ስክሪን ላይ በጣም ግልጽ የሆነ ምስልን ማየት እንደሚያስችላቸው ነው የተገለጸው:: ይህ ከፍተኛ ጥራት ያለው ስክሪን ተጠቃሚዎች በቪዲዮ ጥሪዎች ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ተወዳዳሪ የሌለው ግልጽነት የሚሰጣቸው ሲሆን ተጠቃሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መመልከት እና ከፍተኛ አቅም የሚፈልጉ ጌሞችን መጫወት እንደሚችሉም ነው ኩባንያው የገለጸው፡፡ ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!   \n \nጥያቄ: ቴክኖ ካሞን 17 የተባለው አዲሱ የቴክኖ ኩባንያ ስልክ መቼ ለገበያ ቀረበ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nአሜሪካ ለሁዋዌ ተጨማሪ ሽያጮችን ልታግድ መሆኑን አስታወቀች። አሜሪካ የምታመርታቸውን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት የተመረቱ የቴሌኮም ምርቶችን ለግዙፉ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያ እንዳይሸጡ ለማገድ ስለመዘጋጀቷም ነው የገለጸችው። የትራምፕ አስተዳደር ሁዋዌ የሃገሪቱን ደህንነት ስጋት ላይ ይጥላል በሚል ኩባንያው ላይ ጫና እያሳደረ ነው። የአሜሪካ ግምጃ ቤት ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ ኩባንያውን በጥቁር መዝገብ አስፍሮት እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይም ለኩባንያው ከአሜሪካም ሆነ ከሌሎች ሃገራት የሚጓጓዙ የቴክኖሎጅ ቁሳቁሶች ላይ ገደብ መጣል የሚያስችል ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑንም ገልጻለች። የአሜሪካ ግምጃ ቤት አሁን ባለው ህግ የአሜሪካ የቴክኖሎጅ ምርቶች ከፍ ያለውን ዋጋ ከያዙ ወደ ቻይና የሚላኩ የሌሎች ሃገራትን የቴክኖሎጅ ምርቶች የማገድ ወይም የማስገቢያ ፈቃድ መጠየቅ ይችላል። አሜሪካ ባለፈው ዓመት በደህንነት ስጋት ምክንያት ለሁዋዌ እና 68 ተዛማጅ ኩባንያዎች የቴክኖሎጂና ሌሎች መሳሪያዎችን እንዳይሸጡ ገደብ መጣሏ የሚታወስ ነው። አሜሪካ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያዎችን አገልግሎት መጠቀም ሊያስከትል የሚችለውን የደህንነት ስጋት የሚያሳይ ማስረጃ በማቅረብ በተለይም ምዕራባውያን አጋሮቿ እንዳይጠቀሙ እየወተወተች ትገኛለች። ምንጭ፦ አልጀዚራ \n \nጥያቄ: የአሜሪካ ግምጃ ቤት ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ በጥቁር መዝገብ የያዘው የቻይና ኩባንያ ስሙ ማን ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ ሁዋዌ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nጎፋ የጎፋ ብሔረሰብ ቋንቋ ‹ጎፍኛ› ሲሆን፣ ቋንቋው ከማዕከላዊ ኦማዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ይመደባል። በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 363ሺ9 ነው፡፡ የጎፋ ብሔረሰብ በጋሞጎፋ ዞን ውስጥ ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ ሲሆን፣ ብሔረሰቡ በዋናነነት በጎፋ ዙሪያ፣ ዛላ፣ ዑባ፣ ደብረፀሐይ እና መሎካዛ በሚባሉ ወረዳዎች ይገኛል፡፡ የብሔረሰቡ ዋና የሀብት መሠረት ጥምር ግብርና ሲሆን፤ የገቢ ምንጭ በሚያስገኙ ምርቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ የጎፋ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ነባር ባህላዊ አስተዳደር አለው፡፡ ጥንት በጎፋ ግዛት ክልል ሥር የነበሩ አካባቢዎች በሰባት የካዎ (ነጉሥ) ግዛቶች ተከፋፍለው የተደራደሩ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ከአዎ የአስተዳደር ማዕከል ቤተ-መንግሥት(ጋዶ) ነበረው፡፡ ማዕከላዊ አስተዳደሩ የተለየ ሥልጣንና የሥራ ድርሻ ያላቸውን አስፈፃሚ አካላትን የያዘ ነበር፡፡ ካዎ (ንጉሥ)- የባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮና ከፍተኛ የሥልጣን አካል ሲሆን፤ ከእርሱ ቀጥሎ የሚገኙትን የሥልጣን አካላትንና አማካሪዎችን የመሾምና የመሻር ሥልጣን ነበረው። ጠንከር ያለ ውሳኔን የሚሹ ጉዳዮች የመጨረሻ ብይን የሚያገኙትም በካዎ ነበር፡፡ ብሔረሰቡ ጋብቻ የማፈጸመው የጎሣ አቻነትን፣ የሀብት ደረጃ በማስተያየትና የሥጋ ዝምድና አለመኖርን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ወንዶች ከ17-25፤ ሴቶች ደግሞ ከ14-19 ባለው የዕድሜ ክልል ጋብቻ ይፈጽማሉ፡፡ ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ይገረዛሉ፡፡ ጋብቻ ከመፈጸማቸው በፊት ሴቷ ጥጥ ፈትላ አልባሳት ስታዘጋጅ ወንድም በፊናው የመኖሪያ ቤትና የራሱን የእርሻ ቦታ ያደራጃል፡፡ በብሔረሰቡ የተለያዩ የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች አሉት፡፡ በቤተሰብ ስምምነት፣ በጠለፋ የሚፈጸሙ ጋብቻዎች ኣሉት። በተጋቢዎችም ሆነ በቤተሰብ መካከል ያለመግባባት ሲከሰት ወይም የአግቢው ገቢ ሀብት አቅም ውሱንነት ሲከሰት ተጋቢዎቹ ሳይተዋወቁ የወንዱ አባት ሽማግሌ ይዞ የልጅቷን ቤተሰብ ከ1-2 ቀን ደጅ በመጥናት የሚፈጸም የሽምግልና ጋብቻም ኣለው። የምትክ ጋብቻ የሚባለው ደግሞ፤ ሚስት ከሞተች እህቷ ወይም የቅርብ ዘመዷ በምትክ ሚስትነት የምትሰጥበት የጋብቻ ኣይነት ነው፡፡ ወዶ ገብ ጋብቻ ደሞ ሌላው በብሔረሰቡ የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ ይኸውም፤ ሳታገባ የቆየች ሴት የራሷን ንብረት በመያዝ ወደ ወንዱ ቤት በፈቃዷ ሄዳ በመግባት የሚፈጸም የጋብቻ ዓይነት ነው፡፡ በብሔረሰቡ በበዓላት ቀናት ከሚዘጋጁት ምግቦች መካከል ሸንዴራ ይገኝበታል፡፡ ከበቆሎና ከገብስ ዱቄት የሚሠራ ሆኖ ቅመማቅመምና ቅቤ በማጣፈጫነት ገብቶበት የሚበላ ጥሩ ምግባቸው ነው፡፡ ቡላ በአይብ ጎመንና ቅቤ ገብቶበት የማሠራው ባጭራ የተባለው ምግባቸውና ቅንጬ በበዓላት ቀን ከሚያዘጋጇቸው ተጠቃሾች ናቸው፡፡ \n \nጥያቄ: በጎፋ ብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደሩ ቁንጮ፣ ከእርሱ ቀጥሎ የሚገኙትን ባለሥልጣናትና አማካሪዎችን የመሾምና የመሻር ሥልጣን ያለው ማነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ ካዎ (ንጉሥ) ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nእንደ ፕላቶ ዘገባ፣ የሶቅራጠስ እናት ፌናርት የተሰኘች አዋላጅ ነበረች። ሶቅራጠስ እናቱ ሴቶች ልጅ እንዲወልዱ እንደምትረዳ ሁሉ እርሱ ደግሞ ሰዎች አዳዲስ አሳቦችን እንዲወልዱ ለመርዳት እንደሚሞክር መናገሩ ይጠቀሳል። የሶቅራጠስ አባት ድንጋይ አናጢ የነበረው ሶፍሮኒስከስ እንደነበር ይጠቀሳል። ሶቅራጠስ በዘመኑ ድሃ የነበረ ሲሆን ለዚህ ምክንያቱ ከገንዘብ ይልቅ እውቀት ይበልጣል ብሎ ስለሚያምን ነበር። ሶቅራጠስ ስራ እንደማይሰራና በፍልስፍና ሃሳብና ክርክር ጊዜውን እንደሚያሳልፍ ፕላቶ ዘግቦት ይገኛል። ዛንቲፕ የተሰኘች ከርሱ በዕድሜ በጣም የምታንስ ሴትን አግብቶ ሶስት ልጆች እንደነበሩት ፕላቶ ጽፏል። ሶቅራጠስ 70 ዓመት በሞላው ጊዜ የአቴና መንግስት እንዲያዝና ለፍርድ እንዲቀርብ አደረገ። በወቅቱ ሁለት ክሶች ሲቀርቡበት አንደኛው \"በትምህርትህ ወጣቱን አበላሽተሃል\" የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ \"ለግሪክ ጣዖታት አልተገዛህም\" የሚል ነበር። እንደ ፕላቶ ዘገባ ግን ሶቅራጠስ የግሪክ ጣኦታት አምላኪ ነበር። በአንድ አንድ ተመራማርወች ዘንድ የአቴንስ መንግስት ያቀረባቸው ክሶች በውሸት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። የሆኖ ሆኖ፣ ክሪቶ የተሰኘው የፈላስፋው ጓደኛ ለጠባቂወቹ ጉቦ በመስጠት እንዲያመልጥ ሁኔታውን አመቻችቶ ነበር። ሶቅራጠስ ግን እምቢ በማለት ቀረ እንጂ አላመለጠም። ሶቅራጠስ ለፍርድ በቀረበ ጊዜ ሰፊ የሆነ የመከላከያ ክርክር በማቅረብ የአቴናን መንግስት ክስ ውድቅ ለማደርግ ሞክሯል። ከዚህ በኋላ ዳኞቹ ምን አይነት ቅጣት እንዲበይኑበት እንደሚፈልግ ሲጠይቁት፣ ለአቴና ህብረተሰብ ካበረከተው ጥሩ ተግባራቱ አንጻር በቀሪው ዘመኑ ሁሉ ነጻ እራት እንዲያመጡለት ተናገረ። ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ወይ በቅጣት እንዲለቀቅ ወይንም ደግሞ እንዲገደል የእጅ ምርጫ አደረገ። ውጤቱም ሶቅራጠስ እንዲገደል የሚል ሆነ። ይሁንና ሶቅራጠስ ሞትን አይፈራም ነበር። ሞቱን ለማስቀረት ይቅርታም ሆነ ሌላ ማባበያ አላቀረበም። በርሱ ሥነ ምግባር መሰረት ላመነበት ነገር እስከመጨረሻ መቆሙ ሰናይ ድርጊት ነበር። ስለሆነም ሄምሎክ የተሰኘ መርዝ ጠጥቶ እንዲሞት ስለታዘዘ፣ መርዙን በመጠጣት አለፈ። \n \nጥያቄ: ሶቅራጥስ ምን የሚባል መርዝ ጠጥቶ እንዲሞት ተፈረደበት?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ ሄምሎክ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nበ1240 አካባቢ በግብጽ አገር ቅብጡ አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ፍትሐ ነገሥት በአረብኛ ጻፉ። እብን አል-አሣል ሕጎቹን የወሰዱት በከፊል ከሃዋርያት ጽህፈቶችና ከሕገ ሙሴ፤ በከፊልም ከድሮ ቢዛንታይን ነገስታት ሕጎች ነበር። መጽሐፉ በግዕዝ ተተርጉሞ ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ወቅት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በ1450 አከባቢ እንደነበር የሚል ታሪካዊ መዝገብ አለ። ቢሆንም መጀመርያ እንደ ሕገ ምንግሥት መጠቀሙን የተመዘገበው በዓፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን (ከ1555 ጀምሮ) ነው። ፍትሐ ነገስት እስከ 1923 ዓ.ም. የብሄሩን ዋና ሕግ ሆኖ ቆየ። በ1904 ዓ.ም. ዐጼ 2 ምኒልክ የዘመናዊ ሕገ መንግሥት ፅንሰ ሀሳብ ተረድተው በጸሀፊው መምሬ ብስራት አንድ ሕገ መንግሥት የሚመስል ሰነድ ታተመ፤ ይህ ግን በውነት ሕገ መንግሥት አይባልም። «በምኒሊክ ስለተቋቋሙት ሚኒስቴሮች በምሳሌ የቀረበ ጽሑፍ» በምሳሌና በትርጓሜ የእያንዳንዱን ሚኒስቴር ሥራ እንደ ሰውነት አካላት አስመሰለ። ለምሳሌ፦ ኢትዮጵያ መጀመርያ ዘመናዊ ሕገ መንግሥት የተቀበለችው በ1923 አመተ ምኅረት በአጼ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የታወጀ ሲሆን የሕግ አማካሪ ቤቶች በሁለት ያስከፈለ ነው። ይህ የመንግሥታቸው ዋና መሠረት ሆኖ እስከ 1948 አ.ም. አገለገለ፤ በዚያ አመት ተሻሽሎ በወጣ ሕገ መንግሥት ሕዝቦች በመንግሥት ሥራ የሚጫወቱት ሚና እንደገና ተስፋፋ። ይህ ብቻ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ሆኖ እስከ 1967 አ.ም. ቆየ፤ የዛኔ በደርግ (በሕገ መንግስት እራሱ ባልሆነ ሂደት) ተሰረዘ። \n \nጥያቄ: በግብጽ ሀገር አቡል ፋዳዒል እብን አል-አሣል ያዘጋጀው ፍትሐ ነገሥት በምን ቋንቋ ተጻፈ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ በአረብኛ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nአቡነ ቴዎፍሎስ አቡነ ቴዌፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ጎጃም በሚገኝው በዝነኛው ደብረ ኤሊያስ አካባቢ ከአባታቸው ከአቶ ወልደ ማርያም ውቤ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ዘርትሁን አደላሁ ሚያዝያ ፲፮ ቀን ፲፱፻፪ ዓ/ም ተወለዱ። ሲወለዱም የተሰጣቸው ስም መልእክቱ ወልደ ማርያም ነበር። በልጅነታቸው ንባብ እና ዜማን በመምህር መሪ ጌታ ረዳኸኝ እና ግራ ጌታ ሣህሉ እዚያው የተወለዱበት አካባቢ ተምረዋል። ኋላ የቅኔ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ዝንባሌ ስላደረባቸው እዚያው ደብረ ኤሊያስ ደብር መምህር ገብረ ሥላሴ በሚባሉ ሊቅ ሥር መማር ጀመሩ። በ፲፱፻፻፳ ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ መጥተው ፍትሐ ነገሥትና አዲስ ኪዳንን በመምህር ተክሌ (ነቡረ ዕድ በኋላ ቢትወደድ አቡነ ዮሐንስ) በመባል የሚታወቁት መሪነት ሲከታተሉ ቆይተዋል። በዚህ ጊዜ ውስጥ የኃይማኖት ችግሮችን ለማወቅ ይፈልጉ እንደነበርና ሰፋ ያለ ዕውቀት እንደነበራቸው ይነገራል። በተጨማሪ የኃይማኖት ችግሮችን የሚመለከቱ መጻሕፍትን ሳይታክቱና ሳይሰለቹ ያነቡም ነበር። መልእክቱ ወልደ ማርያም በ፲፱፻፴ ዓ/ም ይህን ዓለም በቃኝ ብለው ደብረ ሊባኖስ ገዳም መንኩሰው ገቡ። ከጠላት ወረራ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቀሳውስቱ በዘመናዊ የኃይማኖት ትምህርት እንዲሠለጥኑ በነበራቸው ሀሳብ መሠረት ፳ የሚሆኑ ሊቃውንት መርጠው በቤተ መንግሥቱ አካባቢ እንዲሰለጥኑ አድርገዋል። ከነኚህም አንዱ አባ መልእክቱ ወልደ ማርያም ናቸው። ቀደም ብሎ በኢትዮጵያና በግብጽ በተደረገው ስምምነት መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊያን ጳጳሶች ሲሾሙ ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ ወልደ ማርያም ለሹመት ከተመረጡት አምስት አባቶች አንዱ ሲሆኑ ወደግብጽ ተጉዘው በእስክንድርያው ፓትርያርክ ዳግማዊ አቡነ ዮሳብ እጅ በካይሮ በትረ ካና ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን እሑድ ሐምሌ ፲፰ ቀን ፲፱፻፵ ዓ/ም ሊቀ ሥልጣናት መልእክቱ “ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ” ተብለው የሐረርጌ ጳጳስ ሆኑ። \n \nጥያቄ: አቡነ ቴዎፍሎስ የሐረርጌ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት የት ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ በካይሮ በትረ ካና ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nአሜሪካ ለሁዋዌ ተጨማሪ ሽያጮችን ልታግድ መሆኑን አስታወቀች። አሜሪካ የምታመርታቸውን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራት የተመረቱ የቴሌኮም ምርቶችን ለግዙፉ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያ እንዳይሸጡ ለማገድ ስለመዘጋጀቷም ነው የገለጸችው። የትራምፕ አስተዳደር ሁዋዌ የሃገሪቱን ደህንነት ስጋት ላይ ይጥላል በሚል ኩባንያው ላይ ጫና እያሳደረ ነው። የአሜሪካ ግምጃ ቤት ባለፈው አመት ሰኔ ወር ላይ ኩባንያውን በጥቁር መዝገብ አስፍሮት እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይም ለኩባንያው ከአሜሪካም ሆነ ከሌሎች ሃገራት የሚጓጓዙ የቴክኖሎጅ ቁሳቁሶች ላይ ገደብ መጣል የሚያስችል ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑንም ገልጻለች። የአሜሪካ ግምጃ ቤት አሁን ባለው ህግ የአሜሪካ የቴክኖሎጅ ምርቶች ከፍ ያለውን ዋጋ ከያዙ ወደ ቻይና የሚላኩ የሌሎች ሃገራትን የቴክኖሎጅ ምርቶች የማገድ ወይም የማስገቢያ ፈቃድ መጠየቅ ይችላል። አሜሪካ ባለፈው ዓመት በደህንነት ስጋት ምክንያት ለሁዋዌ እና 68 ተዛማጅ ኩባንያዎች የቴክኖሎጂና ሌሎች መሳሪያዎችን እንዳይሸጡ ገደብ መጣሏ የሚታወስ ነው። አሜሪካ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያዎችን አገልግሎት መጠቀም ሊያስከትል የሚችለውን የደህንነት ስጋት የሚያሳይ ማስረጃ በማቅረብ በተለይም ምዕራባውያን አጋሮቿ እንዳይጠቀሙ እየወተወተች ትገኛለች። ምንጭ፦ አልጀዚራ \n \nጥያቄ: አሜሪካ የቻይና የቴክኖሎጅ ኩባንያዎች ላይ እገዳ የጣለችው በምን ምክንያት ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ የሃገሪቱን ደህንነት ስጋት ላይ ይጥላል ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nቱርክ በዊኪፒዲያ ላይ ላለፉት ሶስት ዓመታት ጥላው የነበረውን እገዳ በማንሳት ተጠቃሚዎች ድረ ገፁን ማግኘት እንዲችሉ ፈቀደች። የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት እገዳው የመናገር መብትን ይጥሳል ሲል እግዱ እንዲነሳ ውሳኔ አሳልፏል። ዊኪፒዲያ በፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር 2017 የቱርክን መንግስት የሚተች ፅሁፍ ለማንሳት ፈቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ የቱርክ መንግስት እገዳ ማሳላፉ ይታወሳል። በወቅቱ በዊኪፒዲያ ላይ የሰፈረው ፅሁፍ የቱርክ መንግስት ከአይ ኤስ እና አል ቃይዳ ጋር ትብብር አለው የሚል መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። ይህንን ተከትሎም እገዳው ላለፉት 991 ቀናት ተግባራዊ ሆኖ መቆየቱን የኢንተርኔት ክትትል ተቋም የሆነው ኔትብሎክስ አስታውቋል። እገዳው በሂደት ቀስ በቀስ የሚነሳ በመሆኑ እና የተወሰኑ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ዊኪፒዲያን ለመመለስ እየሰሩ በመሆኑ በቱርክ የሚገኙ ሁሉም ተጠቃሚዎች ድረ ገፁን ማግኘት አይችሉም ተብሏል፡፡ ዊኪፒዲያ በበርካታ የዓለም ሀገራት ሳንሱር የሚደረግ ሲሆን በቻይና አሁንም ታግዶ ይገኛል። \n \nጥያቄ: ዊኪፒዲያ በቱርክ ለስንተ ቀናት ታገደ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ 991 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nፐርል በክ ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው። በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ \"The Nation\"፣ \"The Chinese Recorder\"፣ \"Asia\" እና \"The Atlantic Monthly\" በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል። በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል። \n \nጥያቄ: የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው በ1935 የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን የበቃው ማን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ሪቻርድ ዋልሽ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nቀጭኔ ከዝሆን በስተቀር ማንኛውም ሌላ እንስሳ ሊደርስ በማይችልበት ከፍታ ላይ የሚገኙ ረዣዥም ቀንበጠቦችን ለመብላት የሚያስችል አስደናቂ አፈጣጠር አላት። ልዩ የሆነ የመቆንጠጥ ችሎታ ያለው የላይኛው ከንፈሯና እንደተፈገለው የሚተጣጠፍ ችሎታ ያለው ምላሷ ሹል በሆኑ እሾሆች የታጠሩ ቅጠሎችን ለመቀንጠብ ያስችሏታል። ቀጭኔዎች በቀን እስከ 34 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕፅዋት መመገብ ይችላሉ። የተለያዩ ዕፅዋትን የሚበሉ ቢሆኑም ይበልጥ የሚመርጡት በአፍሪካ ሜዳዎች የሚገኙትን እሾሃማ ግራሮች ነው። አንድ ወንድ ቀጭኔ ምግብ ለመፈለግ ምላሱን እስከ 42 ሳንቲ ሜትር መዘርጋት ይችላል። የቀጭኔ አንገት በጣም አስደናቂ የሆነ የመተጣጠፍ ችሎታ አለው። ይህም ላይኛዎቹን የዛፍ ቅርንጫፎች ለመቀንጠብ በምታደርገው እንቅስቃሴ ረዥሙን ራሷን እንደ ልቧ ለማዘንበልና ለማዟዟር ያስችላታል። ለቀጭኔ ወደ ላይ መንጠራራት በጣም ቀላል ነገር ሲሆን ተጎንብሶ ውኃ መጠጣት ግን ይከብዳታል። ወደ ውኃ ጉድጓድ በምትቀርብበት ጊዜ የፊት እግሮቿን ቀስ በቀስ ከፍታ ካራራቀቻቸው በኋላ ወደ ውኃው ለመድረስ እንድትችል ሁለት ጉልበቶቿን አጠፍ ታደርጋለች። ቀጭኔዋ እንዲህ ባለው አመቺ ባልሆነ ሁኔታ እያለች ረዥም አንገቷን እስከ መጨረሻ ትዘረጋለች። ደግነቱ ግን ከምትመገባቸው ቅጠላ ቅጠሎች በቂ እርጥበት ስለምታገኝ ቶሎ ቶሎ መጠጣት አያስፈልጋትም። የቀጭኔ አንገትና ትከሻ የቅጠል ቅርፅ ባላቸውና ቀጫጭን በሆኑ ነጭ መስመሮች ያጌጠ ነው። ቀለማቸው የተለያየ ሲሆን ከወርቃማ ዳለቻ አንስቶ እስከ ቡናማ እንዲያውም ጠቆር እስካለ ቀለም ይደርሳል። የቀጭኔ ዕድሜ እየገፋ በሄደ መጠን ቀለሟም እየጠቆረ ይሄዳል። ቀጭኔዎች ከ2 እስከ 50 የሚደርሱ አባላት ባሉት መንጋዎች ተደራጅተው አንድ ላይ የሚኖሩ ማኅበራዊ ፍጥረታት ናቸው። አንዲት ነፍሰ ጡር ቀጭኔ ልጅዋን ከ420 እስከ 468 ለሚደርሱ እርግዝና ቀናት ከተሸከመች በኋላ ሁለት ሜትር ቁመት ያለው ግልገል ትወልዳለች። ግልገሏ በምትወለድበት ጊዜ ራስዋን ታስቀድምና ከሁለት ሜትር ከፍታ ላይ ወደ መሬት ትወረወራለች። ይሁን እንጂ በ15 ደቂቃ ውስጥ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባት እየተውተረተረች ትነሳና ጡት ለመጥባት ዝግጁ ትሆናለች። ከሁለት ወይም ከሦስት ሳምንት በኋላ በደመ ነፍስ ተመርታ የግራር ቀንበጦችን መለቃቀም ስለምትጀምር ብዙም ሳትቆይ ረዥም እርምጃ ያላትን እናትዋን ተከትላ ለመሄድ የሚያስችል ጉልበት ታገኛለች። አንዲት የቀጭኔ ግልገል በጣም ውብ መልክ ሲኖራት የወላጆችዋ አነስተኛ ግልባጭ ነች። ቁመቷ ከቀጭኔ ርዝመት ጋር ሲወዳደር አጭር ብትሆንም ከብዙ ሰዎች ቁመት ግን ትበልጣለች። በእናቷ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበቃ ተማምና አላንዳች መሸበር አካባቢዋን የምትማትረው ግልገል ላያት ሁሉ ልዩ መስህብ አላት። ግልገል ቀጭኔዎች በተወለዱበት ወራት በግልገል መዋያ ተሰባስበው ሙሉውን ቀን ዕረፍት በማድረግ፣ በመጫወትና በአካባቢያቸው የሚሆነውን ነገር በመመልከት ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። የቀጭኔ ግልገል ለማመን በሚያዳግት ፍጥነት ያድ⁠ጋል። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ሜትር የሚያክል ቁመት ሲጨምር በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በእጥፍ ያድጋል። በአንድ ሳምንት ብቻ 23 ሳንቲ ሜትር ያህል ሊያድግ ይችላል! እናትዬው ለልጅዋ ከፍተኛ ጥበቃ የምታደርግ ሲሆን ልጅዋ የተወሰነ ርቀት እንድትዘዋወር ብትፈቅድላትም ሩቅ የማየት ችሎታ ስላላት በዓይኗ ትከታተላታለች። ቀጭኔ ግዙፍ አካል፣ ከፍተኛ ፍጥነት፣ ቅልጥፍናና የማየት ችሎታ ስላላት ከአንበሳ በቀር የሚያጠቃት ጠላት የለም። ቢሆንም ይህችን የምታምር ፍጥረት የሰውን ያህል በብዛት አድኖ የገደለ የለም። ቀጭኔ በሚያምር ቆዳዋ፣ በሚጣፍጥ ሥጋዋና አንዳንዶች ምትሐታዊ ኃይል አለው በሚሉት ረዥምና ጥቁር ጭራዋ ምክንያት እጅግ ተፈላጊ ስለሆነች በአሁኑ ጊዜ የዚህች ሰላማዊ ፍጡር የወደፊት ሕልውና ስጋት ላይ ወድቋል። በአንድ ወቅት በብዙ የአፍሪካ አካባቢዎች እንደ ልብ ትታይ የነበረችው ቀጭኔ በአሁኑ ጊዜ የምትገኘው በቂ ጥበቃ በሚደረግላት ፓርኮች ብቻ ሆኗል። የቀጭኔ አካላዊ ቅርጽና ግዝፈት ችግሮች ማስከተሉ አይቀርም ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል። በጣም ትልቅ ቁመትና ረዥም አንገት ስላላት የተስተካከለ የደም ዝውውር እንዲኖራትና ወደ ሁሉም የአካሏ ክፍሎች ደም እንዲደርስ ማድረግ የማይቻል ነገር ሊመስል ይችላል። ለምሳሌ ያህል ቀጭኔ አንገቷን ወደ መሬት ስታጎነብስ በስበት ኃይል ምክንያት ብዙ ደም ወደ ጭንቅላቷ ፈስሶ አንጎሏን ማጥለቅለቅ ነበረበት። ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ደሟ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ልቧ ተመልሶ ራሷን እስከ መሳት ሊያደርሳት ይገባ ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ነገር አይደርስም። ለምን? የቀጭኔ የደም ዝውውር ሥርዓት በዓይነቱ ልዩ ለሆነው ለዚህች እንስሳ ቅርጽና መጠን እንዲያገለግል ሆኖ በታላቅ ጥበብ የተሠራ ነው። ልቧ ራሱ በጣም ትልቅ ሲሆን ደሙን ሦስት ሜትር ተኩል ገደማ ርቆ እስከሚገኘው እስከ አንጎላ ለመግፋት የሚያስችል አቅም አለው። በደቂቃ እስከ 170 ጊዜ የሚመታውና 7 ሳንቲ ሜትር ያህል ውፍረት ባለው ጡንቻ የተገነባው የቀጭኔ ልብ ከሰው የደም ግፊት በሦስት እጥፍ የሚበልጥ ግፊት ያመነጫል። ወደ አንጎል የሚሄደውን ደም የሚሸከመው ካሮቲድ የተባለው የደም ቧንቧና ከአንጎል ወደ ልብ የሚመለሰውን ደም የሚሸከመው ጀጉላር የተባለው የደም ቧንቧ እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ግፊት መቋቋም የሚያስችል መጠን ሊኖራቸው ይገባል። በእርግጥም እነዚህ የደም ቧንቧዎች ከ2.5 ሳንቲ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸው ከመሆኑም በላይ ጠንካራና የመለጠጥ ችሎታ ባላቸው ሕዋሳት የተገነቡ በመሆናቸው ከፍተኛ ጥንካሬና የመለመጥ ችሎታ አላቸው። ቀጭኔ ከጭንቅላቷ ጎንበስ በምትልበት ጊዜ ወደ አንጎሏ የሚሄደውን የደም ፍሰት የሚቆጣጠሩ ልዩ መቆጣጠሪያዎች አሏት። አንጎልና አንገት በሚገናኙበት ቦታ ላይ ትልቁ ካሮቲድ የደም ቧንቧ ሬቴ ሚራቢሌ ተብሎ ከሚጠራ አስደናቂ የሆነ መረብ መሰል አካል ይገናኛል። በከፍተኛ ኃይል ተገፍትሮ የመጣው ደም እዚህ ጋር ሲደርስ በጣም በርካታ ወደሆኑ ትናንሽ የደም ሥሮች እንዲገባ ስለሚደረግ የደሙ ግፊት ተስተካክሎ በአንጎል ላይ ጉዳት የማያስከትል ይሆናል። ቀጭኔዋ ራስዋን ጎንበስ በምታደርግበት ጊዜ ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው መረብ ይለጠጣል፤ ራሷን ቀና በምታደርግበት ጊዜ ደግሞ ይኮማተራል። ይህም የስበት ኃይል የሚያሳድረው ተጽዕኖ ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና የደም ግፊቷ በእጅጉ ቀንሶ ራሷን የምትስትበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳታል። የሳይንስ ሊቃውንት በጣም አስደናቂ ርዝመት ያለው የቀጭኔ አንገት ያሉት አከርካሪዎች ቁጥር ከአይጥ ወይም ከብዙዎቹ አጥቢ እንስሳ ጋር እኩል መሆኑን ሲያውቁ በጣም ተደንቀዋል! ይሁን እንጂ የቀጭኔ አከርካሪዎች በጣም ረዣዥሞችና እርስ በርሳቸው ልዩ በሆነ ሁኔታ የተሰካኩ በመሆናቸው እንደ ልብ ሊተጣጠፉ ይችላሉ። ቀጭኔ አንገቷን መጠምዘዝና ማጠፍ ስለምትችል ሁሉንም የአካሏን ክፍሎች ለመላስም ሆነ ረዣዥም የዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ለመድረስ ትችላለች። \n \nጥያቄ: የቀጭኔ ግልገል በምትወለድበት ጊዜ የምታስቀድመው የሰውነት ክፍል የቱን ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ ራስዋን ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nአሸናፊ ከበደ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አዲስ አበባ ግንቦት ፰ ቀን ፲፱፻፴ ዓ/ም ተወለዱ። አባታቸው ግራዝማች ከበደ አድነው ሲሆኑ ክልጅነታቸው ጀምሮ የሙዚቃ ስሜትንና ፍቅር ያሳደሩባቸው እናታቸው ወይዘሮ ፋንታዬ ነከሬ ነበሩ። አያታቸው ሊቀመኳስ አድነው ጎሹ ደግሞ የአድዋ አርበኛ እናየንግሥት ዘውዲቱም ታማኝ አማካሪ እንደነበሩ ይነገራል። የሙዚቃ ፍቅርን ገና በልጅነታቸው ያሳደሩባቸው እናታቸው ሲሆኑ ታዳጊው አሸናፊ ገና የዘጠኝ ዓመት ልጅ ሳሉ እኒህ የሚያፈቅሯቸውና ዕድሜ ልካቸውን በኀዘን የሚስታውሷቸው እናታቸው ሞተውባቸዋል። መሠረታዊ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ኮከበ ጽባሕ) ካጠናቀቁ በኋላ በሐረር የመምህራን ማሠልጠኛ ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኒው ዮርክ ክፍለ-ሀገር ከሚገኘው የሮቼስተር ዩኒቨርሲቲ፣ “ኢስትማን የሙዚቃ ትምህርት ቤት” በ፲፱፻፶፬ ዓ/ም በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፤ የያሬድ ሙዚቃ ትምሕርት ቤትን መሠረቱ። የዚሁ ትምህርት ቤትም የመጀመሪያው ዳይሬክቶር ከመሆናቸውም ባሻገር በአዲስ አበባው የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር (ወ.