query_id
stringlengths
32
32
passage_id
stringlengths
32
32
query
stringlengths
1
300
passage
stringlengths
78
13.7k
category
stringclasses
7 values
link
stringlengths
28
740
⌀
source_dataset
stringclasses
3 values
da54815d2460eb1169b867068cb5da9a
1ae0d45982aa378c6d843c1e57120b26
"የ13 ዓመት ልጄን በነጭ ፖሊስ ልትገደል ትችላለህ ማለት ልብን ይሰብራል" ሶማሊያዊቷ እናት በአሜሪካ
ከተቃውሞዎቹ ባሻገር ለጥቁር፣ ቀደምት አሜሪካውያንና ከነጭ ውጭ ላለው ማህበረሰብ ደግሞ ንዴትን ብቻ ሳይሆን ፍራቻንም አንግሷል። በተለይም በነጭ ፖሊሶች እጅ የሚገደሉት ታዳጊዎች ጭምር መሆናቸው ቤተሰቦች ላይ የሚፈጥረው ጭንቀትና ፍራቻ ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ይከብዳል። በማያቋርጥ ፍራቻ ከሚኖሩት መካከል ሶማሊያዊቷ ኢፍራህ ኡድጉን ትገኝበታለች። በኦሃዮ የሳይንስ መምህር ስትሆን ወደ አሜሪካም የሄደችው ገና በአስራ ሁለት አመቷ ነው። የሶማሊያን እርስ በርስ ጦርነት ሽሽት ወደ አሜሪካ ቢያቀኑም ሌላ መከራ ዘረኝነት ተቀብሏቸዋል። በአሁኑ ሰአት የ13 አመት ታዳጊ ልጅ ያላት ሲሆን የዘር ክፍፍል በነገሰበት፣ የነጭ የበላይነት በሚቀነቀንበትና ጥቁሩ ማህበረሰብ መዋቅራዊና የፖሊስ የጭካኔ በትር በሚያርፍበት ሃገር ልጅ ማሳደግ ልብ እንደሚሰብር አልደበቀችም። ቀደምት አሜሪካውያንን ከሃገራቸው በማፈናቀልና በመጨፍጨፍ የተመሰረተችው አሜሪካ ለበርካታ ስደተኞች ህልምም ቅዠትም ትሆንባቸዋለች። ኢፍራህና ቤተሰቦቿ የእርስ በርስ ጦርነቱን ሸሽተው ወደ አሜሪካ ሲመጡ ቢያንስ ደህና እንሆናለን፣ በጦርነት ከመታመስም እንተርፋለን በሚል ነበር። ቢያንስ ልጆቻችንን በተሻለና ደህንነቱ በተጠበቀ ከባቢም እናሳድጋለን የሚል ተስፋን ሰንቀው የነገንም አልመው ነበር፤ ሆኖም በእንዲህ አይነት ስር በሰደደ ዘረኝነት ውስጥ ማሳደግም ቀላል አይደለም። ለኢፍራንም በአሁኑ ወቅት የሰፈነው ዘረኝነት ከዘመናት ሲንከባለል የመጣና የአሜሪካ ታሪክም ዋና አካል መሆኑን ታስረዳለች። "አሁን እየተፈፀሙ ያሉት የፖሊስ ግድያዎች ዝም ብለው በአንዳንድ መጥፎ ፖሊሶች የሚፈፀሙ ሳይሆን ከአገሪቱ ህግ፣ ምስረታ፣ ፖሊሲዎች ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ያላቸው ናቸው። ይህንን ሁኔታ መረዳት ለወላጅም ልብ የሚሰብር ነገር ነው። ልጄን መጠበቅ እንደማልችና ከኔ ቁጥጥር ውጭ ባሉ ሁኔታዎች ጉዳት እንደሚደርስበት ማሰብም ሆነ ህይወቱ ሊቀጠፍ እንደሚችል ማሰብ ከጭንቅላት በላይ ነው" ትላለች። በአሜሪካ ውስጥ በባለፉት በርካታ አመታት እንደ ትሬይቮን ማርቲን የመሳሰሉት ታዳጊ ጥቁሮች በነጭ ፖሊሶች መገደል የነጭና የጥቁር ህፃናት አለም የተለያየ ስለመሆኑ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ለኢፍራንም ይህ ሁኔታ በጣም ያስፈራታል፤ ህፃናት ልጆች ወይም ታዳጊዎች እንደ ህፃን በማይታዩበት ሁኔታ ልጅ ማሳደግ ሌላ ገፅታ አለው። "ልጄ ህፃን እንደመሆኑ መጠን ሌሎችም እንደ ህፃን ያዩታል የሚለው ነገር አይሰራም። እያደገ ነው። ቁመቱም እየረዘመ ነው፤ ይህ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታም ያስፈራኛል። እና ጎረምሳ መምሰሉ ባለው ስርአት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ለኔ እንደ ጥቁር እናት የጥቁር ታዳጊዎች ህይወት ከቁብ በማይቆጠርበት አገር ማሳደግም አስፈሪ ነው" ትላለች። ለታዳጊ ልጇም አሜሪካ እንደ ስርአት ጥቁር ሰዎችን እንደማትወድ፤ ምንም ያላጠፋ ልጅ አንተንም ሊገድሉህ ይችላሉ ብሎ ማስረዳትም ከባድ ነው። ኢፍራን ግን ከልጇ ጋር ይህ ቀላል የማይባለውን ውይይት ማድረግ ይጠበቅባታል። "ይሄ ደግሞ ሌላ ልብ የሚሰብር ጉዳይ ነው። ዘረኝነትን መጋፈጥ እንዲሁም ስለ ዘረኝነትም ሆነ የፖሊስ ጭካኔ ከህፃናት ጋር ማውራት በጣም አሳዛኝ ነው። እንደ ወላጅ እነሱን ለመጠበቅ ማንኛውንም ነገር ማድረግ አለመቻላችንን ስረዳ የካድናቸው ያህል ይሰማኛል። ልጅነታቸውንም ሆነ የልጅነታቸውን ንፅህና መስረቅ ነው። ሌላ ምን አማራጭ አለ ? ለልጄ ስለ ፖሊስ ጭካኔም ሆነ ዘረኝነት ማስረዳት አለብኝ። የ13 ዓመት ልጄን በነጭ ፖሊስ ልትገደል ትችላለህ ማለት ልብን ይሰብራል ግን ምንም እንዳልተፈጠረ ማስመሰል አልችልም" በማለት ለቢቢሲ ተናግራለች። ልጇ የሚኖርበትን አለም እውነታ ገና...
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
9e7aaab8187fef4f7b24195a31202efc
f58dc828e8e54bcc503fe309b08af336
ሲዳማ ቡና በቀጣይ ሳምንት የሚያደርገው ጨዋታ የቦታ ለውጥ እንዲደረግበት ጠየቀ
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ከሚደረጉ ጨዋታዎች አንዱ የሆነው የወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ላይ የቦታ ለውጥ እንዲደረግ ሲዳማ ቡና ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡ በቀጣዩ ሳምንት ሀሙስ ሶዶ ላይ እንዲከናወን የወጣው መርሐ ግብር በስፍራው ተገኝተን ማድረግ አንችልም የሚል ደብዳቤን ማስገባቱን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል። ክለቡ በደብዳቤው ” በሁለቱ ክለቦች መካከል የተፈጠረ ግጭት ባይሆንም ባለፉት ወራት በሲዳማ እና ወላይታ ዞኖች ተነስቶ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ገና የሁለቱ ህዝቦች በእርቅ ሒደት ላይ ስላሉ ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተፈቶ ወደ ሠላማዊ መንገድ እስኪመጣ ድረስ ይህ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲደረግልን እንጠይቃለን።” የሚል ይዘት ያለው ጥያቄ ነው ለፌዴሬሽኑ ያቀረበው። ክለቡ በሁለተኛው ዙር የሚደረገው ጨዋታም የተጋጣሚን አድቫንቴጅ በጠበቀ መልኩ ከሀዋሳ ይልቅ አዲስ አበባ ላይ ቢደረግ የሚል ምክረ ሐሳብ ማቅረቡ ተሰምቷል።
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/42501
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
9af22c753182513e544492223917f297
19894db76bf8c0110c029300ab065b1d
ኢሬቻ የሰላም ሩጫ በአዲስ አበባ ተካሄደ
‘‘ኢሬቻ ለሰላም’’ በሚል ስያሜ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡በአባቶች ምርቃት በተጀመረው ሩጫ ላይ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል፡፡መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ባደረገው የሩጫ ውድድር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ከ15 በላይ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩ ከወንዶች አትሌት በሪሁ አረጋዊ እና ከሴቶች ደግሞ አትሌት ኦብሴ አብደታ የ‘‘ኢሬቻ ለሰላም’’ የጎዳና ላይ ሩጫ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ለአሸናፊዎቹ የዋንጫ፣ የምስክር ወረቀት እና የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡በውድድሩ በወንዶች ኃይለማሪያም ኪሮስ 2ኛ ሲወጣ ደጀኔ ደበላ 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡በሴቶች ደግሞ መስታወት ፍቅሬ 2ኛ አንቻለም ሀይማኖት ደግሞ 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩ በሁለቱም ፆታዎች 2ኛ እና 3ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የ30 ሺህ እና የ20 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ሽልማቱን ለአሸናፊዎቹ አበርክተውላቸዋል፡፡የኢሬቻ የሰላም ሩጫ በዘንድሮው ዓመት በአዲስ አበባ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው የተካሄደው፡፡  
ሀገር አቀፍ ዜና
https://waltainfo.com/am/32752/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
c51e340370b1bfc67d3b1fb370d85aaa
d7533a78252bfbdc1d1f94a4b4fa4a46
ለተሰንበት ግደይ የዓለምን የ5,000 ሜትር ክብረ ወሰን በስፔን ሰበረች
ከዓምናው የዓለም ሻምፒዮና የ10,000 ሜትር ሁለተኝነቷ በኋላ፣  ለተሰንበት ግደይ በ5,000 ሜትር የመም (ትራክ) ላይ ሩጫ የምንጊዜውም እጅግ ፈጣኗ ሴት ሆናለች። ኢትዮጵያዊቷ ለሰንበት፣ ረቡዕ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ባደረገችው አስደናቂ ሩጫ ለ12 ዓመታት በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን በስፔን ቫሌንሽያ ከተማ፣ በ14:06.62  በመሮጥ ነው የዓለምን ክብረወሰን መስበር የቻለችው። ይህ ድንቅ ክንዋኔዋ ነው በጥሩነሽ ዲባባ በ2008 በ14:11.15 ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን ለመስበር የበቃችው።ኦሊምፒክ ቻነልና ራነርስ ወርልድ እንደዘገቡት የመጨረሻዎቹን አምስት ዙሮች ብቻዋን የሮጠችው ለተሰንበት፣ ከውድድሩ ፍጻሜ በኋላ "ይህ የረዥም ጊዜ ሕልሜ ነው፤ በውድድሩም በጣም ተደስቻለሁ!" ብላለች።  "ይህ በጣም ግሩም ነው፡፡ ከዚህ በፊት ጥሩነሽ ዲባባ ሰበረች፤ አሁን ደግሞ እኔ፡፡” ስትልም አክላለች። የ5,000 ሜትር የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር የኢትዮጵያውያን ሯጮች የፈጣን ሯጭነት ውርስን የ22 ዓመቷ ለተሰንበት አስቀጥላለች።ሌላው የምሽቱ ተጨማሪ  የክብረ ወሰን አስደናቂ ክስተት በቀነኒሳ በቀለ በ26:17.53  ለ15 ዓመታት ተይዞ የነበረው የ10,000 ሜትር ሪከርድን ዑጋንዳዊው ጆሹዋ ቼፕቴጊ በ26:11.02 በመፈጸም መስበሩ ነው። ባለፈው ነሐሴ በተደረገው ዳይመንድ ሊግ በ5000 ሜትርም የቀነኒሳን የዓለም ሪከርድ መስበሩም ይታወሳል፡፡