ወ.ክ.ማ Y.M.C.A.)፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት መርሓ-ዕውራን ትምህርት ቤት እና በመሳሰሉ የወጣቶች ማኅበራት እየተገኙ የሙዚቃ ትምህርት ይሰጡ ነበር። \n \nጥያቄ: ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ የሙዚቃ ስሜትንና ፍቅር ያሳደሩባቸው ማናቸው?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ እናታቸው ወይዘሮ ፋንታዬ ነከሬ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nኒሺ ፍሬደሪክ ዊልሄልም ኒትሸ (ኦክቶበር 15, 1844 - ኦገስት 25, 1900) ጀርመናዊ ጻህፊና ፈላስፋ ሲሆን አለምን ይቀይራሉ ብሎ ያመነባቸውን ብዙ መጻህፍት በመድረስ ይታወቃል። እርግጥ ኒሺ፣ በነበረበትም ሆነ በኋላ ዘመኑ ብዙ ተቃዋሚወች ቢነሱበትም በዚያው ልክ ብዙ ሰወች ስራወቹን እንደ ታላቅ የፍልስፍና እና ስነ ጽሁፍ ስራ ይወስዷቸዋል። ኒትሸ አብዛኛው ጽሁፉ የሚያተኩረው ሰወች እንዴት ሊኖሩ ይገባቸዋል? በሚለው ጥያቄ ነው። በዚህ ምክንያት እሱ ይኖርበት የነበረውን ዘመን የጀርመን ሥነ ምግባር (ኤቲክስ) በመንቀፍ ብዙ ጽፎአል። ሠናይ እና እኩይ (ጥሩና መጥፎ) ተብለው ተለይተው ይሰራባቸው የነበሩትን የጊዜውን ሥነ ምግባር ዋጋወች በመተቸት ሰወች አዲስ ሥነ ምግባር ፈጥረው ለሁሉም ምግባር አዲስ የሠናይነትና እኩይነት (ጥሩ እና መጥፎ) ዋጋ እንዲሰጡ በጽሑፎቹ ብዙ ሞክሯል።በዚህ መሰረት፣ ለምሳሌ፣ በክርስቲያኖች ዘንድ የሚሰራበትን ለደካሞች ማዘንን ሠናይነት ተቃውሟል። በሱ አስተያየት ደካሞች ሲታዘንላቸው የበለጠ ይዳከማሉ የሚል ነው ምክንያቱም በሱ አስተያየት ደካሞቹ በጠንካሮቹ ላይ የበለጠ ጥገኛ በመሆን መላው ህብረተሰብ ይዳከማል የሚል ነው። በተጨማሪም፣ የሰው ልጅ የሚኖርበትን ተጨባጩን አለም መገንዘብ እና ክሁሉ በላይ ስለዚሁ ዓለም ማተኮር አለበት ብሏል። ሰማይና ሌሎች አለማትን በማጣጣል፣ የሰው ልጅ እነዚህን አይነት አለሞች የሚፈጥረው አሁን ያለበትን ተጨባጩ የውኑ አለም ችግሮች መፍታት ሲያቅተው ለመፈርጠጥ ነው በማለት የሰው ልጅ ስለዚህ ምድር ብቻ እንዲያስብ ይወተውታል። ኒሽ የሰው ልጅ እራሱን በራሱ ማሸነፍ እንዲችል አጥብቆ ያምናል። በኒሺ ፍልስፍና፣ አንድ እራሱን ያሽነፈ ሰው በጣም የተለወጠ እና የተሻለ ስለሚሆን \"ሱፐር ማን\" ወይም \"የበላይ ሰው\" እንዲባል ሰይሟል። የበላይ ሰው እንግዴህ ጠንካራና በሌሎች ሰወች \"ሠናይ\" እና \"እኩይ\" ወይም ደግሞ \"ጥሩ\" ና \"መጥፎ\" ዋጋወች የማይመራ፣ ይልቁኑ የራሱን ሥነ ምግባር የሚፈጥር ነው። \n \nጥያቄ: የኒሽ አቁዋም ምን ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ የሰው ልጅ እራሱን በራሱ ማሸነፍ እንዲችል ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nበቁርጥራጭ ብረትና ያገለገሉ ማሽኖች ንግድ የተሰማራው ሳርፌ ቢዝነስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ የግንባታ ብረታ ብረቶች ማምረቻ ፋብሪካ በዱከም ከተማ ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የሳርፌ ቢዝነስ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ክብርይስፋ ተክሌ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኩባንያው እስካሁን ቁርጥራጭ ብረቶች ከውጭ በማስመጣትና ከአገር ውስጥ በመግዛት ለብረት አቅላጮች ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ የብረት ማቅለጫው ማሽኖች ከህንድ ተገዝተው የሚመጡ ሲሆን፣ የብረት መዋቅሩ ደግሞ ከቻይና ይገዛል፡፡ የፋብሪካው ጠቅላላ የኢንቨስትመንት ወጪ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት የተናገሩት አቶ ክብርይስፋ፣ ፋብሪካው ለ300 ኢትዮጵያውያን የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡ ሳርፌ ቢዝነስ ለብረት ፋብሪካው ግንባታ የሚሆን 30,000 ካሬ ሜትር ቦታ በሊዝ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከዱከም ከተማ አስተዳደር በቅርቡ መረከቡን ገልጸው፣ ኩባንያቸው ተገቢውን የአዋጭነት ጥናት ማሠራቱን አስረድተዋል፡፡ \n \nጥያቄ: የሳርፌ ብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለምን ያህል ሰው የሥራ እድል ይፈጥራል?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ለ300 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በ84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ተገኝተዋል። በሰመዕታት መታሰቢያ ቀን የካቲት 12 ቀን በየአመቱ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፤አባት አርበኞች፤ እና የህብረተሰብ ክፍሉ በስድስት ኪሎ ታስቦ ይውላል፡፡ \n \nጥያቄ: የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ማን ይባላሉ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nክዋሜ ንክሩማህ የተወለዱት በ1909 እ.ኤ.አ. ደቡባዊ ምዕራብ ጋና (ቀደም ሲል ጎልድ ኮስት) ንክሮፉል በምትባል ከተማ ነው። ንክሩማህ በካቶሊክ ሚሽነሪ ትምህርት ቤት ይማሩበት በነበረ ወቅት ብሩህ አዕምሮ እንደነበራቸው የተመሰከረላቸው ሲሆን ገና በአሥራዎቹ እድሜ ውስጥ እያሉ ነው በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ የሆኑት። ይሁንና ያለሥልጠና የጀመሩትን ትምህርት በ1926 እ.ኤ.አ. የአክራውን አቺሞታ ኮሌጅ ተቃለቅለው የመምህርነት ምሥክር ወረቀት በማግኘት በተለያዩ የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች አስተምረዋል። በ1935 እ.ኤ.አ. ወደ አሜሪካ በማቅናትም የፔንሴልቬኒያውን ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ተቀላቅለው በኢኮኖሚክስና ሶሲዮሎጂ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን በ1939 የተቀበሉ ሲሆን በ1942ም በሥነ-መለኮት ሌላ ድግሪ ከዚሁ ዪኒቨርሰቲ አግኝተዋል። በ1942 እና በ1943ም የማስተርስ ድግሪያቸውን ከፔንሴልቬኒያ ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ትምህርትና በፍልስፍና ሠርተዋል። በአሜሪካ ቆይታቸውም በግራ ዘመም አሰተሳሰቦች በመማረከቸው የተነሳ በወቅቱ በሥርነቀል ለውጥ ፈላጊነታቸው ከሚታወቁ ምሁራን ጋር ቅርብ ግንኙነት መሥርተው ነበር። አፍሪካውያንን ያሰባሰበ የተማሪዎች እንቅስቃሴ መሥራችና ግንባር ቀደም ተናጋሪ እንዲሁም የአፍሪካ አገራት ነፃ እንዲወጡና የአውሮፓ ቅኝ ግዛት እንዲያበቃ ቁርጠኛ አቋም ነበራቸው። ከዚሁ ጎን ለጎንም የተባበረች አፍሪካ አስፈላጊነትን በማመን አፍሪካውያንና የአፍሪካ ዝርያ ያላቸው ሕዝቦች በአንድነት እንዲቆሙ የሚሰብከው ፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ነበሩ። በ1945 ወደ ለንደን ሕግና ኢኮኖሚክስ ለማጥናት ባመሩበት ወቅትም በማንችስተር እንግሊዝ የተካሄደውን 5ኛው የፓን አፍሪካን ጉባዔ እንዲካሄድ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል። የአፍሪካን ከቅኝ ግዛት የመውጣት እንቅስቃሴ ለማስተባበርና ቅኝ አገዛዝን ለመቃውም የተደራጀው ጉባዔ ንክሩማህ ታዋቂ የጥቁር መብት ታጋዮችና የፀረ-ቅኝ ግዛት ንቅናቄ መሪዎች ጋር እንዲገናኙ ዕድል የሰጣቸው ሲሆን በ1946ም ጥናታቸውን ትተው በ5ኛው ጉባኤ የተቋቋመው የምዕራብ አፍሪካ ብሔራዊ ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊና የምዕራብ አፍሪካ ተማሪዎች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል። \n \nጥያቄ: የተክዋሜ ንክሩማህ መቼና የት ተወለደ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ በ1909 እ.ኤ.አ. ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nየ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፳ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በብራዚል ይካሄዳል። ብራዚል ይህን ውድድር ስታዘጋጅ ይሄ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው። ፊፋ የ2014 እ.ኤ.አ. ውድድር በደቡብ አሜሪካ እንደሚካሄድ በ2007 እ.ኤ.አ. ካወጀ በኋላ ብራዚል ያለማንም ተቀናቃኝ አዘጋጅ አገር ሆና ተመርጣለች። የ፴፩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች ከጁን 2011 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮችን በማለፍ ከብራዚል ጋር በመጨረሻው ውድድር ላይ ለመሳተፍ በቅተዋል። በጠቅላላው ፷፬ ጨዋታዎች በ፲፪ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አዲስ የተገነቡ ወይም የተሻሻሉ ስታዲየሞች ይከናወናሉ። በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎል ላይን ቴክኖሎጂ በጥቅም ላይ ውሏል። በ1930 እ.ኤ.አ. ከተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጀምሮ ሁሉም የዓለም ዋንጫ ሻምፕዮን አገራት (ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሣይ፣ ጀርመን፣ ኢጣልያ፣ እስፓንያ እና ኡራጓይ) በዚህ ውድድር ውስጥ ተሳታፊ ናቸው። ከዚህ በፊት በደቡብ አሜሪካ የተዘጋጁትን ዋንጫዎች እንዳለ የወሰዱት የደቡብ አሜሪካ ቡድኖች ናቸው። ፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $576 ሚሊዮን ነው። ይህም ከ2010 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የ፴፯ ከመቶ ዕድገት አለው። ከዚህ ውስጥ $70 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1.5 ሚሊዮን የተረከበ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ እንደሚመለከተው ተከፋፍሏል፦ $8 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በምድብ ደረጃ የወደቀ ቡድን (፲፮ ቡድኖች) $9 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በየ፲፮ ዙር የወደቀ ቡድን (፰ ቡድኖች) $14 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በሩብ ፍፃሜ የወደቀ ቡድን (፬ ቡድኖች) $20 ሚሊዮን - በአራተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን $22 ሚሊዮን - በሶስተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን $25 ሚሊዮን - በሁለተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን $35 ሚሊዮን - ለአሸናፊው ቡድን በአስራ ሁለት ከተማዎች የሚገኙ አስራ ሁለት ስታዲየሞች ለውድድሩ ተዘጋጅተዋል። ሰባቱ አዲስ የተገነቡ ሲሆን አምስቱ ደግሞ የተሻሻሉ ስታዲየሞች ናቸው። \n \nጥያቄ: ፳ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ በየት ሀገር ይዘጋጃል?