ስፖርት
https://www.ethiopianreporter.com/article/20054
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
2379bf1552703b01d32314d2265580c6
e484d256913d908ad719da8dc56d94e6
ሞ ሳላሕ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች በመሆን ለ2ኛ ጊዜ ተመረጠ
የ26 ዓመቱ አጥቂ ሜዲ ቤናቲያ፣ ካሊዱ ኩሊባሊ፣ ሳዲዮ ማኔ እና ቶማስ ፓርቴይን አሸንፎ ነው ሽልማቱን ያገኘው። "ታላቅ ስሜት ነው፤በሚቀጥለው ዓመትም ለማሸነፍ እፈልጋለሁ። " ሲል ሳላህ ሐሳቡን ለቢቢሲ ገልጿል። • የዘንድሮ የቢቢሲ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ዕጩዎች የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋቾች ባለፈው ዓመት ለሊቨርፑል 52 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 44 ጎሎችን ከማስቆጠርም ባለፈ ቡድኑ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ እንዲደርስ አግዟል። "በእያንዳንዱን ጊዜ ጎሎችን በማስቆጠር ቡድኑ ነጥብ እንዲያገኝ በማድረግ ቡድኑ በሊጉ አናት እንዲቀመጥ እንዳገዝኩ ይሰማኛል. . . ይህ ደግሞ ሁልጊዜ ጥሩ ስሜት ይሰጣል።" ይላል ሳላህ። ሩሲያው የዓለም ዋንጫ ሁለት ጎሎችን ለግብጽ ብሔራዊ ቡድን አስቆጥሯል። ቢቢሲ ዘንድሮ በሽልማቱ ታሪክ ክብረወሰን የሆነ ከ650,000 በላይ ድምፆችን ተቀብሏል። ሳላህ ከናይጄሪያዊው ጄይ-ጄይ ኦኮቻ ቀጥሎ በተከታታይ ዓመት ሽልማቱን ያሸነፈ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። የቀድሞው የቼልሲተጫዋች በቨውሮፓዊያኑ 2017 ከሮማ ወደ ሊቨርፑል ያቀናው። በሮም ቆይታው 15 ጎሎችን አስቆጥሮ 11 ደግሞ ለጎል አመቻችቶ አቀብሏል። በዚህም ቡድኑ ከሰባት ዓመት በኋላ በሴሪአው ሁለተኛው ሆኖ አጠናቋል። ሳላህ የሊቨርፑል ሕይወቱ በድንቅ ሁኔታ ነው የጀመረው። በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 24 ጨዋታዎች19 ግቦችን አስቆጥሯል። ሉዊስ ሱዋሬዝ (2013 -14)፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ (2007-08) እና አለን ሺረር (1979-1996) በአንድ ውድድር ዓመት ካስቆጠሯቸው 38 ጎሎች ጋር እኩል በማስቆጠር ክብረወሰኑን ተጋርቷል። ሞሐመድ ባራክት (2005) እና ሞሃመድ አቡታሪካ (2008) ሽልማቶችን ያገኙ ሌሎች ግብፃውያን ናቸው።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
5e75823de2789e1ffd0ec4f8d3521322
e542b4e62a22981d6d52d86e4ee82908
ወባ ይከላከላል የተባለለት ክትባት ማላዊ ውስጥ ሙከራ ላይ ሊውል ነው
ክትባቱ የሰውነትን የመከላከል አቅም በማጎልበት የወባ ትንኝ የምታመጣውን የወባ ባክቴሪያ ያዳክማል ተብሏል። ከዚህ በፊት በተደረገው ሙከራ መረዳት እንደተቻለው፤ ዕድሜያቸው ከ5-17 ወራት የሆኑ ሕፃናት ክትባቱን ወስደው ከበሽታው መጠበቅ ችለዋል። • በኢትዮጵያ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ 10 ሰዎችን ገደለ ገዳዩን የወባ በሽታ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት የተደረገው ጥረት የተሳካ ቢመስልም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በሽታው ማንሰራራት አሳይቶ ነበር። ዓለም ላይ በወባ ምክንያት ሕይወታቸው ካለፈ ግማሽ ሚሊየን ገደማ ሰዎች መካከል 90 በመቶው አፍሪቃ ውስጥ እንደሚገኙ፤ አብዛኞቹም ሕፃናት እንደሆኑ ጥናት ይጠቁማል። ምንም እንኳ ማላዊ የወባ በሽታን ለመከላከል ሁሉንም ዓይነት መላ ብትጠቀምም ቀንደኛዋ የበሽታው ተጠቂ መሆኗ ግን አልቀረም። በግሪጎሪያን አቆጣጠር 2017 ላይ ብቻ 5 ሚሊዮን የማሊ ዜጎች በወባ በሽታ ተጠቅተዋል። ማላዊን ጨምሮ ኬንያ እና ጋና አርቲኤስኤስ የተሰኘውን የወባ በሽታ ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሞክሩ የተመረጡ ሃገራት ናቸው። ሃገራቱ የተመረጡበት መሥፈርት ደግሞ ወባን ለማጥፋት በየቤቱ አጎበር እስከመዘርጋት ቢደርሱም በሽታው ሊቀንስ አለመቻሉ ነው። • የቢጫ ወባ ካርድ በቦሌ ለሚወጡ ሁሉ ግዴታ ሊሆን ነው? ክትባቱ ለሦስት አሥርት ዓመታት ያህል አሉ በተባሉ ሳይንቲስቶች ሲብላላ የቆየ መሆኑም ተዘግቧል፤ እስካሁንም 1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ወጭ እንደሆነበት ተነግሯል። የክትባቱን ሂደት በበላይነት የሚቆጣጠረው የዓለም ጤና ድርጅት ነው። የክትባቱ የመከላከል አቅም 40 በመቶ ቢሆንም ከሌሎች መከላከያ መንገዶች ጋር በመሆን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ይላል ድርጅቱ። ክትባቱ ለአንድ ሕፃን አራት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን ለሦስት ተከታታይ ጊዜ በየወሩ እንዲሁም የመጨረሻው ከ18 ወራት በኋላ ይወሰዳል። እስከ 2023 ይቆያል የተባለለት ይህ የክትባት ሂደት ማላዊ ውስጥ ከተጀመረ በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኬንያ እና ጋና ላይ የሚቀጥል ይሆናል። • ሃሰተኛ መድሃኒቶችን ለገበያ ያቀረቡ ተፈረደባቸው
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
075e89f075530255841ded001f33b1ff
a3412e503deb2575224467fcc394aa4d
የዓለም ባንክ ለኢኮኖሚ ሪፎርም ከሰጠው ብድር ውስጥ የተወሰነው ለኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ እንዲውል ተወሰነ
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ለማገዝ ከሰጠው 1.7 ቢሊዮን ብር ውስጥ የተወሰነው፣ የኮሮና ወረርሽኝ ጫናን ለመቋቋም እንዲውል ተወሰነ፡፡የኮሮና ወረርሽኝ እያስከተለ ባለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ምክንያት እንቅስቃሴዎች በመቀዛቀዛቸው፣ መንግሥትም ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ያለውን ጥረት አሟጦ እየተጠቀመ በመሆኑ፣ እየገጠመው ያለውን የበጀት ክፍተት ከዓለም ባንክ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ብድር በማዘዋወር መጠቀም እንዲችል ጥያቄ አቅርቧል፡፡የዓለም ባንክ የሰጠው 1.7 ቢሊዮን ዶላር ብድር ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ትግበራ የሚውል በመሆኑና አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ትግበራ ሊገቡ የማይችሉ ፕሮጀክቶች በቀጣይ ዓመት እንዲከናወኑ በማድረግ፣ አሁን የተያዘላቸው በጀት ተተኪ እንደሚሆን ታሳቢ ሆኖ ለመንግሥት የቀጥታ በጀት ድጋፍ እንዲውል መንግሥት ጥያቄ አቅርቧል፡፡በዚህ መሠረት 250 ሚሊዮን ዶላር የኮሮና ወረርሽኝ ጫናን ለመዋጋት በቀጥታ በጀት ድጋፍ ወደ መንግሥት ካዝና እንዲዘዋወር ተጠይቆ፣ በገንዘብ ሚኒስቴርና በዓለም ባንክ መካከል ስምምነት ተፈርሟል፡፡በዚህም መነሻ ስምምነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በመጀመርያ ንባብ እንዲፀድቅ ተደርጓል፡፡ ይህ 250 ሚሊዮን ዶላር ከዚህ ቀደም ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በብድርና በዕርዳታ ከተገኘው 1.7 ቢሊዮን ዶላር ላይ ተቀናሽ ተደርጎ፣ በአዲስ ዓላማ በበጀት ድጋፍ መልክ በአፋጣኝ በአንድ ዙር ፈሰስ የሚደረግ መሆኑንም የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህ ሁኔታ የዓለም ባንክን ይሁንታ አግኝቶ ከፀደቀው 250 ሚሊዮን ዶላር በተጨማሪ፣ በተመሳሳይ 500 ሚሊዮን ዶላር እንዲዘዋወርለት መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን የገንዘብ ሚኒስቴር ሰሞኑን ገልጿል፡፡
ቢዝነስ
https://www.ethiopianreporter.com/article/19274
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
3599f8f42c5148e677134614af290ac2
a869cd5242c61ccc7e33df0808c37381
የሱዳን ወታደራዊ ምክርቤት እና የተቃዋሚዎች ጥምረት ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ላይ ከስምምነት መድረሳቸው ተነገረ
የሱዳን ወታደራዊ ምክርቤት እና የተቃዋሚዎች ጥምረት ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ላይ ከስምምነት መድረሳቸው ተነገረሱዳንን እያስተዳደረ ያለው ወታደራዊ ምክር ቤትና ዋነኛው የተቃዋሚዎች ጥምረት በሀገሪቱ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት በር ይከፍታል በተባለለት ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ላይ ከስምምነት ደርሰዋል ተብሏል።ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ መረጋጋት የተሳናት ሱዳን፤ወታደራዊው ምክር ቤት ስልጣኑን ከተቆናጠጠ በኋላም የሲቪል መንግስት ይመስረት በሚል ተቃዋሚዎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ በመቆየታቸው መረጋጋት ተስኗት ቆይቷል።በዚህም ምክንያት አገሪቷን እያስተዳደረ ያለው ወታደራዊ ምክር ቤቱና ዋነኛው የተቃዋሚዎች ጥምረት ከስምምነት ለመድረስ በርካታ ውይይቶችን ቢያደርጉም ሳይሳካ መቆየቱ ይታወሳል፡፡አሁን ግን ሁለቱ ሐይሎች የሽግግር መንግሥት ለመመስረት በር ይከፍታል በተባለለት ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ ላይ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪው ሞሀመድ ሀሰን ሌባት ስምምነቱን ይፋ ያደረጉ ሲሆን፤ ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል ተብሏል፡፡በሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌው ላይ እየተካሄደ የነበረው ድርድር በመራዘሙ በሀገሪቱ የተከሰተው ግጭት መቋጫ እንዲያጣ አድርጎት መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ሲጠበቅ የነበረው ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌው ላይ ከስምምነት መደረሱ እንደተሰማም የሱዳን ጎዳናዎች ደስታቸውን በሚገልጹ ዜጎች መሞላቱ ተዘግቧል።ሰነዱ ባለፈው ወር በወታደራዊ ምክርቤቱና በተቋዋሚዎች መካከል የሶስት አመት የሽግግር መንግስት ለመመስረት የተቀመጠውን ስምምነት ይዘረዝራል፡፡ዘገባው የቢቢሲ ነው።
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/33316/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
d979f985c8c03ed5834715b86b05a141
d1a583561ed32ab1d03a20f02d4dbdcd
የዱር አራዊት
የዱር ህይወት ወይም wildlife የሚባለው ማንኛውንም ለማዳ ያልሆኑ እንስሳት፣ እጽዋት እና ሌሎች ጥቃቅን ፍጥረቶችን ያጠቃልላል። ከዚህ ውስጥ ነው እንግዲህ ለማዳ ያልሆኑትን እንስሳት ለይተን የዱር እንስሳ የምንላቸው። እነዚህ እንስሳቶች በሰው ልጅ የሂዎት ዘመናቶች ሲጠበቁ ቆይተዋል። ይህም ለከባቢ አየር እና አካባቢያዊ ጤንነት አሉታዊም አወንታዊ አስተዋጽኦዎች አሉት።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
607f9a06bb55a689c087d80c8e3a64b6
c03f9cbfaea616f1a528b4983555f27a
ደቡብ ኮሪያ ፣ ሴንጋፖርና ቻይና ሁለተኛ ዙር ኮሮናቫይረስ እያጠቃቸው ካሉ የእስያ አገራት መካከል ናቸው። ይህ በአገራቱ እየታየ ያለው ሁለተኛ ዙር ኮሮናቫይረስ ከውጭ የመጣ እንደሆነ ተገልጿል።
የእስያ አገራት በሁለተኛ ዙር ኮሮናቫይረስ እየተጠቁ ነው\nየቫይረሱ መነሻ የሆነችው ቻይና እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ የመዘገበችው ምንም ዓይነት አዲስ የኮሮናቫይረስ ሕሙም የለም። ነገር ግን በቅርቡ ከውጭ ወደ ቻይና የገቡ 34 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል። ደቡብ ኮሪያም ከትናንት እስከ ዛሬ 152 አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተገኙባት ሲሆን ከነዚህ ምን ያህሉ ከውጭ የመጡ ናቸው የሚለው አልታወቀም። በትናንትናው እለት ሴንጋፖር ደግሞ 47 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ያገኘች ሲሆን ከእነዚህ 33 የሚሆኑት ከውጭ የመጡ ናቸው ተብሏል። • የኮሮናቫይረስ በአዲስ አበባ ሆቴሎች ላይ ያጠላው ስጋት • በኬንያ ስለኮሮናቫይረስ ሃሰተኛ መረጃ ያሰራጨው ግለሰብ ታሰረ • 'ኮሮናቫይረስ አለብህ' በሚል ቡጢ የቀመሰው የኦክስፎርድ ተማሪ በሌላ በኩል በቻይና ስምንት ሞት የተመዘገበ ሲሆን ሁሉም ሞቶች ኮሮናቫይረስ በተቀሰቀሰባት ሁቤ ግዛት ውሃን ከተማ የተመዘገቡ ናቸው። ሶስቱም አገራት ቫይረሱን በመከላከልና ስርጭቱን በመቆጣጠር ረገድ ውጤታማ እየሆኑ የነበረ ቢሆንም ከእነዚህ አገራት ውጭ ቫይረሱ እየተሰራጨ ያለበት ፍጥነት የአገራቱን ስኬት መና እንዳያስቀረው ከፍተኛ ስጋት አለ። አሁን ትልቁ ስጋት ያለው አውሮፓና አሜሪካ ላይ በመሆኑ ትኩረት ያለውም እነሱ ላይ ሆኗል። ነገር ግን በተጠቀሱት የእስያ አገራት ላይ እየታየ ያለው አዳዲስ ታማሚ እስያም አውሮፓና አሜሪካ ካሉበት ደረጃ ብዙ ሩቅ እንዳልሆነች የሚያሳይ ነው። የማሌዥያ የጤና ሚኒስትር ኑር ሂሻም አብዱላ ዜጎቻቸው ከቤት ሳይወጡ ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን እነዲጠብቁ ለምነዋል። ማሌዥያ በቫይረሱ 710 ሰዎች መያዛቸው ታውቋል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
5e0bfa9953e4ddadc0d92521b353ec58
45f5c885f66cd03ac033f76f6bc4f548
የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በሥስት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 12/2013 (አብመድ) 2 ሺህ 160 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ በሥስት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ( አስታውቀዋል።የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ እንዳሉት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2025ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚገነባው ኢኮኖሚ 20 ሺህ ሜጋ ዋት ኃይል እንደሚያስፈልገው በስትራቴጂክ ዕቅድ ተቀምጧል። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ ዕቅድም ተይዟል፤ ከዚህ አንጻር የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በሶስት ዓመት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።ግድቡ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘውን የጊቤ ሦስት ውሃ የሚጠቀም በመሆኑ 6 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሊትር ውኃ ብቻ እንዲይዝ ተደርጎ እንደሚገነባና ይህም ግድቡን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ዕድል ይሰጣል ነው ያሉት።ግድቡ “በገበታ ለሀገር” የኮይሻ ፕሮጀክት መካተቱን ጠቅሰው፤ የግድቡ በፍጥነት መጠናቀቅ አካባቢውን የጎብኝዎች መዳረሻ በማድረግም ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።የፕሮጀክቱ የኮንትራት ስራዎች ተቆጣጣሪ እዩኤል ሰለሞን እንደተናገሩት በእስካሁን ሂደት የውኃውን ተፈጥሯዊ አቅጣጫ ማስቀየርን ጨምሮ መሠረታዊ የቁፋሮ ሥራዎች ተጠናቀዋል፤ የማስተንፈሻ ግንባታ ቁፋሮው ከግማሽ በላይ መከናወኑንም አክለዋል። ።ዋናው ግድብና የኃይል ማመንጫው በተለያዩ ቦታዎች መኖራቸው አንደኛው ግንባታ ሌላኛውን ሳይጠብቅ በተመሳሳይ ጊዜ እንዲከናወኑ ዕድል ይሰጣል ብለዋል።የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በጊቤ-ኦሞ ወንዝ ቀጣና ከሚገኙ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች አራተኛው ነው።ለአራት ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረው የኮይሻ ኃይል ማመንጫ የግንባታ ስምምነቱ የተፈረመው በመጋቢት 2008 ዓ.ም ነው።ኢዜአ እንደዘገበው የፕሮጀክቱ አሁናዊ የግንባታ አፈፃፀም 39 በመቶ ደርሷል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.amharaweb.com/%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%8b%ad%e1%88%bb-%e1%8a%83%e1%8b%ad%e1%88%8d-%e1%88%9b%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%ab-%e1%8d%95%e1%88%ae%e1%8c%80%e1%8a%ad%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%88%a5%e1%88%b5%e1%89%b5/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
c17663cfaa5940f907c1eed92b795e17
7b4e3193b095bc98c38d246bde85c929
ትልቅ ራዕይ የሰነቁ መኪና አጣቢዎቹ
በርካታ አረንጓዴ ዩኒፎርም የለበሱ ወጣቶች ጥቅጥቅ ባለ የባህር ዛፍ ደን ውስጥ ስንመለከት፣ ከትምህርት ቤት የፎረፉ ተማሪዎች እንጂ መኪና አጣቢዎች አልመሰሉንም፡፡ ወደ ቦታው ቀረብ ስንል ግን ተረኞቹ መኪና አጣቢዎች ደኑ ስር አረፍ ካሉት ዩኒፎርም ለባሾች ጋር ተመሳሳይ የደንብ ልብስ የለበሱ መሆናቸውን አስተዋልን፡፡ እነዚህ ወጣቶች “ይገርማል የመኪና” እጥበት አባላት ናቸው፡፡ ከስምንት ዓመት በፊት ትምህርቱን እስከ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀው ወጣት ስንታየሁ አየለ፤ መንገድ ላይ መኪና በማጠብ ነው ሥራ የጀመረው። ትንሽ ቆይቶም ሌላ ልጅ ተጨመረ፡፡ነገር ግን መኪናው የታጠበበት ውሃና ዘይት አካባቢን በመበከል ችግር ፈጠረ፡፡ የአካባቢው ፖሊሶችም ስንታየሁና ጓደኞቹን ማባረርና መያዝ ሥራቸው ሆነ፡፡ ወጣቶችም እየታሠሩ መፈታት የዕለት ተዕለት ሥራቸው እስኪመስላቸው ተደጋገመ፡፡ “በወቅቱ እኛ ብር ማግኘታችንን እንጂ የመኪና እጣቢው ጉዳት እንዳለው አላሰብንም ነበር” ይላል የማኅበሩ መስራች ወጣት ስንታየሁ አየለ፡፡ በመንገድ ላይ የመኪና እጥበት የተነሳ ታስረው በከባድ ማስጠንቀቂያ ከተፈቱ በኋላ፣ ስንታየሁና ጓደኞቹ ሥራ ፈተው መቆየታቸውን አጫውቶኛል፡፡ “ምን ልሥራ እያልኩ ሳሰላስል ለመኪና እጥበቱ ለምን መፍትሔ አልፈልግም የሚል ሃሳብ በአዕምሮዬ ሽው አለ” ይላል፡፡ ይኼኔ ነው “Water recycling from Car Washing” የተሰኘ ባለ 23 ገጽ ፕሮፖዛል ጽፎ ለፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ያስገባው። ባለስልጣኑ ፕሮጀክቱን አገላብጦ ከተመለከተ በኋላ፣ ባለሙያ በመመደብ በፕሮፖዛሉ ላይ መጠነኛ ማስተካከያ ተደርጐ ወደ ሥራ እንዲገቡ አሁን የሚሠሩበትን አንድ ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ለሙከራ እንደተሰጣቸው ወጣቱ ይናገራል፡፡ በዚሁ መሠረት በ1999 ዓ.