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ በብራዚል ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nሚያዝያ ፴ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵ ኛው ዕለትና የወርኅ ፀደይ (በልግ) ፴፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፮ ቀናት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመን ማርቆስ ደግሞ ፻፳፭ ቀናት ይቀራሉ። ታሪካዊ ማስታወሻዎች ፲፰፻፸፬ ዓ/ም - እምባቦ በሚባል ሥፍራ የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ሠራዊት እና የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ሠራዊት ውጊያ ገጥሞ ድሉ የንጉሥ ምኒልክ ሲሆን፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተማረኩ። ፲፰፻፺ ዓ/ም - በጣልያ አበጋዙ ባቫ-በካሪስ ብዙ መቶ ሰልፈኞች በመድፍ ገደላቸው። ፲፱፻፳፭ ዓ/ም - የሕንድ አባት በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ሞሃንድራስ ካራምቻንድ ጋንዲበአገሩ የእንግሊዝን አስተዳደር በመቃወም የሃያ አንድ ቀን የ'ረሀብ አድማ' ጀመረ። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - በአውሮፓ የሁለተኛው የዓለም ጦርነትን ማክተም ምክንያት በማድረግ 'ሴቲፍ' በተባለች የአልጄሪያ ከተማ በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፻፫ አውሮፓውያን በመሞታቸው፣ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ እስከ ስድስት ሺ አልጄሪያውያን ተጨፍጭፈዋል። የዚህ አረመኔያዊ ድርጊት ሳቢያ በመላው የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ ታሪካውያን ይዘግባሉ። ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - በሩሲያኖች የተገነባው የአሰብ የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ዶክቶር ምናሴ ኃይሌ እራሳቸውን ከሥልጣናቸው አስወገዱ። ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - አቶ ለገሰ ዜናዊ አስረስ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አድዋ ላይ ተወለዱ። \n \nጥያቄ: የሰሜን አፍሪቃ የፈረንሳይን ቅኝ ገዢነት ማክተሚያ አብሳሪ እንደሆነ የሚገረው ምንድን ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ የገዢው የፈረንሳይ መንግሥት ፖሊሶች እና ወታደሮች ባካሄዱት ጨካኝ በቀላ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nአሸናፊ ከበደ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አዲስ አበባ ግንቦት ፰ ቀን ፲፱፻፴ ዓ/ም ተወለዱ። አባታቸው ግራዝማች ከበደ አድነው ሲሆኑ ክልጅነታቸው ጀምሮ የሙዚቃ ስሜትንና ፍቅር ያሳደሩባቸው እናታቸው ወይዘሮ ፋንታዬ ነከሬ ነበሩ። አያታቸው ሊቀመኳስ አድነው ጎሹ ደግሞ የአድዋ አርበኛ እናየንግሥት ዘውዲቱም ታማኝ አማካሪ እንደነበሩ ይነገራል። የሙዚቃ ፍቅርን ገና በልጅነታቸው ያሳደሩባቸው እናታቸው ሲሆኑ ታዳጊው አሸናፊ ገና የዘጠኝ ዓመት ልጅ ሳሉ እኒህ የሚያፈቅሯቸውና ዕድሜ ልካቸውን በኀዘን የሚስታውሷቸው እናታቸው ሞተውባቸዋል። መሠረታዊ ትምህርታቸውን በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እና በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ኮከበ ጽባሕ) ካጠናቀቁ በኋላ በሐረር የመምህራን ማሠልጠኛ ኮሌጅ ተመርቀዋል። ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በኒው ዮርክ ክፍለ-ሀገር ከሚገኘው የሮቼስተር ዩኒቨርሲቲ፣ “ኢስትማን የሙዚቃ ትምህርት ቤት” በ፲፱፻፶፬ ዓ/ም በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፤ የያሬድ ሙዚቃ ትምሕርት ቤትን መሠረቱ። የዚሁ ትምህርት ቤትም የመጀመሪያው ዳይሬክቶር ከመሆናቸውም ባሻገር በአዲስ አበባው የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር (ወ.ወ.ክ.ማ Y.M.C.A.)፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት መርሓ-ዕውራን ትምህርት ቤት እና በመሳሰሉ የወጣቶች ማኅበራት እየተገኙ የሙዚቃ ትምህርት ይሰጡ ነበር። \n \nጥያቄ: የአሜሪካው ሮችስተር ዩኒቨርሲቲ በየት ክፍለ-ሀገር ይገኛል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ በኒው ዮርክ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nሳዑዲ አረቢያ የሣውዲ አረቢያ ግዛት 28.7 ሚሊዬን የሚሆን ህዝብ ብዛት የያዘ ሲሆን 2ዐ ሚሊዬኑ የሣውዲ ዜጎች ሲሆኑ 8 ሚሊዬኑ የሌላ አገር ዜጎች ናቸው፡፡ ሳውዲ አረቢያ በምዕራብ ኤዥያ ከሚገኙ አገሮች በሙሉ በቆዳ ስፋቷ አንደኛ ናት፡፡ የአገሪቱ መሬት ስፋት 2,15ዐ,ዐዐዐ ኪሎ ሜትር ስኩኤር ነው፡፡ ጆርዳን እና ኢራቅ በሰሜን፣ ኩዌት ደግሞ በሰሜን ምስራቅ ኳታር ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኤምሬት በምስራቅ ኦማን በደቡብ ምስራቅ እና በስተመጨረሻ የመን በደቡብ በኩል ሣውዲ አረቢያ ያዋስኗታል፡፡ የቀይ ባህር እና የፐርዢያን ገልፍ ባህርን የያዘ ብቸኛ አገር ሲሆን የሣውዲ መሬት ለመኖር በሚያስቸግር በረሃ የተከበበ ነው፡፡ አሁን ያለው የሣውዲ ግዛት በፊት ጊዜ አራት ቦታዎችን ያጠቃለለ ነበር፡፡ ሄጃዝ፣ ናጅድ፣ አል አሻ እና አስርን የያዘነው፡፡ የሣውዲ አረቢያ ግዛት ተመሠረተው በ1932 እ.ኤ.አ. በኢብን ሣኡድ በተባለ ሰው ነው፡፡ ኢብን ሣኡድ ቀድሞ በ1894 ዓም (1902 እ.ኤ.አ.) ከብሪታንያ ግዛት ከኩወይት ዘምቶ ሪያድን ያዘ። ኢብን ሳኡድ አራት የነበሩትን የተለያዩ ግዛቶች አንድ በማድረግ ሣውዲ አረብያን ከተመሠረተ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ሀገሪቱ በዘውድ አገዛዝ እና በእስልምና ሃይማኖት መሠረት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡ እስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ ዋሀቢ እስላም የሣውዲ አረቢያ አንደኛ እምነት ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ለእስልምና እምነት ትልቅ ቦታ የሚይዙት ቅዱስ ስፍራ ተብለው መካ እና መዲና በሣውዲ ስለሚገኙ ሣውዲ አረቢያ አብዛኛው ጊዜ የተቀደሱትን ሁለት መስጊዶች የያዘው መሬት ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ትልቅ የነዳጅ አምራች ሀገራት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በተጨማሪም ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ካሉ ሀይድሮ ካርቦን ክምችት ካላቸው አገሮች በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በሀገሪቱ ባለው የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛ ክምችት ምክንያት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ እና የህዝብ ቁጥር እድገት ከያዙ ሀገራት ጋር ትመደባለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ G-2ዐ ተብለው ከሚታወቁት ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ካላቸው የሀገራት ቡድን ውስጥ ብቸኛዋ የአረቡ ዓለም አገር ናት፡፡ ይህም ቢሆን የሣውዲ ኢኮኖሚ በአብዛኛው በአንድ ቡድን የተያዘ ነው፡፡ የሣውዲ አረብያን ፈላጭ ቆራጭ በሆነ የመንግስት ስርዓት በመመራት “ነጻነት የለም” በሚል “ነጻነት ቤት” በሚል በሚታወቀው ድርጅት ተሰይማለች፡፡ ሣውዲ አረቢያ በዓለም ላይ ለጦር ሀይል ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያወጡ አገሮች ዝርዝር በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2ዐ1ዐ-2ዐ14 በስኘሪ ተብሎ በሚታወቅ ድርጅት በተደረገው ጥናት ሣውዲ አረቢያ ዓለም ላይ ከሚገኙ የጦር መሣሪያዎች በከፍተኛ ደረጃ በማስገባት ሁለተኛዋ ሀገር ናት፡፡ ሣውዲ አረቢያ በአካባቢው ካሉ ሀገሮች በዓለም ላይ ከፍተኛ አስተዋጾኦ በማድረግ ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የኦፔክ፣ ጂሲስ እና የእስላም ግሩፕ አባል ናት፡፡ \n \nጥያቄ: ሳውዲ አረብያ በደቡብ ምስራቅ የሚያዋስናት ሀገር የትኛው ነው ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ የመን ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nተክለጻድቅ መኩርያ ተክለጻድቅ መኩርያ በ፲፱፻፮ ዓ.ም. በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ አሳግርት ልዩ ስሙ ሳር አምባ በተባለ ሥፍራ ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምሕርት ሲደርስ መጀመሪያ ከአባታቸውና ቀጥሎም በአጥቢያቸው ባህላዊውን ትምሕርት እስከቅኔ ያለውን ቀስመዋል። ከዚያም አዲስ አበባ መጥተው አሊያንስ ፍራንሴዝና ተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ገብተው የጊዜውን የትምሕርት ደረጃ አጠናቀዋል። ኢጣልያ አገራችንን የወረረች ጊዜም በየካቲት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ፍጅት ተይዘው ወደ ሶማሌ ደናኔ ተግዘው ለሦስት ዓመታት ታስረዋል። ከነጻነትም መልስ አገራቸውን በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል። መጀመሪያ ተቀጥረው ያገለገሉት በትምሕርትና ሥነጥበብ ሚኒስቴር ነበር። እዚያም ሳሉ በአገራችን ሰው የተጻፈ የአገራችን ታሪክ አንድም ባለመኖሩ በቁጭትና በመቆርቆር ነበር ‘መጻፍ አለብኝ’ ብለው በደንብ ከሚታወቀው ከቅርቡ ጊዜ በቅጡ ወደማይታወቀው የሩቁ ዘመን መጻፍ የጀመሩት። የመጀመሪያውን መጽሐፍ “የኢትዮጵያ ታሪክ ከዓፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ” የሚለውን በ ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. አሳተሙ። ከጫፍ እስከ ጫፍ ጽፈው የመጨረቻውን መጽሐፍ፣ የታሪካችን መጀመሪያ የሚሆነውን “የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ-አክሱም-ዛጉዬ እስከ ዓፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት” የሚለውን በ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. አቅርበዋል። እኒህኑ መጻሕፍት ትምሕርት ሚኒስቴር ታሪክ ለማስተማሪያ በትምሕርት ቤት ተጠቅሞባቸዋል። ተክለጻድቅ ከታሪክ ውጭ የጻፏቸው “የሰው ጠባይና አብሮ የመኖር ዘዴ” እና በሚዮቶሎዢያ (አፈ ታሪክ) ላይ ያተኮረ “ከጣዖት አምልኮ እስከ ክርስትና” የሚሉም መጽሐፎች አሏቸው። ተክለጻድቅ በምድር ባቡር በዋና ጸሐፊነት፥ በቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ዋና ሥራ አስኪያጅነት፥ እንዲሁም በፈረንሳይ፥ በእስራኤል፥ በዩጎዝላቪያ በዲፕሎማሲ ሥራ በመጨረሻም የትምሕርትና የባህል ሚኒስቴር ሆነው አግልግለዋል። በፈቃዳቸው ጡረታም ከወጡ በኋላ በምርምር የታገዙ ሦስት ታላላቅ የታሪክ ሥራዎችን አቅርበዋል። ተክለጻድቅ ከረጅም የአገልግሎት ዘመን በኋላ በተወለዱ በ ሰማንያ ስድስት ዓመታቸው ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. አርፈዋል። \n \nጥያቄ: የተክለጻድቅ መኩርያ የመጨረሻው መጽሐፍ ምን ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ-አክሱም-ዛጉዬ እስከ ዓፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nየባቢሎን ግንብ በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ዘንድ፣ የባቢሎን ግንብ ሰማይን እንዲደርሱ የተባበሩት ሰው ልጆች የሠሩ ግንብ ነበር። ያ ዕቅድ እንዳይከናወንላቸው ለመከልከል፣ እግዚአብሔር እያንዳንዱ በተለየ ቋንቋ እንዲናገርበት ልሳናታቸውን አደባለቀ። መግባባት አልተቻላቸውምና ስራው ቆመ። ከዚያ በኋላ፣ ሕዝቦቹ ወደ ልዩ ልዩ መሬት ክፍሎች ሄዱ። ይህ ታሪክ ብዙ የተለያዩ ዘሮችና ቋንቋዎች መኖሩን ለመግለጽ እንደሚጠቅም ይታስባል። በትንተና የሰው ልጆች ሁሉ አንድ ኅብረተሰብ ሆነው የሠፈሩባት አገር ሰናዖር ለኤፍራጥስ ወንዝ ቅርብ ነበረች። ባቢሎን በጥንታዊ አካድኛ ምንጭ በተገኘ ባቢሉ (ባብ-ኢሉ) ማለት «የአማልክት በር» ለማለት ነው። በዕብራይስጥ ትርጉም ግን የ«ባቤል» ስም «መደባለቅ» ለማለት ለሚለው ቃል ይመስላል። ከውድቀቱ በፊት የተናገረው ቋንቋ አንዳንዴ «የአዳም ቋንቋ» መሆኑ ይባላል። በታሪክ አንዳንድ ሰው በግምት ያም ሆነ ይህ ቋንቋ መጀመርያው ቋንቋ እንደ ነበር የሚለው ክርክር አቅርቧል። ለምሳሌ ቋንቋው ዕብራይስጥ፣ አራማይስጥ፣ ግዕዝ ወይም ባስክኛ ቢሆንም እንደ ነበር በልዩ ልዩ አስተያየቶች ዘንድ ተብልዋል። \n \nጥያቄ: ሰዎች ወደ ሰማይ ለመውጣት የሰሩት ግንብ ትታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ የት ይገኛል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nነሐሴ ፳፯ ነሐሴ ፳፯ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፯ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፰ ዕለታት ይቀራሉ። ፲፮፻፶፰ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የጋየውና አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ተነሳ። ፲፯፻፵፬ ዓ/ም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን በለወጡ በሁለት መቶ ዓመታቸው፣ ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ተቀበለች። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በጠላት ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው የልጅ ኢያሱን ልጅ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን አነገሡ። አዲሱ 'ንጉሥ' ወዲያው የአርበኞች መሪ ለነበሩት ባላምባራስ አበበ አረጋይ የራስነት ማዕርግ ሰጠ። መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ/ም አረፎ አንኮበር አካባቢ በሚገኘው ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓን በተሸናፊነቷ እጇን ሰጠች። ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ነጻነትን አስከትሎ በጃዋሃርላል ኔህሩ ምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራ የሕንድ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ። ፲፱፻፺ ዓ/ም የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ የተባለውን የቀድሞ ከንቲባ ላይ ፍርዱን የወንጀለኛነት ፍርድ ፈረደበት። \n \nጥያቄ: በነሐሴ ፳፯ ቀን ፲፮፻፶፰ ዓ/ም አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ለስንት ቀን ቆየ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ ለሦስት ቀናት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nየኢትዮጵያ ሙዚቃ የመጀመሪያውን ግራማፎን ወይም የሸክላ ማጫወቻ በ፲፰፻፹፱ ዓ.ም. ሄንሪ ደ አርሊንስ እና ኒኮላስ ሊዋንቲቭ ለዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ አመጡላቸው። ይኸውም ማጫወት ብቻ እንጂ ድምጽ አይቀዳም ነበር። በኋላ ግን በዓመቱ በ፲፱፻፺ ዓ.ም. ከንግሥት ቪክቶሪያ የተላኩ የእንግሊዝ መልዕክተኞች በመጡ ጊዜ ግራማፎኑንና ድምፅ መቅጃውን ይዘውላቸው መጡ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸው በዲስክ የተቀረፁት ዓፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ ናቸው። ዛሬ በእንግሊዝ አገር በለንደን ከተማ ብሪቲሽ ኢንስቲቲውት ኦፍ ሪኮርድ ሳውንድ በተባለው ሙዚየም ውስጥ ይገኛል። በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በሸክላ የተቀረፀው የመጀመሪያው ዜማ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ስራዎች ሲሆኑ ዘመኑም በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ነበር። ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በጀርመን ቆይታቸው ወቅት የጀርመን የሙዚቃ ድርጅት ጠይቋቸው የኢትዮጵያ መዲናና ዘለሰኛ ዜማዎች በ፲፯ አይነት ስልት እየተጫወቱ ተቀርፀዋል። ኩባንያው የተሰማ እሸቴን ዜማዎች በ፲፯ ሸክላዎች የቀረፀው ሲሆን ለዜማው ባለቤት የድካም ዋጋ እንዲሆን በወቅቱ ፲፯ ሺህ የጀርመን ማርክ ከፍሏቸዋል። በዘመኑ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያም አሁንም እነዚህ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ብርቅዬ ሸክላዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ውስጥ ተሰብስበው ይገኛሉ። እነዚህ በተቋሙ እጅ ያሉት ፲፮ ሸክላዎች እያንዳንዳቸው ሁለት ዜማዎችን የያዙ ሲሆኑ ባጠቃላይ ፴፪ ዜማዎች ተቀርፀውባቸዋል። እያንዳንዱ የሸክላው ገፅ ላይ A ወይም B ተብሎ ተሰይሟል፣ የዜማው ስም ተፅፎበታል፣ የዜማው ባለቤት ተሰማ እሸቴ ስም አለ፣ ሸክላው ጀርመን ሀገር መሰራቱ እንዲሁም የሸክላው ቁጥር ተጠቅሷል። በ፲፱፻፳፭-፳፮ ዓ.ም. አካባቢ የእነ ፈረደ ጎላ፣ ንጋቷ ከልካይና ተሻለ መንግሥቱ የዜማ ሸክላዎች ብቅ እስከሚሉ ድረስ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ሸክላዎች ከ፳ ዓመታት በላይ አቅም ባላቸው ቤተሰቦች ዘንድ በብቸኝነት በግራማፎን ሲደመጡ ቆይተዋል። \n \nጥያቄ: በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በሸክላ የተቀረፀው የመጀመሪያው ሙዚቀኛ ዜማ የማን ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nአፍሪካ አፍሪካ (አፍሪቃ) ከዓለም ሁለተኛ ትልቅ አህጉር ነች። ከ869 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በዚች አህጉር የሚኖር ሲሆን በጠቅላላ 54 ሀገሮች ይገኛሉ። ከእነዚህም ሀገሮች መሀል ናይጄሪያ በህዝብ ብዛት (127 ሚሊዮን) የመጀመሪያውን ደረጃ ስትይዝ፤ ግብፅና ኢትዮጵያ በ73 ሚሊዮን እና በ72 ሚሊዮን ህዝብ በሁለተኛና በሶስተኛ ደረጃ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት የህዝብ ብዛት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ከሌሎች የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ጋር በመደማመር ድህነትን በማባባስ ደረጃ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ ጂዎግራፊና ሕዝብ ከስድስቱ ዓለማት አንዱ አፍሪካ ነው። አፍሪካ ሰፊ ነው። የዓለምም አራተኛ ክፍል ይሆናል። ከኤውሮጳ የሚለየው በሜዴቲራኒያን ባሕር ነው። ከአሜሪካም በአትላንቲክ ውቅያኖስ ይለያል። ከኒው ዮርክም ቢሆን ወይም ከቦስቶን ከአሜሪካ የሚቀርበው ክፍል ሦስት ሺህ ማይል ይሆናል። ነገር ግን በጊብሮልታር (ጂብራልታር) በኩል የሆነ እንደ ሆነ ለኤውሮጳ በጣም ቅርብ ነው። ከእስያ በኤርትራ ባሕር ይለያያል። የሆነ ሆኖ እስያ ባንድ ወገን ሱዝ ካናል በሚባለው በኩል ከአፍሪካ ጋር ተጋጥሞአል። ሙሴ ሌስፖስ መርከብ እንዲተላለፍ ብሎ አስቆፍሮ ያስከፈተው በዚህ በኩል ነው። \n \nጥያቄ: በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት አንደኛ ሀገር ማን ነች?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ ናይጄሪያ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nቢል ክሊንተን ዊልያም ጄፈርሰን «ቢል» ክሊንተን (William Jefferson Bill Clinton) (የትውልድ ስም፦ ዊልያም ጄፈርስን ብላይዝ ፬ኛ፣ እንግሊዘኛ፡ William Jefferson Blythe IV) በነሐሴ 13 ቀን፣ 1938 ዓ.ም.(1946 እ.ኤ.አ.) በሆፕ አርካንሳው የተወለዱ ሲሆን ከ1993 እስከ 2001 እ.ኤ.ኣ. ድረስ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ፕሬዝዳንት ከመሆናቸዉ በፊት አምስት ጊዜ የአርካንሳው ስቴት አስተዳዳሪ ነበሩ። \n \nጥያቄ: ቢል ክሊንተን ፕሬዝደንት ሳይሆኑ በፊት ስንቴ የአርካንሳው ግዛት አስተዳዳሪ ሆነው ሰሩ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ አምስት ጊዜ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nዚምባብዌ የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት። ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማᎆ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው። የድንጋይ ዘመን አዳኞች በቦታው ከአምስት ሺህ ዓመታት በፊት እንደነበሩ የሚጠቁም ብዙ መረጃ አለ። እነዚህ ሰዎች ከዛሬው ኮይሳን ብሔር ጋር የሚዛመዱ ሲሆን በባንቱ ብሔር ተተክተዋል። ህይወታቸውን የሚያሳዩ ሥዕሎች በዚምባብዌ ባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዋሻዎች ይገኛሉ። በብረት ዘመን የነበሩ የባንቱ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ አካባቢው ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት ፈልሰት ጀመሩ። ዛሬ የሀገሩን አራት አምስተኛ ሕዝብ ብዛት የሚሆኑት የሾና ሰዎች የዘር-ሐረጋቸው ወደ ጥንታዊው ሰዎች ያመለክታል። የታላቅ ዚምባብዌ ፍርስራሾች በመካከለኛው ዘመናት የባንቱ ስልጣኔ እንደ ነበረ ያመለክታሉ። ወደ 10ኛው ክፍለ-ዘመን አካባቢ ከሙስሊም ነጋዴዎች ጋር በኢንዲያን ባህር ላይ ንግድ ተጀመረ። ይህም ታላቅ ዚምባብዌ በ11ኛው ክፍለ-ዘመን አንድትሻሻል ረድቷል። ወርቅ ፣ የዝሆን ጥርስ እና መዳብ ይሸጡ ነበር። በ1828 ዓ.ም.፣ በደቡባዊ ዚምባብዌ የነበሩ የሾና ህዝቦች በንዴቤሌ ብሔር ተወረው ግብር ለመክፈልና ወደ ሰሜናዊ ዚምባብዌ ለመሰደድ ተገደዱ። በ1881 ዓ.ም. ብሪታኒያዊው ሴሲል ሮድስ ከንዴቤሌ ንጎሥ ሎቤንጉላ የማዕደን ማውጣት ፈቃድ አገኘ። ሴሲል ሮድስ በሊምፖፖ ወንዝና ታንጋኒካ ሐይቅ መካከል ያለውን ቦታ (ዛምቤዚያ ብሎ ሰይሞት) ተመሳሳይ ፈቃድ እንዲሰጡ አበረታቷል። ይህም ቦታው በብሪታኒያ ቅኝ-እንዲገዛ መንገድ ከፍቷል። በ1887 ዓ.ም.፣ የብሪታኒያ ደቡብ አፍሪካ ኮባኒያ የዛምቤዚያን ስም ወደ ሮዴዢያ (ለሴሲል ሮድስ) ለወጠ። ከዛም በ1891 ዓ.ም. ከዛምቤዚ በታች ያለው ቦታ 'ደቡባዊ ሮዴዢያ ተብሎ' በኩባኒያው ተሰየመ። ደቡባዊ ሮዴዢያ ወደፊት ዚምባብዌ ሆነ። ከዛምቤዚ በላይ ያለው ክልል ሰሜናዊው ሮዴዢያ ከተባለ በኋላ አሁን ዛምቢያ ነው። የንዴቤሌና ሾና ሕዝቦች የሮድስ አመራር ቢቃወሙም አልተሳካም ነበር። ከዛም ነጮች በስፍራው በብዛት ሰፈሩ። ነጮችን የሚጠቅምም የቦታ ክፍፍል ተጀመረ። የዚምባብዌ የቦታ ውዝግብ እስከዛሬ ድረስ ይቀጥላል። ደቡባዊ ሮዴዢያ እራሱን የሚያስተዳድር የብሪታኒያ ግዛት በ1916 ዓ.ም. ሆነ። በ1945 ዓ.ም. ብሪታኒያ ሁለቱን ሮዴዢያዎች ከኒያሳላንድ (አሁን ማላዊ) ጋር አገናኝታ በአንድላይ የሮዴዢና ኒያሳላንድ ፌዴሬሽን ተባሉ። ረብሻና የአፍሪካዊ ሰሜት ብሪታኒያ ፌዴሬሽኑን በ1956 ዓ.ም. እንድታፈርስ አደረጉ። በ1958 ዓ.ም. ኢያን ስሚዝ ከብሪታኒያ ነጻነት አወጀ። ከዛም በ1962 ዓ.ም. ደቡባዊ ሮዴዢያ የሮዴዢያ ሪፐብሊክ ሆነች። በኢያን ስሚዝ የሚመራው የነጮች መንግሥት የሮዴዢያን ነጻነት በኖቬምበር 11፣ 1965 እ.ኤ.አ. አወጀ። የብሪታኒያ መንግሥት ከስሚዝ አመራር ጋር በ1966 እና 1968 እ.ኤ.አ. ያደረገው ንግግሮች ስኬታዊ ስላልነበሩ ዩናይትድ ኔሽንስን በሮዴዢያ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣልባት ጠየቀች። የስሚዝ አመራር የሪፕብሊክ መንግሥት መሆኑን በ1970 እ.ኤ.አ. ቢያስታወቅም እውቅና የሰጠው ሀገር ግን የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ብቻ ነበር። የደፈጣ ተዋጊዎች ነጮችን ማጥቃት ጀመሩ። የስሚዝ አመራር በሮበርት ሙጋቤ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ብሔራዊ ሕብረት እና በጆሱዋ ንኮሞ ከሚመራው የዚምባብዌ አፍሪካዊ ሕዝብ ሕብረት ጋር የድርድር ንግግሮችን ጀመረ። በማርች 1978 እ.ኤ.አ. የስሚዝ አመራር ሊወድቅ ሲደርስ በሊቀ ጳጳስ አቤል ሙዞርዋ በሚመሩ ሶስት ጥቁር መሪዎች ጋር የነጭ ዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ ስምምነት ፈረመ። በ1979 እ.ኤ.አ. ሁሉም ፓርቲዎች በለንደን ተገናኝተው የእርስ-በርስ ጦርነቱን ለማቆም የላንካስተር ቤት ስምምነትን ፈረሙ። \n \nጥያቄ: ደቡባዊ ሮዴዢያ ራሱን የሚያስተዳድር የእንግሊዝ ግዛት የሆነው መቼ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ በ1916 ዓ.ም. ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nበጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ። ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ። በፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች። አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣ፣ ጥጥ፣ ጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው። ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል። \n \nጥያቄ: ከ1981 እ.ኤ.