ም “ይገርማል የመኪና እጥበት አገልግሎት” ተመሠረተ፡፡ፕሮጀክቱ ውሃን በማጣራት መላልሶ መጠቀም ሲሆን ይህ የመኪና እጥበት አገልግሎት አዲሱ ገበያን አልፎ በሱልልታ መንገድ በተለምዶ ድልበር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ላይ ይገኛል፡፡ ወጣት ኃይለሚካኤል ላንቴ በ“ይገርማል የመኪና እጥበት አገልግሎት” ሠራተኛ ነው፡፡ ሥራውን ከጀመረ ሁለት ዓመት ሆኖታል፡፡ “ተወልጄ ያደግሁት ጅሩ የሚባል አገር ነው፡፡ ሥራ ፍለጋ አዲስ አበባ ስመጣ ሰዎች ከስንታየሁ ጋር አስተዋወቁኝ” የሚለው ኃይለሚካኤል፤ ምንም እንኳን ከዚያ በፊት መኪና አጥቦ ባያውቅም ለአንድ ሳምንት ያህል በተግባርና በቪዲዮ የተደገፈ ስልጠና ወስዶ አሁን ጐበዝ መኪና አጣቢ ለመሆን መቻሉን ይናገራል፡፡ “ስልጠናው መኪና ማጠብ ብቻ አይደለም” የሚለው ወጣቱ፤ ስለ መልካም ስነምግባር፣ ስለ ደንበኛ አያያዝና መስተንግዶ፣ በሥራ ላይ ስለመተባበርና ስለእርስ በእርስ ተግባቦት ስንታየሁ እንዳሠለጠናቸው ይናገራል፡፡ “በአሁኑ ሰዓት የምፈልገውን ካደረግሁ በኋላ የተረፈኝን ብር ስንታየሁ ባስተማረኝ መሠረት እየቆጠብኩ አራት ሺህ ብር ያህል አጠራቅሜያለሁ” ብሏል፡፡በሁለት አባላት የተመሠረተው ማኅበር፣ በአሁኑ ወቅት 54 አባላት ያሉት ሆኗል፡፡ በየቀኑም በርካታ መኪኖች ያጥባሉ፡፡ ውሃን እያጣሩ መልሶ በመጠቀም ዘዴ መኪኖች ሲታጠቡ የሚወርደው ቅባትና ዘይት አንድ ቦታ ተንሳፎ ይቀራል፤ ጭቃው ይዘቅጣል፤ ውሃው ተመልሶ ወደማጣሪያው ይገባና ቢያንስ ለስምንት ዙር አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ወጣቶቹ መኪና የሚያጥቡበት ውሃ እጅግ ኩልል ያለና ንፁህ ሲሆን ስምንት ጊዜ መኪና ታጥቦበታል ብሎ ለማመን ያስቸግራል፡፡ የማህበሩ መስራች ወጣት ስንታየሁ እንዳጫወተን፤ ቦታውን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከወሰዱ በኋላ፣ ከአዲስ ብድርና ቁጠባ 10ሺህ ብር በመበደር የማጣሪያውን ዝርጋታ አካሄዱ፡፡ “ወደ አካባቢው የሚለቀቅ አንዳች ቆሻሻ የለም” ይላል ወጣት ስንታየሁ፡፡ ሌላው ቀርቶ ከመኪናው የሚወጣው ዘይትና ቅባት በሊትር ሦስት ብር ከሰባ አምስት ሳንቲም ይሸጣል፡፡ “እንዴት?” የሚል ጥያቄ አነሳሁ፡፡“የጠለለውን ዘይትና ቅባት በአብዛኛው የሚገዙኝ ኮንስትራክሽን ሥራ ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ ሻወር ቤት ያላቸውም ይወስዱታል” የሚለው የፕሮጀክቱ ጠንሳሽ፤ “የኮንስትራክሽን ሠራተኞቹ ፓኔል ሲሰሩ ሲሚንቶ ልክክ አድርጐ እንዳይዝባቸው የተቃጠለውን ዘይትና ቅባት ይቀቡታል፡፡ ባለሻወር ቤቶቹ ደግሞ በዚሁ ዘይት ላይ ዲናሞ ገጥመው ውሃ ያሞቁበታል” ብሏል፡፡ በስፍራው በመኪና እጥበት ሥራ ላይ ተፍ ተፍ ሲል ቆይቶ ፋታ ሲያገኝ ያናገርኩት ወጣት ኃይሌ በየነ፤ ሥራ ከጀመረ አራት ዓመት ሆኖታል፡፡ ከመኪና እጥበት ጋር የተዋወቀው በዚሁ ስፍራ ነው፡፡ ላለፉት አራት ዓመታት መኪና ሲያጥብ ጐን ለጐን መንጃ ፈቃድ ለማውጣት ያደረገው ጥረት ተሳክቶለታል። “ስራው ደስ ይላል፣ የሠራ ሰው የሚያገኝበት ነው። እኔም ከመሰረታዊ ፍላጐቴ አልፌ መንጃ ፈቃድ አውጥቻለሁ፡፡” የሚለው ኃይሌ፤ በቀጣይ ወደ ሹፍርና ሙያ ለመግባት እቅድ አንዳለው ይናገራል፡፡ “እዚህ ከምትመለከቻቸው ውስጥ ስምንት ወጣቶች መንጃ ፈቃድ አውጥተዋል፡፡የማታ ትምህርት የሚማሩም አሉ” ይላል ሊቀመንበሩ ስንታየሁ፡፡ የመኪና እጥበት ዓለም አቀፍ ሥራ እንደሆነ በፅኑ የሚያምነው ስንታየሁ፤ “በእኛ አገር ለመኪና እጥበትና አጣቢ የሚሰጠው ግምት ዝቅተኛ ቢሆንም እኛ ግን የሰውን አመለካከት የሚቀይር ሥራ እየሰራን ነው” ብሏል፡፡ መኪና ከሚያጥቡት ሠራተኞች ለየት ያለ የደንብ ልብስ ለብሷል፡፡ ደብተርና እስክሪብቶ ይዞ ዙሪያውን ይንጐራደዳል። ከሁኔታው መኪና አጣቢ እንዳልሆነ ብረዳም የማህበሩ ሠራተኛ መሆኑ ግን አልጠፋኝም፡፡ ተሾመ ጠርዝነህ ይባላል፡፡ እርሱም በስፍራው ለአምስት ዓመት ሰርቷል፡፡ ከመኪና አጣቢነት ተነስቶ የሠራተኞቹ ሱፐርቫይዘር ሆኗል፡፡ ከጅሩ የመጡ ጓደኞቹ ጠቁመውት መኪና እጥበቱን የተቀላቀለው ተሾመ፤ “አገሬ እያለሁ ትምህርቴን አቋርጬ ቦዘኔ ነበርኩ” ብሏል፡፡ ያቋረጠውን ትምህርት በማታ ቀጥሎ አሁን ስምንተኛ ክፍል ደርሷል፡፡ ሁሉም ተፍ ተፍ ይላል፣ ይጣደፋል፣ ግማሹ ያጥባል ግማሹ ይወለውላል፣ ግማሹ የሞተሩን ፓምፕ ይቆጣጠራል፡፡ መኪናው በሚታጠብበትና ውሃው በሚጣራበት ቦታ ዙሪያ በሚወርደው ውሃ የሚበቅል ጐመን፣ ቃሪያ፣ ድንች፣ ቆስጣና መሰል የጓሮ አትክልቶችን ተመለከትኩና ጠየቅሁት። “እነዚህ አትክልቶች ለሽያጭ የሚውሉ ሳይሆኑ ሠራተኞች አብስለው እዚሁ የሚጠቀሟቸው ናቸው” የሚለው ስንታየሁ፤ ውሃው ይሄን ያህል ጤናማ እንደሆነ አጫውቶኛል፡፡የማኀበሩ ጸሐፊ የሆነው ወጣት ብሩክ ተስፋዬ፤ ከCPU ኮሌጅ በአካውንቲንግ ከተመረቀ በኋላ በ “ይገርማል የመኪና እጥበት” በጸሐፊነት መቀጠሩን አጫውቶኛል፡፡ “መኪና እጥበት ቤት ነው የተቀጠርኩ ስላቸው ቤተሰቦቼ ደስተኛ አልነበሩም” ያለው ብሩክ፤ መጥተው ስፍራውን ከጐበኙ በኋላ ሐሳባቸውን እንደቀየሩ አጫውቶኛል፡፡ “እዚህ ስፍራ ተቀጥሬ ደሞዝ ከመቀበል ባለፈ ከስንታየሁና ከባልደረቦቹ በርካታ ቁምነገሮችን ተምሬያለሁ” የሚለው ወጣት ብሩክ፤ ከደሞዙ ላይ በወር 300 ብር እንደሚቆጥብ፣ ከጸሐፊነት ሥራው በተጨማሪ አስፈላጊ በሆነ ቦታ ሌሎቹን እንደሚያግዝ አጫውቶኛል፡፡ ወደ ማጣሪያው ጠጋ ብለን ስንመለከት የተለያዩ ሂደቶችን አስተዋልን፡፡ ስፖንጅ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ጠጠሮች፣ የተለያዩ በቱቦ የተገናኙ ፕላስቲክ ጋኖች ይታያሉ፡፡ አጠቃላይ የውሃ ማጣሪያ ዘዴው የአረቄ አወጣጥን (ዴስትሌሽን ሲስተምን) ይመስላል፡፡ ከዚህ በመነሳት ስለ ጠጠሮቹ ዓይነትና ከየት እንደተገኙ ጠየቅሁት። “ጠጠሮቹ River Gravel” ይባላሉ፡፡ የገፈርሳና የለገዳዲ ውሃ የሚጣራባቸው ናቸው፤ ብዙ ዓይነትና ደረጃ ቢኖራቸውም በመኪና እጥበቱ ስምንቱን ዓይነት ብቻ ነው የምንጠቀምባቸው” ብሏል፡፡“የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ሰሜን ቅርንጫፍ፣ እኛን ለማበረታታት በነፃ ነው የሰጡን” ያለው ስንታየሁ፤ እነዚያን ቁሶች በነፃ ባያገኙትና እንግዛ ቢሉ በጣም ውድ መሆኑንም ጠቁሞናል፡፡ አንዱ ካሬ ጠጠር ከ560 ብር በላይ ዋጋ ሲኖረው፣ ለውሃው ማጣሪያ ወደ 60 ካሬ ጠጠር ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን የውሃና ፍሳሽ ሰሜን ቅርንጫፍ ሃላፊዎች በስፍራው ተገኝተው ከጐበኟችው በኋላ፣ በሥራው በመደሰት ጠጠሮቹን በነፃ ሰጥተዋቸዋል፡፡ በዚህ ሥራ ውስጥ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ አካባቢን ከብክለትና ውሃን ከብክነት ይከላከላል፡፡ ደረጃውን የጠበቀ የመኪና እጥበትና ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ማስገኘቱም ሌላው ጥቅም ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ በብዙ የጽዳት ጉድለቶች የተጨናነቀች ከተማ መሆኗን የሚጠቅሰው ስንታየሁ፤ ጭንቀቷን ከሚጨምሩባት አንዱ የመንገድ ዳር የመኪና እጥበት እንደሆነ ይናገራል፡፡ በዚህም ዙሪያ ከፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር ውሃን በማጣራት መኪና ማጠብ ለሚፈልጉ ማህበራት ወይም ግለሰቦች ፕሮጀክቱን በነፃ ለመስጠትና በስፍራው እየተገኘ ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን ይናገራል፡፡ እስካሁን ቦሌ ክፍለ ከተማና አቃቂ አካባቢ ለሚገኙ ሁለት የመኪና እጥበት ማህበራት፣ ፕሮጀክቱን በነፃ ከመስጠቱም ባሻገር የምክር አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አጫውቶኛል፡፡ሪሳይክል እየተደረገ ጥቅም ላይ ስለሚውለው ውሃ ደህንነት ጥያቄ ባነሣሁ ጊዜ፣ አንዱን ሠራተኛ ጠርቶ በውሃው ፀጉሩን እንዲታጠብ አድርጐ ከማሳየቱም በላይ፣ ማኅበሩ ለ12 ጊዜ የውሃ ደህንነት ማረጋገጫ ያገኘበትን ሠርትፍኬቶች አሳይቶኛል፡፡ “ጉዳዩን ቀደም ሲል አስበንበታል፡፡ ለዚህም ፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በየዓመቱ የውሃውን ናሙና እየፈተሸ ማረጋገጫ ይሰጠናል። 12ኛው ደብዳቤ (ማረጋገጫ) የ2005 ዓ.ም ፍተሻ የተደረገበት ነው” ሲል አስረዳኝ፡፡ “መጀመሪያ ውሃውን ስድስት ዙር በማጣራት እንጠቀም ነበር፡፡ አሁን ወደ ስምንት ዙር ከፍ አድርገን እየተጠቀምን ነው” ያለው ስንታየሁ፤ በቀጣይ 40 ዙር ሪሳይክል ለማድረግ አዲስ ፕሮጀክት እየቀረፁ ይገኛሉ፡፡ “በዚህ ዘርፍ ሌላ የሚፎካከረን ድርጅት ቢመጣ እኛ ወደተሻለ አዲስ ፕሮጀክት እናድግ ነበር” ብሏል፡፡ በቦታው የተባበሩት ፔትሮሊየም ምርቶችና ዕቃዎች በስፋት አይተን ጥያቄ አነሳን፡፡ ይህን ስራ ሲጀምሩ የተለያዩ ድጋፍ እንዲደረግላቸው በየማደያዎቹ ፕሮጀክቱን ቢያስገቡም ምላሽ የሚሰጥ ጠፋ፡፡ተስፋ ሳይቆርጡ ወደተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም ሄዱና ያልጠበቁትን ምላሽ አገኙ፡፡ እንደ ማህበሩ ሊቀመንበር ገለፃ፣ የተባበሩት ብሔራዊ ፔትሮሊየም ኩባንያ ኃላፊዎች ፕሮጀክቱን እንዳዩት ወደ ስፍራው በመምጣትና በመጐብኘት የካምቢዮ ዘይት ማጠጫ ማሽንን ጨምሮ 380 ሺህ ብር ግምት ያላቸው ዘመናዊ መሣሪያዎችን በነፃ እንደለገሷቸው ጠቅሶ፤ “አንዲህ አይነት ፈጣን ምላሽ ለሰጡን ወገኖች ከፍተኛ ምስጋናና አክብሮት አለን” ብሏል። ኩባንያው ዘመናዊ መሣሪያዎችን በነፃ ከመስጠት አልፎ እስከ መቶ ሺህ ብር የ“bp” የሞተር ዘይቶችን ሸጠን ትርፉን እንድንጠቀምና ዋናውን እንድንመልስ ሲሰጡን ምንም ማስያዣ አይጠይቁንም ይላል ስንታየሁ፡፡ በስፍራው ተገኝተን ለመረዳት እንደቻልነው “ይገርማል የመኪና እጥበት ድርጅት” ትልቅ ፕሮጀክት ነው፡፡ በቀን በትንሹ 120 መኪና በዛ ሲባል ደግሞ 180 መኪና ያጥባል፡፡ድርጅቱ በ10ሺህ ብር ካፒታል ሥራ የጀመረ ቢሆንም በአሁኑ ሠዓት ካፒታሉን ወደ 1 ሚሊዮን ብር ማሣደጉን ወጣት ስንታየሁ አየለ አስረድቶናል። ለወደፊት ትልቅ እቅድ አላቸው - እነዚህ መኪና አጣቢ ሠራተኞች፡፡ 54ቱን ሠራተኞች በእጥፍ በማሳደግ፣ 30 ደቂቃ ይፈጅ የነበረውን የአንድ መኪና እጥበት ወደ 15 ደቂቃ የማሳጠርና የደንበኞችን ጊዜ የመቆጠብ ሐሳብ አላቸው፡፡ “የትኛውም ነገር በገንዘብ ይገዛል፤ ጊዜን በገንዘብ ማግኘት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ደንበኞችም እኛም ጊዜያችንን መጠቀም አለብን” ባይ ነው፤ ወጣት ስንታየሁ፡፡ ወጣቱ በመጨረሻም ለስራቸው መቀናት ትልቅ ድጋፍ ያደረጉ ድርጅቶችንና ግለሠቦችን አመስግኗል፡፡
ቢዝነስ
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=12307:%E1%89%B5%E1%88%8D%E1%89%85-%E1%88%AB%E1%8B%95%E1%8B%AD-%E1%8B%A8%E1%88%B0%E1%8A%90%E1%89%81-%E1%88%98%E1%8A%AA%E1%8A%93-%E1%8A%A0%E1%8C%A3%E1%89%A2%E1%8B%8E%E1%89%B9&Itemid=240
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
fd0d46a3fa938a07c4daf41024e0c44c
fdc0ec556871f639931d951b0875e272
ሰሜን ኮሪያ በኒውክሌር ጉዳይ
ዛሬ የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የታቀደው የጦር ልምምድ ባለፈው ዓመት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እና ኪም ጆንግ ኡን ሲንጋፖር ውስጥ የደረሱትን ሥምምነት የሚጥስ ነው ማለቱን የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት ባወጣው መገለጫ አስታውቋል።
ዓለም አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/us-south-korea-drills-could-impact-nuclear-talks-say-north--7-16-2019/5002595.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
a0d4e7a4673e68a73daef65d84b389e5
c21291242330d4a6f941f59011eab260
ባለፉት 24 ሰዓታት 959 የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 735 ሰዎች አገግመዋል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተካሄደ 8 ሺህ 101 የላብራቶሪ ምርመራ 959 የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።በዚህ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 78 ሺህ 819 ደርሷል።ባለፉት 24 ሰዓታት ከቫይረሱ ምክንያት የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 222 መድረሱ ተነግሯል።እንዲሁም በ24 ሰዓታት ውስጥ 737 ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 33 ሺህ 60 ዶክተር ሊያ አስታውቋል።በአሁን ወቅት 44 ሺህ 535 ሰዎች ቫይረሱ የሚገኘባቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 285ቱ ፅኑ ህሙማን መሆናቸው ተጠቁሟል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%89%a3%e1%88%88%e1%8d%89%e1%89%b5-24-%e1%88%b0%e1%8b%93%e1%89%b3%e1%89%b5-959-%e1%8b%a8%e1%8a%ae%e1%88%ae%e1%8a%93-%e1%89%ab%e1%8b%ad%e1%88%a8%e1%88%b5-%e1%88%b2%e1%8c%88%e1%8a%9d%e1%89%a3%e1%89%b8/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1e15610a5aa732e5d7f70d3753f16238
b685c9b0b91a15cfa0c75f5a2469487e
የ”ስቴይ ኢዚ” ሆቴል ባለቤት ሆቴሉን ለኮሮናቫይረስ ለይቶ ማቆያ እንዲሆን አበረከቱ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) በአዲስ አበባ የሚገኘው “ስቴይ ኢዚ” ሆቴል የኮሮናቫይረስ ምልክት ለሚታይባቸው የህክምና ባለሙያዎች ለይቶ ማቆያ እንዲሆን የሆቴሉ ባለቤት ወይዘሮ ህይወት አየለ ትናንት ለኮቪድ-19 ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረክበዋል። እንደ አገር የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ሆቴሉ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር እስኪቻልና መደበኛ እንቅስቃሴ እስኪጀመር ለለይቶ ማቆያ እንዲውል መፍቀዳቸውንም ገልጸዋል። ኮሚቴውን ወክለው ሆቴሉን የተረከቡት ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም በበኩላቸው ፣ ባለሃብቷ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው ለሌሎችም አርአያ እንደሚሆን ገልጸዋል። አዲስ ዘመን መጋቢት 26/2012
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=29741
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
e3f2c37104d1c189ff084c52aa8ec791
2e1e378d50392ebb932589abebe662f3
ዋልያዎቹ ዛሬ አመሻሽ ቀለል ያለ ልምምድ ባህር ዳር ላይ ሰርተዋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2019ኙ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ 5 ከኬንያ፣ ጋና እና ሴራሊዮን ጋር ተደልድሎ የምድብ ጨዋታውን እያከናወነ ይገኛል። ባህር ዳር ላይ ከኬንያ ጋር ለሚያደርገው የምድቡ ሶስተኛ ጨዋታም ከዛሬ ጀምሮ ልምምድ ማከናወን ጀምሯል።ቡድኑ ዛሬ ረፋድ ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በአምበሉ እና አሰልጣኙ አማካኝነት መግለጫ ከሰጠ በኋላ በቀጥታ ጨዋታው ወደሚደረግበት ባህር ዳር ያቀና ሲሆን ልምምዱንም ዛሬ ጀምሯል። ብሔራዊ ቡድኑ ከ45 ደቂቃዎች የዓየር ላይ ጉዞ በኋላ ባህር ዳር እንደደረሰ በከተማው ነዋሪ እና የስፖርት ቤተሰብ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን ከአቀባበሉ በኋላም በማረፊያነት ወደመረጠው ብሉ ናይል ሆቴል አቅንቷል። የቡድኑ ተጨዋቾች መጠነኛ እረፍት ካደረጉ በኋላም ከ11:30 ጀምሮ የሪከቨሪ ልምምዶችን ባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም አጠገብ በሚገኘው የልምምድ ሜዳ አከናውነዋል። በልምምዱ ከፋሲል ከነማ የተመረጡት ሶስቱ ተጨዋቾች (ሙጂብ ቃሲም፣ ሽመክት ጉግሳ እና አምሳሉ ጥላሁን) እንዳልተገኙ የተሰማ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ቡድኑን ተቀላቅለው መደበኛ ልምምዳቸውን እንደሚሰሩ ለማወቅ ተችሏል። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ (ኢንስትራክተር) ከቡድኑ ጋር ወደ ባህር ዳር ከማቅናታቸው በፊት በሰጡት አስተያየት የቅዱስ ጊዮርጊሶቹ ሳላዲን በርጌቾ፣ አስቻለው ታመነ እና በኃይሉ አሰፋ ከጉዳት እና ከጨዋታ መደራረቦች ጋር በተያያዘ ከቡድኑ ጋር አብረው እንደማይጓዙ በተናገሩት መሰረት ሶስቱም በልምምዱ ያልተገኘ ሲሆን ነገ ምሽት 11 ሰዓት በሚወጣ የኤም አር አይ ውጤት መሰረት ቀጣይ ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ያላቸው እጣ ፈንታቸው እንደሚወሰን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታው እስከሚደረግበት ዕለት (ረቡዕ መስከረም 30) መደበኛ ሰባት ልምምዶችን እንደሚሰራ ሲጠበቅ ከፊታችን ሀሙስ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ድረስ በውጪ ሀገራት የሚጫወቱ አራቱ ተጨዋቾች (ሽመልስ፣ ቢኒያም፣ ጋቶች እና ዑመድ) በማካተት በሙሉ ስብስቡ ልምምዱን እንደሚቀጥል ተነግሯል።
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/39965
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
50f0cfe9649c200460e29a954d6c6298
7d07d76e4a031ef35671cc734df70f33
ካናዳ የቬንዝዌላውን አምባሳደር ዊልመር ባሪኤንቶስ ፈርናንዴዝ እና ምክትላቸውን አንጄላ ሄሬራ ከሀገር ላስወጣ ነው አለች።
ካናዳ የቬንዝዌላን አምባሳደር አባረረች\nፕሬዝዳንት ማዱሮ በቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። የካናዳ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ክርስችያ ፍሬላንድ ሀገራቸው ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ የካናዳ ዲፕሎማቶች ከካራካስ መባረራቸውን ተከትሎ ነው ብለዋል። ቬንዝዌላ በተደጋጋሚ ካናዳን በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ትገባለች ስትል ከሳታለች። ካናዳ በበኩሏ የፕሬዝዳንት ማዱሮ መንግስት የሰብዓዊ መብት አያያዙ አስከፊ ነው ስትል ትወቅሳለች። ''እኛ ካናዳዊያን የዜጎቹን ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምብት ነጥቆ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከሚያሳጣ መንግሥት ጋር ወዳጅነት ሊኖረን አይችልም'' ሲሉ የካናዳው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ክርስችያ ፍሬላንድ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በመጠናቀቅ ላይ ባለው 2017 በነበሩ ጸረ-መንግሥት ተቋሞዎች ከ120 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። በመጠናቀቅ ላይ ባለው 2017 በነበሩ ጸረ-መንግሥት ተቃውሞዎች ከ120 ሰዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። የቬንዝዌላው አምባሳደር ከሀገር ውጪ መሆናቸውን እና ወደ ካናዳ እንዲገቡ አንደማይፈቀድላቸው እንዲሁም ምክትል አምባሳደሯ ካናዳን ለቀው አንዲወጡ እንደተነገራቸው የውጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ጨምረው ተናግረዋል። የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርም በፕሬዝዳንት ማዱሮ ላይ ማዕቀቦችን ጥሏል እንዲሁም ''አምባገነን'' ሲል ፈርጇቸዋል ማዱሮን። የቬንዙዌላ ተቃዋሚዎች ፕሬዝደንት ማዱሮ እና የቀድሞ ፕሬዝደንት ሁጎ ቻቬዝ በሶሻሊስት ሥርዓተ-መንግሥታቸው የቬንዝዌላን ኢኮኖሚ ክፉኛ ጎድተዋል ሲሉ ድምጻቸውን ያሰማሉ። ቬንዝዌላ በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ካለባቸው ሀገራት አንዷ ስትሆን መድሃኒትን ጨምሮ መሰረታዊ የሚባሉ ሸቀጦች እጥረት በተደጋጋሚ ያጋጥማታል። የፕሬዝደንት ማዱሮ የስድስት ዓመት የስልጣን ዘመን እአአ 2019 ይጠናቀቃል። በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ አስታወቀዋል። ከጥቂት ቀናት በፊትም የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማገዳቸው ተዘግቧል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