ኣ. ለሃያ ዓመት የሴኔጋል ፕሬዝዳንት የነበሩትት አብዱ ዲዮፍ መጀመሪያ ወደ ስልጣን የመጡት በማን አማካኝነት ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ በሊዎፖልድ ሴንግሆር ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ለሚከተለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከዚህ በታች የቀረበውን አውድ ተጠቀም፡ \nኤዎስጣጤዎስ በግዕዝ ኤዎስጣቴዎስ ወይም ዮስጣቴዎስ፣ ከሐምሌ ፭ ቀን ሺ፪፻፷፭ – ሺ፪፫፵፬ በኢትዮጵያ ሰለሞናዊ መንግሥት አገዛዝ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ታላቅ መሪ የነበሩ አባት ናቸው። በጣም አጥብቀው ከሚያስተምሩት ትምህርት ስለ ሰንበት መከበር ነበረ። ተከታዮቻቸው የኤዎስጣጤዎስ ቤት ወይም በግል ሲጠሩ ኤዎስጣጤዎሳውያን ይባሉ ነበር ለተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ናቸው። የኤዎስጣጤዎስ መጀመሪያ ስማቸው ማዕቀበ እግዚእ ሲሆን ከእናታቸው ከስነሕይወትና ከአባታቸው ከክርስቶስ ሞዐ ሐምሌ ፳፩ ቀን ፩ሺ፪፷፭ ተወለዱ። እኒህም ደጋግና እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ነበሩ ። ኤዎስጣጤዎስ የታወቀውን ደብራቸውን (ደብረ ፀራቢን) የመሠረቱት የተወለዱበት ቦታ እዛው (እንድርታ) እንደሆነ ገድላቸው ይገልፃል። በወጣትነታቸው ዘመን በሺ፪፸፪ አካባቢ ከአጎታቸው አባ ዳንኤል (የደብር ስማቸው አባ ዘካርያስ) ቆርቆር (ደብረ ማርያም) አስተዳዳሪ ጋር እንዲኖሩ ወደ ገራልታ ይላካሉ። አባ ዳንኤልም ኤዎስጣጤዎስን ተቀብለው ተገቢውን የሃይማኖት ትምህርትና የደብር ሕይወትን ካስተማሩ በኋላ ማዕቀበእግዚእ በ፲፭ ዓመቱ ቅስና ሥራዬ መሆን አለበት ብሎ በወሰደው ውሳኔ መሠረት ስሙ ኤዎስጣጤዎስ ተብሎ ተሰየመ። ኤዎስጣጤዎስ ከአባ ዳንኤል የቅስና መዐረጋቸውን ካገኙ በኋላ የራሳቸውን ደብር በ(ሰራይ) መሠረተው በዚያም በማስተማር ብዙ ተማሪዎችን አፈሩ ። በሰንበት ላይ ያተኮረ አመለካከታቸውን ለይተው ያስተምሩ ነበር ፣ የሚቃወማቸው አቡነ ያእቆብ ፫ኛው አስኪመጣ ድረስ። ከዛ ግን ከተከታዮቻቸው ከባካርሞስ ፣ መርቆርዮስ ፣ ገብረእያሱ ጋር ኢትዮጵያን ለቀው ወደ ግብፅ (ካይሮ) ገብተው በአሌክሳንድሪያው ጳጳስ ቢንያም ፪ኛው ፊት በሰንበት ባላቸው አመለካከት ፀንተው ከዛም ወደ ኢየሩሳሌም አምርተው በመጨረሻም የሕይወታቸው ማብቂያ ወደ ሆነችው አርሜኒያ ገብተው ኖሩ። \n \nጥያቄ: የኤዎስጣጤዎስ ወላጆች ማን ይባላሉ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልሱ እናታቸው ከስነሕይወትና ከአባታቸው ከክርስቶስ ሞዐ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nአቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ በሃገራችን ኢትዮጵያ ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው። ጻድቁ የተወለዱት በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅ እና ቅድስት እድና ይባላሉ ። የተወለዱበት አካባቢም ሮም ነው ። ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው። ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረአምላክ ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ። በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል። ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል። \"የት ልሒድ?\" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮጵያን አሳያቸው። ተመልሰውም ለስምንት ባልንጀሮቻቸው \"ሃገርስ ባሳየኋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር\" ብለው ከስምንቱ ጋር ከቃልኬዶን ጉባዔ በኋላ በ፬፻፶፩ ዓም ወደ ኢትዮጵያ መጡ ። ከዘጠኙ ቅዳሳን ወደ ኢትዮጵያ ከሮምና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከፈለሱት አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው ። በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ። ወደ ሃገራችን የመጡ በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል። በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል ። አቡነ አረጋዊ ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል ። በመጨረሻም ደብረ ዳሞ ማረካቸዋለች ። ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታ በመንፈቀ ለሊት ተገልጾ ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁብሎ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ ብሎ ተስፋቸውን ነገራቸው፡፡ እሳቸው መነኮሳቱን ሰብስበው ከእንግዲህ በሥጋ አታዩኝም ብለው ነግረዋቸው አበምኔት (የገዳም አባት ወይም አለቃ) ሾመውላቸው ጥቅምት አሥራ አራት ቀን በዚያው በደብረ ዳሞ ተራራ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ተሰውሯል ፡፡ \n \nጥያቄ: ለአቡነ አረጋዊ ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም ማን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ ዘሚካኤል ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nመርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ጅሩ ቆላ ውስጥ እምባጮ መግደላዊት በሚባል ሥፍራ መጋቢት ፲፯ ቀን በ፲፰፻፺፩ ዓ/ም ተወለዱ። በቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያ ትምህርታቸውን እስከ ዳዊት ድረስ ካጠናቀቁ በኋላ የዜማ ትምህርት ተከታትለው ጾመ ድጓ እና ድጓን ዘልቀዋል። ቀጥሎም የቅኔ ትምህርታችውን አጠናቀው በ ፲፱፻፭ ዓ/ም በአሥራ አራት ዓመት ዕድሜያቸው በወንበር ፀሐፊነት የመጀመሪያ ሥራቸውን ጀመሩ። የመጻሕፍተ ሐዲሳትን ትርጓሜ፤ የዮሐንስ አፈወርቅን ትርጓሜ፤ እንዲሁም የመቅድመ ወንጌልን ትርጓሜ ትምህርት ያጠናቀቁት እኝህ ታላቅ ሰው ብርሃንና ሰላም (ጋዜጣ) የተሰኘው ጋዜጣ ሲመሠረት የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ በመሆን፣ ቀጥለውም በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የግዕዝና የአማርኛ አስተማሪ በመሆን አገልግለዋል። ከፋሺስት ወረራ በኋላ ከ፲፱፻፴፫ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፷፫ ዓ/ም ድረስ በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በኃላፊነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ሥነ ጽሑፍንና ታሪክን በተመለከተ፣ አሥራ ሦስት መጻሕፍትን የደረሱ ሲሆን፣ ሰባት መጻሕፍት ደግሞ ተርጉመው አቅርበዋል። እንዲሁም የተለያዩ ጽሑፎችን አሰባስበው ከማዘጋጀታቸው ባሻገር፣ የቅዱሳት መጻሕፍት ሥራዎችም ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር በትብብር አዘጋጅተዋል። \n \nጥያቄ: ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ መቼ ተወለዱ?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ መጋቢት ፲፯ ቀን በ፲፰፻፺፩ ዓ/ም ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nቦትስዋና ቦትስዋና ወይም በይፋ የቦትስዋና ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ Republic of Botswana ሰጿና፡ Lefatshe la Botswana) በደቡባዊ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ አገር ናት። ቦትስዋና የቀድሞ የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ስትሆን ነፃነቷን በመስከረም ፳ ቀን ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. ከተቀዳጀች በኋላ መሪዎቿ በነፃ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ተመርጠዋል። ቦትስዋና ሜዳማ ስትሆን ከሰባ ከመቶ በላይ በካለሃሪ በርሃ የተሸፈነች ናት። በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ከደቡብ አፍሪካ፣ በምዕራብና ሰሜን ከናሚቢያ እና በሰሜን ምሥራቅ ከዚምባብዌ ጋር ትዋሰናለች። ከዛምቢያም ጋር በደንብ ያልተወሰነ ቢበዛ በመቶ ሜትር የሚቆጠር ወሰን አላት። \n \nጥያቄ: ቦትስዋና የት አህጉር የምትገኝ ሀገር ነች?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ አፍሪካ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nቴምፕላርስ ቴምፕላር ወይም በሙሉ ስማቸው የክርሰቶስ እና የሰለሞን መቅደስ ምስኪን ወታደሮች የሚባሉት በጣም ታላቅ እና ሃይለኛ ከነበሩት ክርስቲያናዊ ወታደራዊ ስርአቶች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው። ይህ ስርዓት በ1088 ዓ.ም. ከተካሄደው አንደኛው የመስቀል ጦርነት በኋላ ማለትም በ1110 ዓ.ም. አዲስ የተቋቋመውን የእየሩሳሌም መንግስት ከእስላሞች ለመከላከልና ወደ ከአውሮፓ ወደ እየሩሳሌም የሚጎርፉትን ተሳላሚዎች ደህንነት ለመጠበቅ የተመሰረተ ነው። ቴምፕላሮች የተዋቀሩት በገዳማዊ ስርዓት ሲሆን ይኸውም የሲሰተርሲያን ስርዓት መስራች የነበረው የክላርቮው በርናርድ በዘረጋላቸው ህግጋት መሰረት ነው። ቴምፕላሮች ከብዙ መሳፍንት ጋር ግንኙነት ስለነበራቸው እና ጳጳሱም እነሱ ከሚቆጣጠሩዓቸው ቦታዎች ሁሉ ግብርና አስራት እንዲሰበስቡ ስለፈቀደላቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝነኛና ሃይለኛ ለመሆን ችለዋል። ቴምፕላሮቹ አራት ዋና ክፍሎች የነበሩአቸው ሲሆን እነዚሁም ዋነኞቹ ወታደሮች ወይም ናይትስ የሚባሉት ሙሉ የፈረሰኛ ትጥቅ የታጠቁ ከዝቅተኛ የህብረተሰቡ ክፍል የተውጣጡት ወይም ሰርጀንትስ በመባል የሚታወቁት፤ መለስተኛ የፈረሰኛ ትጥቅ የታጠቁ ገበሬዎች ዋነኛው ስራቸው የስርዓቱን ንብረት ማስተዳደር የነበረ፤ እንዲሁም ካህናት ስራቸው የስርዓቱን መንፈሳዊ ህይወት መከታተል የነበረ ናቸው። \n \nጥያቄ: ክላርቮው በርናርድ የመሰረተው የገዳማውያን ሥርዓት ምን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ የሲሰተርሲያን ስርዓት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nነሐሴ ፳፰ ነሐሴ ፳፰ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፰ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፰ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፯ ዕለታት ይቀራሉ። 1862 - የፕሩሲያ (ጀርመን) ሠራዊት 3ኛ ናፖሊዎንን ከ100,000 ጭፍሮች ጋር በሰዳን ውግያ አሸነፈ። 1890 - በኦምዱርማን ውግያ ሱዳንን የእንግሊዝ ሠራዊት ድል በማድረግ ቅኝ አገር አደረጉት። 1935 - በ2ኛ አለማዊ ጦርነት ኢጣልያ በጓደኞቿ ሃያላት (በጀርመን ኃይል) ተወረረች። 1946 - የቻይና ኃያላት የደቡብ ኮርያ ደሴቶችን በቦምብ ደበደቡ። ፲፱፻፸፱ ዓ/ም በቡሩንዲ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሻለቃ ፒዬር ቡዮያ የአገሪቱን ፕሬዚደንት ዣን ባፕቲስት ባጋዛን ከሥልጣን አስወረዱ። \n \nጥያቄ: በ1890 በተደረገው የኦምዱርማን ውግያ ሱዳንን ድል ያደረጋት የማን ሀገር ሠራዊት ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ የእንግሊዝ ሠራዊት ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nላሊበላ ላሊበላ በኢትዮጵያ፣ በአማራ ክልል በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሃገር የምትገኝ ከተማ ነች። በ ላይ የምትገኘው የላሊበላ ከተማ ከባህር ጠለል በላይ 2,500 ሜትር ከፍታ ያላት ስትሆን የህዝቡም ብዛት ወደ 11,152 ነው። 1 ላሊበላ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ከተማዎች መካከል ከአክሱም ቀጥላ በሁለተኛነት ደረጃ የምትገኝ ከተማ ስትሆን፣ ለአብዛኞቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንደ ዋና የእምነት ማእከል በመሆን ታገለግላለች። የላሊበላ ነዋሪዎች በአብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው። የላሊበላን ከተማ በዋነኛነት ታዋቂ ያረጉዋት ከክ.ል. በኋላ በ13ኛው መቶ ክፍለዘመን እንደ ተሰሩ የሚነገርላቸው 11 አብያተ-ክርስቲያናት ናቸው። በኢትዮጵያ ትውፊት መሰረት እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት በንጉሥ ላሊበላ ዘመን በቅዱሳን መላዕክት እረዳትነት እንደተሰሩ የሚታመን ሲሆን ግርሃም ሃንኮክ የተባለው እንግሊዛዊ ፀሃፊ ግን እኤአ በ1993 ዓ.