593ca8799321ef4ca21b5c63892cd9fd
7f6ea96a4b371501447d16df1d00193d
ቀዳማዊ ምኒልክ
ቀዳማዊ ምኒልክ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሰሎሞናዊ ንጉሥ ናቸው ተብሎ ይታመናል። ደግሞ ይዩ የኢትዮጵያ ነገሥታት የኢትዮጵያ ነገሥታት ቤተ እስራኤላውያን እነማን ናቸው? ታሪኩን ለመረዳት ከጌታችን ልደት በፊት በእስራኤል ላይ ነግሦ የነበረውን የንጉሥ ዳዊት ልጅ የሆነውን የጠቢቡ ሰሎሞንን ታሪክ እና በኢትዮጵያ/በአቢሲኒያ የነገሠችውን የንግሥተ ሳባን ታሪክ ማየት ግድ ይለናል። እንድሁም ታራኩ ከታቦተ ፅዮን አመጣጥ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት ያለው ሲሆን በመጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ምዕራፍ 10 ላይ እና በሌሎች አዋልድ መጻሕፍት ላይ ተፅፎ እናገኜዋለን። ጌታችን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 12:42 ላይ "ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና" በማለት የጠቀሳት ንግሥተ ማክዳ ወይም ንግስተ ሳባ በወቅቱ የኢትዮጵያን/የአቢሲኒያን ሕዝብ የምታስተዳድር ንግሥት ነበረች፡፡ እንድሁም በጊዜው በእስራኤል ላይ ነግሦ የነበረውን የሰሎሞንን መንፈሳዊ ጥበብ በነጋደዎች በኩል ትሰማ ነበር። ዕለት ዕለትም የሰማችውን የሰሎሞንን ጥበብ እና ዝና ለማየት ትጓጓ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ የሰሎሞንን ጥበብ በአካል ታይ ዘንድ፣ በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ፣የሁለቱን አገራት ግንኙነት ታጠናክር ዘንድ በማሰብ ታምሪን በተባለ ነጋደ መሪነት ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘች፡፡ (መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 10:1፤) ያለ አንዳች መሰናክልም ተጉዛ ኢየሩሳሌም ደረሰች፡፡ ለታቦተ ጽዮን ክብርና ለንጉሥ ሰሎሞንም ገጸ በረከት አቀረበች፡፡ ንጉሥ ሰሎሞንም እርሷንና ተከታዮቿን በጥሩ መስተንግዶ ተቀበላቸው፡፡ ንግሥት ሳባም የቤተ መንግሥቱን ሥርዓት ሥጋዊና መንፈሳዊ ጥበቡንም ሁሉ አስተዋለች። የጠየቀችውን እንቆቅልሽ ሁሉ ፈታላት፤ ሊፈታላት ያልቻለውና ከንጉሡ የተሰወረ ነገርም አልነበረም።" ንጉሡንም አለችው፦ "ስለ ነገርህና ስለ ጥበብህ በአገሬ ሳለሁ የሰማሁት ዝና እውነት ነው። እኔም መጥቼ በዓይኔ እስካይ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም ነበር፤ እነሆም፥ እኩሌታውን እንኳን አልነገሩኝም ነበር፤ ጥበብህና ሥራህ ከሰማሁት ዝና ይበልጣል።" አለችው። 1ኛ ነገሥት 10፥6-7 ንግሥተ ሳባ/ማክዳ በኢየሩሳሌም ቆይታዋ ከንጉሥ ሠሎሞን ቀዳማዊ ምኒልክን ፀነሰች፡፡ ወደ ኢትዮጵያም ተመልሳ ልጇን ምኒልክን ወለደች፡፡ ቀዳማዊ ምኒልክ በሀገሩ/በኢትዮጵያ ተወለዶ 12 ዓመት በሆነው ጊዜ ከእናቱ የተሰጠውን ለንጉሥ ሰሎሞንና ለታቦተ ጽዮን እጅ መንሻ ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ፡፡ ንግሥተ ሳባም ለንጉሥ ሠሎሞን “ንጉሥ ሆይ ልጄ ምኒልክ ሙሴ የጻፋቸውን ሕግጋትና ሥርዓተ ክህነት አስተምረህ ላክልኝ፡፡” የሚል መልእክትም አብራ ልካ ነበር፡፡ ቀዳማዊ ምኒልክም በኢየሩሳሌም ከአባቱ ዘንድ ለሦስት ዓመት ያህል የሙሴን መፃህፍት፣ ሕገ መንግሥትን፣ ሥርዓተ ክህነትንና የዕብራይስጥን ቋንቋ ከሊቀ ካህናቱ ከሳዶቅ እየተማረ ከቆየ በኋላ፤ ንጉሥ ሠሎሞን ልጁ ሮብኣም ገና ስድስት ዓመቱ ነበርና ምኒልክን አልጋ ወራሽ ሊያደርገው ቢያስብም ምኒልክ ግን ፈቃደኛ ስላልሆነና ወደ አገሩ ለመመለስ በመፈለጉ ምክንያት በካህኑ ሳዶቅ ቅብዓተ ንግሥ ተፈፅሞለት፤ ከአስራ ሁለቱም ነገደ እስራኤላውያን የተውጣጡ 12,000 ከሚሆኑ የእስራኤል ሌዋውያን ካህናት እና ከቤተመንግሥት ሹማምንቶች የበኩር ልጆች ጋር ወደ አገሩ/ኢትዮጵያ ላከው፡፡ የእስራኤል የበኩር ልጆችም ወደማናውቀው አገር ስንሄድ ታቦተ ፅዮንን ትረዳናለችና እሷን ሳንይዝ አንሄድም በማለት ተመካክረው የእግዚአብሔርም መልካም ፈቃድ ሆኖ ምንልክም ሆነ ሌሎች እስራኤላውያን ሳያውቁ በሙሴ እጅ የተቀረፀችውን ፅላት ይዘዋት ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ንግሥት ሳባም ታቦተ ጽዮን መምጣቷን ስትሰማ ለእግዚአብሔር መስዋዕት አቀረበች፡፡ ሰዎችን መርጣ ታቦተ ጽዮንን እንዲጠብቁ አድርጋለች፡፡ የመንግሥቱን ሥልጣን በሙሉ ለቀዳማዊ ምኒልክ አስረክባ ከዚህ ዓለም በሞተ በተለየች ጊዜ በዚያው በአክሱም ተቀብራለች፡፡ ለእስራኤላውያን ብዙ ተአምራትን ያደረገች ይህችም ፅላት ለ3000 ዓመታት ያህል እስከዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ በአክሱም ፅዮን ማርያም ትገኛለች፡፡ ታሪኩን ወደ ዋናው ርዕሳችን (ቤተ እስራኤላውያን) ስናመጣው እንድህ ነው። የመጀመሪዎቹ ቤተ እስራኤላዊያን ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት ከንጉሥ ሠሎሞንና ከንግሥት ሳባ ልጅ (ከቀዳማዊ ምንልክ) ጋር ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የእስራኤል የሹማምንቶች የበኩር ልጆች ናቸው። በጊዜው የሰፈሩትም በኤርትራ፣በአክሱም ትግራይ አካባቢዎች ይኖሩ የነበረ ሲሆን፤በኢትዮጵያ የክርሥትና ሃይማኖት የሀገሪቱ ብሔራዊ ሀይማኖት ሁኖ በታወጀበት ወቅት፣ የክርስትናን ሃይማኖትን አንቀበልም በማለታቸው ምክንያት ከአክሱም ተባረው በወገራ፣ ደምቢያ፣ ጭልጋ፣ ጣና ሀይቅ ዳር፣ እና በሰሜኑ ተራራማ ቦታዎች ሰፍረዋል። በህገ ኦሪት የሚመራ የራሳቸውን ስርወ መንግስትም አቋቁመዋል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/yosefw/amharic-wikipedia
beaf5d0a3bb418ea345fdb6963dd468f
bdaceefbf6119766e652c4ac05206d46
የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች ግጭት ውድመት ሪፖርት እየተጠናቀቀ ነው
አራት መቶ ሺሕ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ እስር ቤት ይገኛሉበመስከረም ወር 2010 ዓ.ም. በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ግጭት ምክንያት የደረሰውን ውድመት የሚያጣራው ቡድን ሪፖርት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ከሁለቱም ክልሎች ከ900 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ መጠኑ የማይታወቅ ንብረት ወድሟል፡፡የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ማክሰኞ ግንቦት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ባወጣው የሁለት ሳምንታት ሪፖርት መሠረት፣ መንግሥት ከብሔራዊ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ ከፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴርና ከተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የተወጣጣ ቡድን በተለያዩ አካባቢዎች በመገኘት ማጣራት አካሂዷል፡፡አጣሪው ቡድን በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ሥፍራዎች የደረሰውን የመሠረተ ልማቶች ውድመት ዓይነትና ስፋት፣ እንዲሁም በግጭቱ ምክንያት በግለሰቦች ንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት መመርመሩ በሪፖርቱ ተካቷል፡፡በተደረገው ማጣራት በመንግሥት መሠረት ልማቶችና በሕዝብ መገልገያዎች ላይ ጉዳት መድረሱ መረጋገጡን፣ በተለይም የውኃ፣ የጤና፣ የትምህርትና የግብርና ተቋማት መጎዳታቸው ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም በግል ንብረቶችና ይዞታዎች፣ እንዲሁም በማሳዎች፣ በቤቶች፣ በእንስሳትና በመሳሰሉት ላይ የደረሰው ጉዳት መካተቱ ተጠቁሟል፡፡ የደረሰው ውድመት ግምት ለጊዜው ይፋ ባይደረግም፣ በአጣሪው ቡድን ሪፖርት መጠኑ እንደሚገለጽ ታውቋል፡፡እየተጠናቀቀ ያለው ሪፖርት በቅርቡ ለመንግሥትና ለለጋሾች ጭምር እንደሚቀርብ፣ በዚህም ላይ በመመሥረት ከ900 ሺሕ በላይ ለሆኑ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ለማቅረብ የሚያስችል ንቅናቄ ይደረጋል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም ለመካከለኛና ለረጅም ጊዜ የድጋፍ ዕቅድ እንደሚረዳም ተጠቁሟል፡፡በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያም ሆነ በሶማሌ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮች በበቂ መጠን እየተረዱ አለመሆኑን እየገለጹ ነው፡፡ ተፈናቃዮቹን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረገው ጥረትም አዝጋሚ እንደሆነ ይነገራል፡፡ይህ በዚህ እንዳለ ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (አይኦኤም) በባለፈው አንድ ዓመት ከሳዑዲ ዓረቢያ የተመለሱ ዜጎች ቁጥር 160 ሺሕ ያህል ቢሆንም፣ 400 ሺሕ የሚሆኑት በእስር ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡ባለፈው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት 1,400 ያህል እስረኞች መፈታታቸውን ያስታወሰው ድርጅቱ፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በሚያዝያ ወር በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው እስረኞች መካከል 39 በመቶው ወይም 400 ሺሕ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ናቸው ብሏል፡፡
ፖለቲካ
https://www.ethiopianreporter.com/article/10598
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1fc10e373cd3f757c6bd26b63e6680df
1ab79386d1bde7c8bb6df4c1465cf305
የኦስትሪያ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሂጃብን ጨምሮ የተለያዩ ሐይማኖት መገለጫዎችን ማድረግ የሚከለክለውን ሕግ ሰረዘ።
ኦስትሪያ ትምህርት ቤት ውስጥ ሂጃብ ማድረግ የሚከለክለውን ሕግ ሰረዘች\nሕጉ የሐይማኖት ነፃነትን የሚጋፋ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል። ሕጉ የተላለፈው ወግ አጥባቂው 'ፒፕልስ ፓርቲ' ከግራ ዘመሙ 'ፍሪደም ፓርቲ' ጋር ጥምር መንግሥት መስርቶ በነበረበት ወቅት ነው። ፍርድ ቤቱ ሕጉ ሴት ሙስሊሞችን አግላይ እንደሆነ ተናግሯል። መንግሥት ሕጉን ሲያወጣ ሙስሊም ተማሪዎች በክፍል ጓደኞቻቸው ጫና እንዳይድርባቸው ለመጠበቅ ነው ቢልም፤ ፍርድ ቤቱ ግን "ሕጉ ወንጀለኛ አድርጎ ያስቀመጠው ትክክለኛውን ሰው አይደለም" ብሏል። ፍርድ ቤቱ አክሎም፤ መንግሥት ሙስሊም ተማሪዎችን መከላከል ከፈለገ ሐይማኖት እና ፆታን መሠረት አድርገው መድልዎ የሚያደርሱ ሰዎችን የሚቀጣ ሕግ ነው ማውጣት ያለበት ብሏል። ሕጉ ተግባራዊ የተደረገው አምና ነበር። ሂጃብ ማድረግ ክልክል ነው ብሎ በግልጽ ባያስቀምጥም፤ "እስከ 10 ዓመታቸው የሆኑ ልጆች ራስ ላይ የሚጠመጠሙ ሐይማኖታዊ ልብሶችን ማድረግ አይችሉም" ይላል። የሲክ እና የአይሁድ እምነት ተከታይ ልጆችን ሕጉ እንደማያካትት መንግሥት ተናግሯል። ስለዚህም ሕጉ ሂጃብ ላይ ያነጣጠ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ተናግሯል። የፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ክሪስቶፍ ግራቤንዋርተር "ሕጉ ክልከላ የጣለው ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ነው። ይህ ሕግ ከሌሎች ተማሪዎች ነጥሎ ያገላቸዋል" ብለዋል። የትምህርት ሚንስትር ሄንዝ ፋስማን "ሴቶች ያለ ጫና በትምህርት ሥርዓቱ ማለፍ አለመቻላቸው ያሳዝናል" ብለዋል። የኦስትሪያ የሙስሊም ማኅበረሰብ ተቋም ሕጉ መሻሩን በደስታ ተቀብሎታል። "ሴቶችን እኩል እድል ማግኘታቸውን ማረጋገጥ እና በራሳቸው የሚወስኑትን መቀበል የሚቻለው ክልከላ በመጣል አይደለም" ሲል መግለጫ አውጥቷል። ሕጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲረቅ፤ መራሔ መንግሥት ሰባስሽን ከርዝ "ሕጉ የኦስትሪያ ማኅበረሰብ ውስጥ ተነጥሎ የሚወጣ ማኅበርን ያስወግዳል" ብለው ነበር። የፍሪደም ፓርቲ ምክትል መራሔ መንግሥት ሄንዝ ክርስትን ስትራቼ፤ መንግሥት ታዳጊ ሴቶችን "ከፖለቲካዊ እስልምና" ለመጠበቅ እየሞከረ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ከዚያም ሕጉ እአአ 2019 ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ተድርጓል። አሁን ላይ ፒፕልስ ፓርቲ ከግሪን ፓርቲ ጋር ተጣምሯል። ሂጃብ የሚከለከለውን ሕግ እስከ 14 ዓመት በደረሱ ታዳጊዎች ላይ ተግባራዊ የማድረግ እቅድ ነበረ።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
1dcb5fa310ad82b95b8609ee635fb6d3
9c543d741a0e1fbca1bd4b617832106b
ዓመታዊው የአምባሳደሮች ስብሰባ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዋናው መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባሳደሮች እና ቆንስል ጀኔራሎች ዓመታዊ ስብሰባ ተጠናቀቀ።ስብሰባው “ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኳችን ለሃገራዊ ብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል ነበር ላለፉት 15 ተከታታይ ቀናት በቢሾፍቱ ሲካሄድ የቆየው፡፡ተሳታፊዎቹ በተያዘው በጀት ዓመት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚከያናውናቸው ዋነኛ ጉዳዮች ላይ አተኩረው ተወያይተዋል፡፡እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በአዲሱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ መክረዋል፡፡በተመሳሳይ በኢትዮጰያ የ10 ዓመት /ከ2013 እስከ 2022 ዓም/ መሪ የልማት እቅድ ላይ ውይይት አድርጓል።በመጨረሻም የውይይቱ ተሳታፊዎች ባለፉት ሁለት ሳምንታት የመከሩባቸውን ጉዳዮች መሰረት አድርገው ለሀገራቸው የተሻለ ነገር እንደሚያበርክቱ ገልጸዋል፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8b%93%e1%88%98%e1%89%b3%e1%8b%8a%e1%8b%8d-%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%88%9d%e1%89%a3%e1%88%b3%e1%8b%b0%e1%88%ae%e1%89%bd-%e1%88%b5%e1%89%a5%e1%88%b0%e1%89%a3-%e1%89%b0%e1%8c%a0%e1%8a%93%e1%89%80/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
45d997f6c7fee7f216fc6a0d0d1ec2f9
e4d4f24f7f4a0fe268a5705bdd8cd54b
የኢትዮጵያ ጦር ኃይል አቅም በአፍሪካ ስድስተኛ ደረጃ መያዙን ዓለም አቀፍ ሪፖርት አመለከተ
የአገሮችን ወታደራዊ አቅም ከኢኮኖሚያዊ አቋማቸውን በመንተራስ ደረጃቸውን ይፋ የሚያደርገውና ‹‹ግሎባል ፋየርፓወር›› የተሰኘው የአሜሪካ ተቋም፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኃያል ከሚባሉ አሥር ዋና ዋና አገሮች ውስጥ በስድስተኛ ደረጃ የሚያሠልፋት የጦር ኃይል አቅም እንዳላት ይፋ አደረገ፡፡ ተቋሙ ባስቀመጣቸው 55 ልኬቶች፣ ደረጃዎችና መደቦች መሠረት ኢትዮጵያ በግብፅ፣ በአልጄሪያ፣ በደቡብ አፍሪካ፣ በናይጄሪና በአንጎላ ተቀድማ ከአፍሪካ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተደልድላለች፡፡ ኢትዮጵያ ይህንን ደረጃ የያዘችው ከቀደመው ደረጃ ወደ ታች ወርዳ ሲሆን፣ በዓለም ደረጃ ንፅፅር ተደረጎባቸው ደረጃ ከተቀመጠላቸው 136 አገሮች ውስጥም በ51ኛ ረድፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ግሎባል ፋየርፓወር እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ወታደራዊ ትንታኔዎችን በማውጣት ዘመናዊ ጦር የታጠቁ 136 አገሮችን ማነፃፀር የጀመረ ሲሆን፣ ከእነዚህ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ በመሆን በደረጃ ተመድባለች፡፡ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ እንዳላት ከሚገመተው ከ105 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ውስጥ ለጦር ኃይል አባልነት ሊመለመል የሚችል 40 ሚሊዮን ኃይል የሰው ኃይል እንዳላት ሪፖርቱ አመላክቶ፣ ከዚህ ውስጥ 24 ሚሊዮን ሕዝብ ለውትድርና አገልግሎት ብቁ መሆኑን አስፍሯል፡፡ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ለውትድርና ዕድሜው ብቁ የሚሆነው ሕዝብ ብዛት ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ መሆኑን፣ በአሁኑ ወቅት ያለው መደበኛ የአገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ብዛት ግን 162 ሺሕ እንደሆነም ግሎባል ፋየርፓወር አሥፍሯል፡፡ ኢትዮጵያ ተጠባባቂ ጦር ከሌላቸውና የባህር በር አልባ ከሆኑ አገሮች ተርታ ትገኛለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 80 የጦር አውሮፕላኖች እንዳሏት፣ ከእነዚህ 48 ተዋጊና ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች መሆናቸውን 42 የመጓጓዣ፣ 14 የሥልጠና፣ እንዲሁም 33 ሔሊኮፕተሮች እንዳሏት ከእነዚህ ውስጥም ስምንቱ የውጊያ መሆናቸውም በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪ 800 የውጊያ ታንኮች፣ 800 ብረት ለበስ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፣ 183 የሮኬት ተወንጫፊዎችና ሌሎችም ወታደራዊ መሣሪያዎችን በመታጠቅ በአፍሪካ ኃያል ከሚባሉ አገሮች ተርታ መግባቷን፣ ለመከላከያ የምትመድበው ዓመታዊ በጀት ከ340 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ በአንፃሩ በአፍሪካ አንደኛ በዓለም 12ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ግብፅ፣ 875 ሺሕ ተጠባባቂ ጦሯን ጨምሮ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የሠራዊት አባላት እንዳሏት ዓመታዊ የመከላከያ በጀቷም ከ4.