ም ባሳተመውና The Sign and the Seal በተባለው መጽሃፉ አብያተ-ክርስቲያናቱን በማነፁ ሥራ ላይ ቴምፕላርስ የሚባሉት የመስቀል ጦረኞች ተካፍለዋል ሲል አትቷል ነገር ግን ማረጋገጫ አልነበረውም። እነዚሀ አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ አርባ ትንንሽ ቤተክርስቲያኖች አሉ። \n \nጥያቄ: ላሊበላ ከባህር ጠለል በምን ያህል ከፍታ ላይ ትገኛለች?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ 2,500 ሜትር ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nባሕር-ዳር ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች። ባሕር-ዳር ከአዲስ አበባ 565 ኪ.ሜ ወደ ሰሜን-ሰሜን ምዕራብ ትገኛለች። ባህር ዳር ከጢስ አባይ በ30 ኪሎሜትር ስለምትርቅ ለጎብኚዎች አመቺ ቦታ ላይ ናት። ባህር ዳር የአንድ የአስፋልት ንጣፍ ያለው ኤርፖርት የሰፊ ገበያና የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች እና ታሪካዊ እና ጥንታዊ ግዳማት መግኛ ቦታ ናት። ባሕርዳር ከተማ የምትገኘዉ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዲስ አበባ በ 565 ኪሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ አስትሮኖሚያዊ መገኛ ቦታዋ በ 11º 38’ በሰሜን ላቲቲውድ እና በ37º15’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው የባሕር-ዳር ስያሜን ያወጡት አፄ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ እሳቸውም ይሕን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ \"ከባሕሩ-ዳር\" አድርጉ የተባሉ ሰወች ለመንደሩ ባሕር-ዳር ብለው ስያሜ አወጡለት ይባላል። ባሕር-ዳር ከተማ የተቆረቆረችው በ1915 ዓ.ም ነው ፡፡ ባሕር-ዳር በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንድዋ ስትሆን፤ የከተማ አስተዳደር፣ 3 ሜትሮፖሊታን ክ/ከተማዎች፣ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት፣ 9 የከተማ ቀበሌዎችና 4 የገጠር ቀበሌዎች አሏት፡፡ ከተማዋ በ1998 ዓ.ም የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡ የተቆረቆረችበትን ዓመት፣ የቆረቆሩትን ቀደምት ሠዎች፣ የሠፈሮችን ስሞች፣ ለባሕር-ዳር የተገጠሙትና የተዘፈኑ ታሪካዊ ግጥሞችና ስነ ቃሎች፣ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጎጆ ቤት ወደ አሁኑ ይዞታው አመጣጥ (ባሕር-ዳርን ስናስብ ጊዮርጊስን ሚካኤልን እና ገበያውን ከገበያው አካባቢ የነበረውን ፍርድ ቤት ነጣጥሎ ማየት አይቻልም የሚል አስተያየት ስላለ ነው)፣ ባሕር-ዳር እንደባሕር ዳርነቱ ከመቆርቆሩ በፊት በሚካኤል እና በሽመምብጥ ሠፈር አካባቢ ስለነበረው አሰፋፈር፣ ስለማዘጋጃቤቱ፣ ስለ አውቶቡስ ተራው፣ ስለ ድባነቄ ተራራ፣ እና ስለ መሳሉት፣ ስለፖሊቴክኒክ፣ ስለዓባይ ወንዝና ድልድዩ፣ ስለዓባይ ወንዝና ስለጣና ሐይቅ መገናኛ እና ስለሌሎችም ቁልፍ ነገሮችን ማቅረብ የሚችሉ አፈታሪኮች አሉ። \n \nጥያቄ: ባሕር ዳር ከተማ በሰሜናዊ ጫፍ የምትገናኘው ከየትኛው ሐይቅ ጋር ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ከጣና ሐይቅ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ከዚህ በታች በተሰጠው አውድ መሰረት መልሱ፡ \nነሐሴ ፳፯ ነሐሴ ፳፯ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፶፯ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስ፤ ማርቆስ እና ዮሐንስ ደግሞ ፰ ዕለታት ይቀራሉ። ፲፮፻፶፰ ዓ/ም ለሦስት ቀናት የጋየውና አስር ሺህ ሕንጻዎችን ያወደመው የሎንዶን ትልቁ እሳት ተነሳ። ፲፯፻፵፬ ዓ/ም የምዕራብ አውሮፓ አገራት ዘመን አቆጣጠራቸውን በለወጡ በሁለት መቶ ዓመታቸው፣ ብሪታንያ የጎርጎራዊ ዘመን አቆጣጠርን ተቀበለች። ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - በጠላት ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው የልጅ ኢያሱን ልጅ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን አነገሡ። አዲሱ 'ንጉሥ' ወዲያው የአርበኞች መሪ ለነበሩት ባላምባራስ አበበ አረጋይ የራስነት ማዕርግ ሰጠ። መልአከ-ፀሐይ ኢያሱ መስከረም ፳፬ ቀን ፲፱፻፴፩ ዓ/ም አረፎ አንኮበር አካባቢ በሚገኘው ዞማ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተቀብሯል። ፲፱፻፴፯ ዓ/ም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጃፓን በተሸናፊነቷ እጇን ሰጠች። ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ነጻነትን አስከትሎ በጃዋሃርላል ኔህሩ ምክትል ፕሬዚደንትነት የሚመራ የሕንድ ጊዜያዊ መንግሥት ተመሠረተ። ፲፱፻፺ ዓ/ም የርዋንዳን ፍጅት አስከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቋቋመው የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ጃን ፖል አካዬሱ የተባለውን የቀድሞ ከንቲባ ላይ ፍርዱን የወንጀለኛነት ፍርድ ፈረደበት። \n \nጥያቄ: በነሐሴ ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፱ ዓ/ም በጣልያን ወረራ ዘመን የሸዋ አርበኞች ቡልጋ ላይ ተሰባስበው ያነገሡት ማንን ነበር?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው ትክክለኛው ምላሽ መልአከ-ፀሐይ ኢያሱን ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nጎግል ስለኮሮና ቫይረስ መረጃዎችን ለማቅረብ የኤስ ኦ ኤስ ማንቂያን ወደ ስራ ማስገባቱን አስታወቀ። ኩባንያው በትናንትናው ዕለት ወደ ስራ ያስገባው ማንቂያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማድረስ ያግዛል ተብሏል። ስለኮሮና ቫይረስ እና ተያያዥ ጉዳዮች ሰዎች መረጃዎችን በሚፈልጉበት ወቅት ጎግል “በነጭ ካርድ መደብ” ላይ የኤስ ኦ ኤስ ማንቂያውን በማሳየት ተፈላጊውን መረጃ ለተጠቃሚዎቹ በቀጥታ ያጋራልም ነው የተባለው። ጎግል ለዓለም አቀፍ መረጃ ፈላጊዎች በማንቂያው ላይ የዓለም ጤና ድርጅት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራሎችን አድራሻ ማካተቱንም አስታውቋል። አስፈላጊ ከሆነም በሂደት ማንቂያውን ለአካባቢያዊ መረጃ ፈላጊዎች በሚሆን መልኩ እንደሚያካትትም ገልጿል። በቀጣይም ስለ ኮሮና ቫይረስ ጠቃሚ መረጃ፣ ያለበትን ሁኔታ እና ጥያቄና መልሶችን ያካተቱ አንቀጾች ያሉበት “የእርዳታ እና መረጃ” ማፈላለጊያን ከዓለም ጤና ድርጅት አድራሻ ጋር በማያያዝ አቀርባለሁ ብሏል። ኩባንያው በአስፈላጊ እና ወሳኝ ወቅት ላይ ተጨማሪ የመረጃ ማሻሻያ እንደሚያደርግ በመግለፅ የማንቂያ ስርዓቱ ለኮሮና ቫይረስ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲገኙ ያስችላል ነው ያለው። በሞባይሎች እና ድረ ገፆች ላይ የሚገኘው ኤስ ኦ ኤስ ማንቂያ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት እንዲሁም በአጠቃላይ የሰዎች ደህንነት አደጋ ላይ በሚሆንበት ወቅት ጥቅም ላይ የሚውል ነው። ከዚህ ባለፈም ኩባንያው ለቻይና የቀይ መስቀል ማህበር የ250 ሺህ ዶላር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ በመረጃ ማፈላለጊያ ገጹ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በተከፈተ ዘመቻ ከ800 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰብ ተችሏል። ምንጭ፦ ጎግል \n \nጥያቄ: ስለኮሮና ቫይረስ መረጃዎችን ለማቅረብ የኤስ ኦ ኤስ ማንቂያን ወደ ስራ ያስገባው ድርጅት ማን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ ጎግል ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "የተሰጠውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የቀረበውን መረጃ ይመልከቱ፡ \nኢትዮ ሬይን ሜከርስ ኢትዮ ሬይን ሜከርስ (Ethio Rain Maker) በኢትዮጵያ ውስጥ ዛፎች በመትከል ረሃብን ለመከልከል የተቋቋመ ቡድን ነው። አሁን ወደ ምድረ በዳ መጥተው በወንድማማችነት ገነት ይሠራሉ። በድርቅ አፈር ውስጥ የሚተክሉት ዘር ታላቅ ደን ይሆናል፤ ምድሪቱ እንደገና በሙሉ እስክትሸፈን ድረስ ረጀም ዛፎች በዝተው አረንጓዴ ክንፎቻቸውን ይዘረጋሉ። ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም መገናኛ ብዙሃን በረሃብ ስትጠራ፣ ህዝቦችዋ በጠኔ ሲሰቃዩ ዘመናት ተቆጥረዋል። የወገኖቻችን ስቃይ፣ የሀገራችን ኋላ ቀርነት በኢትዮጲያዊነታችን እያንዳንዳችንን ይመለከተናል። ላለፉት ሰላሳ አመታት በጎ አድራጊ ድርጅቶች በአይነትም ሆነ በጥሬ ገንዘብ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደረዱን መረጃ አውጥተዋል። የኛ ስቃይ ግን አላበቃም። መከር ሲመጣ ሰብል ከማጨድና ምርት ከመሰብሰብ ይልቅ ለልመና እጁን የሚዘረጋ ኢትዮጲያዊ ቁጥር በሶስት እጥፍ ጨመረ። ይህ ሂደት መቆም አለበት። እንዴት? አበው “ነገርን ከስሩ …” እንደሚሉት የሁሉም ችግር መፍትሔው ያለው ከመነሻው ላይ ነው። የኛ ረሐብ መንስዔው ምንድነው? በአጭሩ ለመግለጽ ያህል ለረሐባችን መንስዔ የዝናብ አለመኖር (ድርቅ) መሆኑን ከረሐባችን ታሪክም ሆነ ጥናቱን ካካሄዱት ምሁራን መረዳት ይቻላል። ዛሬም ቢሆን ገበሬው ዝናብ በማጣቱ ሰብሉ መበላሸቱን ከአንደበቱ እየሰማን ነው። ጦርነትን ለማቆም የጦርነት መነሻ ሃሳቦችን ማስወገድ እንጂ ጦርነትን ከጦር ሜዳ ማስቆም እንደማይቻል ሁሉ የሃገራችንንም ረሃብ ከመንስዔው እንንቀለው። ኢትዮ ሬይን ሜከርስ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ደን ማደነን (አፎረስቴሽን) ችግራችንን ከመቅረፊያ መንገዶች አንዱ እንደሆነ በማመን የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ችግኞችን መትከል ጀምሯል። በ1995 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለ አደራ ጋር በመተባበር በእንጦጦ የተፈጥሮ መናፈሻ አስር ሺህ ችግኞችን ተክሎ ሰባ ሁለት ከመቶው (7167) ፀድቋል። በ1996 ክረምት ደግሞ ሀምሳ ሺህ ችግኞችን ለመትከል አቅዶ ሀያ ከመቶው ተጠናቋል። በአሰላ፣ በመቀሌና በባህር ዳር አንድ ሺህ ዛፎችን የሚይዙ የተፈጥሮ መናፈሻዎችንን በመስራት ላይ ነን። በ1997 ለሀገራችን የሺህ አመት ስጦታ እንስጥ በሚል መነሻ ሀሳብ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ አንድ ዛፍ ተክሎ የሚንከባከብበትን እቅድ አውጥተናል። ከነዚህም አንዱ አንድ ዛፍ ለአንድ ተማሪ ነው። የሃገራችን የዘመናት ችግር በአንድ አመትና በጥቂት ሰዎች ጥረት አይፈታም። ለዚህ አላማ መሳካት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥረትና እገዛ ያስፈልጋልና ሃገራችንን ከረሐብ ለመታደግ አብረን ዛፍ እንትከል። እንንከባከብም። \n \nጥያቄ: ኢትዮ ሬይን ሜከርስ በ1995ዓ.ም. እንጦጦ አካባቢ ከማን ጋር በመሆን አስር ሺህ ያህል ችግኝ ተከሉ?", "role": "human" }, { "content": "ለተጠቀሰው ጥያቄ ትክክለኛው ምላሽ ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለ አደራ ጋ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት ቀረቡ። በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ኢትዮጵያን በመወከል ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸው ነው የተነገረው። የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሂሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋና የቋንቋ ጥናት ክፍል ለረጅም ዓመታት በመምህርነት አገልግለዋል። \n \nጥያቄ: ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት እጩ የቀረቡት ማን ናቸው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር መረጃ በመጠቀም ለሚከተለው ጥያቄ መልስ ይስጡ፡ \nቅልልቦሽ ቅልልቦሽ የኢትዮጵያ ህጻናት በጠጠር የሚጫወቱት ሲሆን አጨዋወቱም አንዱዋን ጠጠር ወደአየር በማጉናት እሱዋ ባየር ላይ እያለች የተቻለን ያክል ጠጠር ከመሬት ማፈስ ነው። ባየር ላይ ያለችው ጠጠር ስትመለስ በተጫዋቹ እጅ \"መቀለብ\" ወይም \"መያዝ\" ይኖርባታል። ሳትያዝ መሬት ላይ ከወደቀች፣ ጨዋታው አለቀ ማለት ነው። ጨዋታው \"ጠጠር\" በመባልም ይጠራል። ብዙ አይነት የቅልልብልቦሽ ጨዋታዎች ሲኖሩ፡ በጣም የታወቀው \"ዓይጥ አለብሽ\" በመባባል የሚጫወቱት ነው። ልጆቹ ሁለት ወይም ሶስት ይሆኑና፡ አምስት ቆንጆ ድብልብል ጠጠሮች፡ ስፋትና ርዝመታቸው ከግማሽ ኢንች የማይበልጡ፡ ይለቅሙና መሬት ይቀመጣሉ። ቀድሞ \"ብጀ\" ያለ መጀመርያ ይጀምራል። ብጀ ማለት ብጀምር ማለት ነው። ያንን ለማለት እሽቅድምድም ነው።\"ብቀ\" ያለ ከርሱ የሚከተል ነው ማለት ነው፡፡ ብቀ ማለት ብቀጥል ማለት ነው። ሁለት ልጆች እኩል \"ብቀ\" ካሉ በድምጽም ቢሆን ቀድሞ \"ብ!\" ከአፉ የወጣው ሰው ሁለተኛነቱን ያገኛል። \"ብቀጣጥል!\" ያለ ሶስተኛ ነው። \"እንጀራ ብጋግር!\" ያለ አራተኛ ነው። አምስተኛ ካለ \"ወጥ ብሰራ!\" ብሎ ተራውን ያሳውቃል። በዚህ ተራ ተስማምተው ጀማሪው ይጀምራል። \n \nጥያቄ: በቅልብልቦሽ ጨዋታ አራተኛ ለሆነ ምን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው አንጻር ትክክለኛው መልስ እንጀራ ብጋግር ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nአሦር አሦር (አሹር) ማለት በጥንታዊ ዘመን በላይኛ ጤግሮስ ወንዝ አጠገብ የተገኘ ከተማና አካባቢው ነበረ። በኋለኛ ጊዜ የአሦር መንግሥት ሃይለኛ ሆኖ መላ መሬት እስከ ግብጽ ድረስ ገዛ። በጥንታዊ አሦር ከተማና በጤግሮስ አጠገብ ያሉትም ተራሮች እስከ ዛሬው አርሜንያ ድረስ 'የአሦር ተራሮች' ይሰየሙ ነበር። በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት አሦር (አሹር) ከኖኅ ልጅ ሴም ልጆች አንዱ ሲሆን፥ ከሰናዖር ወጥቶ አንዳንድ ከተማ ሠራ። በአሦራውያንም እምነት ዘንድ 'አሹር' ከተማውን የመሠረተው አምላክ ስም ነበረ። ከቅድመኛው ዘመን አውራጃው ሹቡር ተብሎ ከሰናዖር (ሹመር)፣ ማሪ ወይም ከአካድ ይገዛ ነበር። ሹቡር በታላቁ ሳርጎን መንግሥት ውስጥ ክፍል ሆኖ ጉታውያን እስከ አጠፉት ድረስ ቆየ። በኋላ እስከ 1879 ዓክልበ. ግ. ከኡር 3ኛ ሥርወ መንግሥት ይቆጣጠር ነበር። የዑር መንግሥት ሲወድቅ የአሦር ከተማ ነገሥታት ሊሙ ስሞች ይመዘገባሉ። በዚህ ወቅት አሦር ከተማ-አገር ብቻ ነበረ። ሆኖም አሦራውያን የብረታብረት ንግዳቸውን ለማስፋፋት በማሰብ አንዳንድ ቅኝ-ከተማ (ካሩም) በሐቲ (ዛሬው ቱርክ) ውስጥ መሠረቱ። ከነዚህም ዋነኛው ካነሽ የተባለው ከተማ ነበር። በ1720 ዓክልበ. ግ. አሞራዊው ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ አገሩን ከነአሦር ከተማ አቀና። ልጁን 1 እሽመ-ዳጋን (1688-1678 ዓክልበ.) በአሦር ላይ ሾመው። ነገር ግን የባቢሎን ንጉስ ሃሙራቢ ድል አድርጎት ዙሪያው ወደ ባቢሎን መንግሥት ተሳለፈ። ከትንሹ እስያ ይካሄድ የነበረው የብረታብረት ንግድ በዚያን ጊዜ ተቋረጠ። ለሚከተለው መቶ አመት አሦር ለባቢሎን ተገዥ ነበር። በ1507 ዓክልበ. ግ. ባቢሎን ለካሣውያን ከወደቀ በኋላ፥ አሦር በሚታኒ መንግሥት (ሑራውያን) በ1441 ዓክልበ.ግ. ይሸነፍ ነበር። ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ ግን የአሦር ንጉስ አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን አዋጀ (1366 ዓክልበ. ያህል)። ከዚህ በላይ ይህ አሹር-ኡባሊት የራሱን ልጅ ኩሪጋልዙን በባቢሎን ዙፋን ላይ አሾመው። በ1290 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ የሚታኒን መንግሥት አሸነፈ። የአዳድ-ኒራሪ ተከታይ 1 ስልምናሶር መንግሥቱን በከጢያውያን አግጣጫ እስከ ከርከሚሽ ድረስ አስፋፋ። የስልምናሶርም ልጅ 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ እንኳን በባቢሎን ላይ ገዛ። ሆኖም በቅርብ ጊዜ ባቢሎን በአሦር ላይ አመጽ ታደርግ ነበር። በ1200 ዓክልበ.. አካባቢ የኬጢያውያን መንግሥት በሙሽኪ (ፍሩጋውያን) ግፊት ስለ ወደቀ፥ ባቢሎንና አሦር ለአሞራውያን መሬት ተወዳዳሪዎች ሆኑ። የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በዚህ አቅራቢያ በ1140 ዓክልበ. በባቢሎንን ንጉሥ 1 ናቡከደነጾር ላይ አሸነፈ። የአሹር-ረሽ-ኢሺ ልጅ 1 ቴልጌልቴልፌልሶር የመንግሥቱን ጠረፍ በጣም አስፋፋ። ከርከሚሽን ከመማረኩ በላይ በሙሽኪ ላይ እስከ ጥቁር ባሕር ድረስ ዘመቻ አደረገ። ደግሞ እስከ ሜድትራኒያን ባሕር ድረስ ሲዘረጋ ፊንቄን (ሊባኖስ) ያዘ። ከ1 ቴልጌልቴልፌልሶር በኋላ ከጎረቤቶቹ ከአራማውያንና ከኡራርቱ የተነሣ የአሦር ኅይል ደክሞ ነበር። በ920 ዓክልበ. ግን 2 አዳድ ኒራሪ ንጉሥ ሆሞ የአሦር ሃይል ታደሰ። ደግሞ ወደ ስሜን የኖሩትን ሕዝቦች በሙሉ በሰፈራ አፈለሳቸው። ይሁንና መንግሥቱ ከአቦር ወንዝ ወደ ምዕራብ አልዘረጋም። ንጉስ አሹር-ናሲር-ፓል ከ890 ዓክልበ. ጀምሮ ነግሦ ያለ ምኅረት ጠረፎቹም አስፋፋ። ከአቦርና ከኤፍራጥስ መካከል ያሉትን አራማውያን ድል አድርጎ በሜድትራኒያን ሲደርስ ፊንቄን ቀረጠ። ካልሁንም ዋና ከተማው እንዲሆን አደረገው። በልጁ 3 ስልምናሶር 34 አመት ዘመን (865-831 ዓክልበ.) አሦር በየአመቱ ለጦርነት ሠለፈ። ባቢሎን ተወርሮ ተቀረጠ። የሶርያ (አራም-ደማስቆ) ንጉስ ወልደ አዴር (አድርአዛር) ከእስራኤል ንጉስ አክዓብ ጋራ በቃርቃር ፍልሚያ ስልምናሶርን አጋጠመው። ስልምናሶርም ፊንቄንና የእስራኤል ንጉስ ኢዩን አስቀረጠ። በዋና ከተማው በካልሁ የተገኘው ጥቁር ሐውልት ስለ 3 ስልምናሶር ዘመን ድርጊቶች ይመሰክራል። \n \nጥያቄ: የሚታኒን መንግሥት በ1290 ዓክልበ. ያሸነፈው የአሦር ንጉስ ማን ይባላል?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች በተገለጸው አውድ ተከታዩን ጥያቄ ይመልሱ፡ \nየላሊበላ ግሎባል ኔትወርክስ ድርጅት ተባባሪ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ (ዶ/ር) ዓለም አቀፉን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ አዲስ የስራ ፈጣራ ውድድር አሸነፉ። ኢትዮጵያዊቷ በየዓመቱ የሚካሄደውን ዓለም አቀፉን ፒአይቲሲኤች (PITCH) አዲስ የስራ ፈጠራ ውድድር በትላንትናው እለት ማሸነፉቸው ይፋ ሆኗል። ውድድሩ 2500 ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወደ መጨረሻው ዙር ያለፉት ደግሞ 700 የሚሆኑ አዲስ ፈጣሪዎች ነበሩ። ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ ውለታ ለማ(ዶ/ር) በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያቀረቡት አዲስ የስራ ፈጠራ በቅርበት ተፎካካሪ ከነበሩት የአሜሪካና የእንግሊዝ የስራ ፈጣሪዎችን በመብለጥ የዓመቱ ውድድር አሸናፊ ሆኗል። ውለታ ለማ (ዶ/ር) ለውድድሩ ያቀረቡት የስራ ፈጠራ አባይ ሲ ኤች አር (ABAY CHR) የተባለ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ህክምና ዘርፍ ያለውን ሰፊ የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታል በመቀየር ስራን የሚያቀልና የሚያቀላጥፍ እንዲሁም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪን የሚያስቀር የሥራ ፈጠራ ነው ተብሏል። \n \nጥያቄ: ዶ/ር ውለታ ለማ ያሸነፉበት አዲስ የሥራ ፈጠራ ውድድር በምን ዘርፍ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ከጥያቄው ጋር የሚስማማው ምላሽ በጤና ቴክኖሎጂ ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nበጃኑዋሪ 1958 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋልና የፈረንሣይ ሱዳን ተቀላቅለው የማሊ ፌዴሬሽንን መሠረቱ። ይህም ፌዴሬሽን በአፕሪል 4፣ 1960 እ.ኤ.አ. ከፈረንሣይ ጋር በተፈረመው የሥልጣን ዝውውር ስምምነት አማካኝ በጁን 20፣ 1960 እ.ኤ.አ. ነጻነቱን አውጀ። በውስጣዊ የፖለቲካ ውዝግቦች ምክኒያት ፌዴሬሽኑ ክሁለት ወር በኋላ ተከፈለ። ሴኔጋልም ነጻነቱን በድጋሚ አውጀ። ሊዎፖልድ ሴንግሆርም የመጀመሪያው ፕሬዘዳንት ሆኖ በኦገስት 1961 እ.ኤ.አ. ተመረጠ። ፕሬዝዳንት ሊዎፖልድ ሴንግሆር ሀገሩን መምራት ከጀመረ በኋላ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማማዱ ዲያ ጋር ባለው አለመስማማት ምክኒያት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ መፈንቅለ-መንግሥት በዲሴምበር 1962 እ.ኤ.አ. ተካሄደ። ይህ መፈንቅለ-መንግሥት ያለ ደም ፍስሻ የከሸፈ ሲሆን ማማዱ ዲያም ታሰረ። ከዛም ሴኔጋል የፕሬዝዳነንቱን ሥልጣን የሚያጠነክር አዲስ ሕገ-መንግሥት አሳለፈች። በ1980 እ.ኤ.አ. ፕሬዝዳንት ሴንግሆር በራሱ ፍቃድ ከሥልጣኑ የወረደ ሲሆን በ1981 እ.ኤ.ኣ. በራሱ በሊዎፖልድ ሴንግሆር የተመረጠው አብዱ ዲዮፍ ፕሬዝዳንት ሆነ። በፌብሩዋሪ 1፣ 1982 እ.ኤ.አ.፣ ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ የሴኔጋምቢያ ኮንፌዴሬሽንን መሠረተች። ከስምንት ዓመት በኋላ ግን በ1989 እ.ኤ.አ. ኮንፌዴሬሽኑ ፈረሰ። ከ1982 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በደቡባዊ ሴኔጋል በካሳማንክ አካባቢ የሚገኙ አማጺዎች ከሴኔጋል መንግሥት ጋር በየጊዜው ተጋጭተዋል። ሴኔጋል ዓለም-አቀፍ ሰላም-አስከባሪ ሃይሎችን በመላክ ትታተወቃለች። አብዱ ዲዮፍ ከ1981 እስከ 2000 እ.ኤ.አ. ድረስ ፕሬዝዳንት ነበረ። በሥልጣን ጊዜው አብዱ የፖለቲካ ተሳትፎን አበረታትቷል፣ መንግሥቱ በኤኮኖሚው ላይ ያለውን ቁጥጥር አሳንሷል፣ እና ሴኔጋል ክውጭ በተለይም ከታዳጊ ሀገሮች ጋር ያላትን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን አጠናክሯል። አብዱ ለአራት የሥራ-ጊዜዎች ፕሬዝዳንት ሆኖ አገልግሏል። በ2000 እ.ኤ.አ. በዓለም-አቀፍ ታዛቢዎች ነጻና ዲሞክራሲያዊ በተባለ ምርጫ የአብዱ ዲዮፍ ተቀናቃኝ አብዱላይ ዋዲ አሸንፎ ፕሬዝዳንት ሆኗል። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ አሣ፣ ጥጥ፣ ጨርቅ፣ ባምባራ ለውዝ (Vignea subterranea)፣ ካልሲየም ፎስፌት ናቸው። ሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ናት። ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ፕሬዝዳንቷ በየአምስት ዓመት የሚመረጥ ሲሆን ከዛ በፊት ደግሞ በየሰባት ዓመት ነበር። ያሁኑ ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ሲሆኑ በማርች 2007 እ.ኤ.አ. እንደገና ተመርጠዋል። \n \nጥያቄ: ሴኔጋል ከጋምቢያ ጋር ተዋሕዳ ፈጥራው የነበረው ኮንፌደሬሽን ስምምንት መቼ ፈረሰ?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ በ1989 እ.ኤ.አ. ነው።", "role": "assistant" } ]
[ { "content": "ከዚህ በታች ያለውን ጽሑፍ በማጣቀስ እባክዎን ለሚከተለው መልስ ይስጡ \nፐርል በክ ፐርል በክ በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ተሸላሚ (1938) ለመሆን የበቃች አሜሪካዊት ደራሲ ናት። በክ ጁን 26 ቀን 1982 ዓ.ም በምእራብ ቨርጂኒያ ሂልዝቦሮ በተባለ ቦታ ተወለደች። ወላጆቿ ፕሬስብቴርያዊ ሚሲዮኖች የነበሩ ሲሆን ብዙውን የሚሲዮን ስራቸውን በቻይና ነው ያሳለፉት። በዚሁ የተነሳ በክ ከልጅነቷ ጀምሮ እንግሊዝኛን ብቻ ሳይሆን ቻይንኛንም አቀላጥፋ ትናገር ነበር። ትምህርቷን በ1914 እንዳጠናቀቀች ወደ ቻይና ነው ያቀናችው። በ1915 የወደፊት ባሏ ከሚሆነውን ከጆን ሎሲንግ በክ ጋር ተገናነች። በ1917 ጋብቻቸውን ከፈጸሙ በኋላ ኑሯቸውን ናንሹ በተባለችው የገጠራማዋ አንህዌ ግዛት አደረጉ። በዚሁ ቆይታዋ ነው ወደፊት የሥነ-ጽሁፍ ስራዋ ጉልላት ለመሆን የበቃውን ስሙር መሬት (The Good Earth) ለተባለው መጽሃፏ የሚሆናትን መረጃ የሰበሰበችው። በክ ጽሁፎቿን ማሳተም የጀመረችው ከ1920ዎቹ ጀምራ ሲሆን አጫጭር ስራዎቿ \"The Nation\"፣ \"The Chinese Recorder\"፣ \"Asia\" እና \"The Atlantic Monthly\" በተሰኙ መጽሄቶች ታትመውላታል። የመጀመሪያው ወጥ ልብ-ወለድ ድርሰቷ (East Wind, West Wind) በ1930 በጆን ዴይ ኩባንያ ታትሟል። የጆን ዴይ ኩባንያ አሳታሚ የነበረው ሪቻርድ ዋልሽ ኋላ ላይ (1935) የፐርል በክ ሁለተኛ ባሏ ለመሆን በቅቷል። በ1931 ጆን ዴይ ኩባንያ የፐርል በክን ሁለተኛ ወጥ ልብ-ወለድ ድርስት የሆነውን ስሙር መሬትን አሳተመ። ይኸው ሥራዋ በተከታታይ በ1931 እና በ1932 ዓ.ም በገበያ ላይ አንደኛ ተፈላጊ ሆኖ ለመዝለቅ የቻለ ሲሆን ለሷም በ1935 ዓ.ም የፑሊትዘር ሽልማት እና የሃዌልስ ሜዳልያ አስገኝቶላታል። ስሙር መሬት በ1937 ዓ.ም በኤም.ጂ.ኤም አማካይነት በፊልም መልክ ተቀናብሮ ለተመልካች ቀርቧል። ከዛ በተከታታይ ሌሎች ድርሰቶችን ለአንባቢ አቅርባለች። በክ በ1938 ዓ.ም በስነ-ጽሁፍ የኖቤል ሽልማትን በመቀበል የመጀመሪያዋ (ሴት) አሜሪካዊት ሆናለች። ፐርል በክ በ1973 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ስትለይ ከ70 በላይ ስራዎቿ ታትመውላታል። መቃብሯም ፔንሲልቬንያ ውስጥ በክስ በተባለው ቀበሌ ይገኛል። \n \nጥያቄ: ፐርል በክ የመጀመሪያ ጋብቻዋን የፈጸመችው መቼ ነው?", "role": "human" }, { "content": "ለጥያቄው መልስ በ1917 ነው።", "role": "assistant" } ]