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት አገር እንደሆነች በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡ ከ1132 በላይ የጦር አውሮፕላኖች ያሏት ግብፅ፣ 309 ተዋጊ አውሮፕላኖች እንዳሏት ተጠቅሷል፡፡ 269 ሔሊኮፕተሮች፣ 5,000 ያህል ታንኮች፣ ከ15 ሺሕ በላይ ብረት ለበስ የጦር ተሽከርካሪዎች፣ ከ1,200 በላይ ተወንጫፊ ሮኬቶች አሏት ተብሏል፡፡ ከዚህ ባሻገር ስድስት ባህር ሰርጓጆች፣ ሁለት አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችና ከ320 ያላነሱ የባህር ኃይል የውጊያ አሃዶች የገነባች አገር ተብላለች፡፡ በጦር ኃይል ልዕልና መለኪያውና በደረጃ አወጣጡ ላይ 55 መሠረታዊ መነሻ ነጥቦች ተብለው ከተቀመጡት ዋነኛ ይዘቶች መካከል የወታደር ብዛት፣ የጠቅላላው ሕዝብ ብዛትና ለውትድርና ከሚፈለገው ውስጥ ለአገልግሎት ብቁ የሆነው የሰው ኃይል ብዛት፣ በየዓመቱ ለአቅመ ውትድርና የሚደርሰው የሰው ሀብት ብዛት፣ በውትድርናው መስክ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርገው የሰው ኃይል ብዛት፣ በንቃት የሚጠባበቅ የወታደር ኃይል ብዛት የሚሉት በሰው ኃይል መመዘኛ መስክ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በአየር ኃይል ረገድ ጠቅላላ የአውሮፕላን ብዛት፣ የተዋጊና የቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ብዛት፣ የወታደራዊ ማጓጓዣ አውሮፕላኖች፣ የሥልጠና አውሮፕላኖች፣ ተዋጊ ሔሊኮፕተሮችን ጨምሮ የጠቅላላ ሔሊኮፕተሮች ብዛትም በተዋጊ አውሮፕላኖች መስክ አገሮች በደረጃ የሚቀመጡበት መስክ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የተዋጊ ታንኮች፣ የብረት ለበስ ጦር ተሽከርካሪዎች፣ የሮኬት ማስወንጨፊያዎች፣ በባህር ኃይል መስክም የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦች፣ ተዋጊዎች፣ ሰርጓጆች፣ የፓትሮልና ሌሎችም ለጦር ኃይል ሥምሪት የሚውሉ መርኮቦች ያሏቸው አገሮች በደረጃቸው እንደ አቅማቸው ተቀምጠዋል፡፡ በየዓመቱ ለመከላከያ የሚመበደው በጀትን ጨምሮ የውጭ ዕዳና ተቀማጭ ገንዘብ መጠን፣ የሎጂስቲክስ አቅም፣ የተፈጥሮ ሀብት፣ እንዲሁም መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ አገሮችን በጦር ኃይል ደረጃ ለመመደብ የተቀመጡ መሥፈርቶች ናቸው፡፡
ፖለቲካ
https://www.ethiopianreporter.com/article/14233
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
49d5b09ed219f666e16b0b6bdae972f8
ab168f835a8162dab77542c3584b4627
ፕሪሚየር ሊግ ፡ ኤሌክትሪክ ወሳኝ 3 ነጥቦችን አሳካ
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተደረገ ብቸኛ ጨዋታ ኤሌክትሪክ አርባምንጭ ከነማን 1-0 አሸንፎ ከወራጅ ስጋት በመጠኑ የሚያላቅቀውን ወሳኝ 3 ነጥብ አሳክቷል፡፡የኤሌክትሪክን ብቸኛ የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈው በውድድር ዘመኑ አጋማሽ ቀዮቹን የተቀላቀለው ሰውረን ኦልሪስ ሲሆን ለግቧ መቆጠር የአርባንጪ ግብ ጠባቂ አንተነህ መሳ ስህተት ጉልህ ድርሻ አበርክታለች፡፡አርበንጮች በሁለተኛው አጋማሽ የፍፁም ቅታት ምት አግኝተው የነበረ ቢሆንም አማኑኤል ጎበና የመታውን ኳስ አብርሀም ይርጉ አክሽፎበታል፡፡ከጨዋታው በኋላ የኤሌክትሪኩ አሰልጣኝ አጥናፉ አባተ አስፈላጊውን ነጥብ እንዳሳኩ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ውጤቱ ለኛ በጣም አስፈላጊያችን ነበር፡፡ አርበንጭ ከነማ ጠንካራና በፈላጎት የሚጫወት ቡድን በመሆኑ በአጨዋወታቸው ጫና ውስጥ ሊከቱን ሞክረዋል፡፡ ይህንን ጨዋታ ማሸነፋችን በደረጃ ሰንጠረዡ ከፍ እንድንል ከመርደቱም በላይ በጫና ውስጥ ለነበሩት ተጫዋቾቻችንም ትልቅ መነቃቃት ይፈጥርብናል፡፡ ›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡የአርባምንጩ አለማየሁ አባይነህ በበኩላቸው ‹‹ ተጫዋቾቼ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል፡፡ ኤሌክትሪኮች ሰአት ሲያባክኑ የእለቱ አርቢትር ካሳየው ቸልተኝነት ውጪ ጨዋታው በእንቅስቃሴም ሆነ በዳኝነቱ መልካም ነበር፡፡ አላማችን በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ ላይ ሆኖ ማጠናቀቅ ሳይሆን ያለፉት አመታት ውጤቶቻችንን ዘንድሮ አሻሽሎ መጨረስ ነው፡፡ ›› ብለዋል፡፡
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/2526
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
124eca995f47384a294e8a8f9084e6ca
4103a7881b53f1477f08232b60ac9f2a
የሼክ ሙሐመድ ሑሴን አል-አሙዲ ስታዲየም በቅርቡ ይመረቃል
በወልድያ ከተማ የተገነባው የሼክ ሙሐመድ ሑሴን አሊ አል-አሙዲ ስታዲየምና የስፖርት ማዕከል በመጪው ጥር 6 እንደሚመረቅ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አስታወቀ፡፡የኩባንያው ፕሬዝዳንት ዶክተር አረጋ ይርዳው የስታዲየሙን ግንባታ መጠናቀቅ አስመልክተው ዛሬ በሸራተን አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስታዲየሙ 25ሺህ155 ተመልካቾችን የመያዝ አቅም እንዳለውና 567ሚሊየን 890ሺህብር ወጪ መደረጉን አስታውቀዋል ፡፡ስታዲሙ በተጓዳኝ የተሟላ የሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ማለትም የእጅ ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ የሜዳ ቴንስ፣ የኦሎምፒክ ውድድሮችን ማስተናገድ የሚችል የመዋኛ ገንዳና የእንግዳ ማሪፊያ አጣምሮ የያዘ ነው ብለዋል ፡፡ስታዲየሙ የዓለም አቀፉን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን መስፈርቶችን የሚያሟላና ሙሉ የጸሐይ መጠለያ፣ የመሮጫ ትራክ፣ ዘመናዊ የድምጽ ማጉያዎች፣ ሁለት የውጤት ማሳያ ሰሌዳዎች ከዘመናዊ መብራቶች ጋር የተገጠመለት መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡በ177 ሺህ  ሜትር ካሬ ያረፈውን ስታዲየሙ ሙሉ ወጪ በሼክ ሙሐመድ ሑሴን አሊ አል-አሙዲ የተሸፈነ ሲሆን የወልደያ ከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች በጋራ 30 ሚሊየን ብር በማዋጣት የእንግዳ ማረፊያውን እንደገነቡት ገልጿል፡፡ሚድሮክ ኩባንያ በስሩ ካሉት 25 ኩባንያዎች አስሩ በግንበታው ላይ እደተሳተፉና 95 በመቶ የሚሆነው የግንባታ ጥሬ ዕቃ በኩባንያው እንደተሸፈነ ዶክተር አረጋ አስታውቀዋል፡፡በተጨማሪም ለግንባታው የሚያስፈልገው የሰው ኃይል ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ብቻ እንደተከናወነ ተመልክቷል፡፡ግንባታው በሚድሮኩ ኩባንያ ሁዳ ሪል ስቴት የተከናወነ ሲሆን ግንባታው አራት ዓመት ተኩል እንደፈጀም  አስታውቀዋል፡፡በግንባታው 800 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የስራ ዕድል እንደተፈጠረና ከፍተኛ የሆነ የዕውቀትና ክህሎት ልምድ መቅሰም በመቻሉ በቀጣይ ሀገሪቷ ለሚያስፈልጋት በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል በቂ ሥራ በመሰራቱ ተጨማሪ ስታዲየሞችን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት እጥረት እንደማያጋጥም አክለው ገልጸዋል፡፡በኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉት ስታዲየሞች መጠናቀቅ በቀጣይ አህጉር ዓቀፍና አለምአቀፍ ስፖርታዊ ውድሮችን ለማስተናገድ የሚኖረውን ዕድል እንደሚያሰፋ መግለጻቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
https://waltainfo.com/am/31520/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
8939b8bd619ed9ba81bf6ad7d3651293
2993524f47a9ba3c113167815badd301
የቆሼ ተጎጂዎች ማቋቋሚያ ፓኬጅ በተለያዩ ምክንያቶች መጓተቱ ተገለጸ
ለቆሼ ተጎጂዎች እንዲውል በተዘጋጀው የማቋቋሚያ ፓኬጅ ያላግባብ ለመጠቀም በገቡ ሰዎች፣ በቤተሰብ መካከል በተነሱ የይገባኛል ጥያቄዎችና ተጎጂዎች መረጃዎቻቸውን በአግባቡ አሟልተው ባለማቅረባቸው በሥራው ላይ መንጓተት እንዲፈጠር ምክንያት መሆናቸው ተገለጸ፡፡ ያላግባብ ለመጠቀም በገቡ 166 ሰዎች ላይም አስተዳደራዊ ውሳኔ መሰጠቱና በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግም ምርመራ እየተካሄደባቸው የሚገኙ እንዳሉ ታውቋል፡፡ ፍርድ ቤት ለተለያዩ ሁለት ሰዎች የወራሽነት መብት በመስጠቱ ጭቅጭቅ ያስነሳ ጉዳይም መኖሩ ተጠቁሟል፡፡  ‹‹በደንብ መታየት ያለባቸው የይገባኛል ጥያቄዎች ያላቸው ጉዳዮች አሉ፤›› የሚሉት የአዲስ አበባ ከተማ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው፣ ሌሎች ለመዘግየቱ ምክንያት የነበሩ ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ተጎጂዎችን በጊዜያዊነትና በዘላቂነት ከማቋቋም አንፃር በመንግሥትና በኅብረተሰቡ የተደረጉና እየተደረጉ ያሉ ድጋፎችን፣ እንዲሁም በቀጣይ በዘላቂነት ለማቋቋም የተጀመረውን ተግባር ይፋ ለማድረግ ተጎጂዎችና ሌሎች ባለድርሻዎች በተገኙበት እሑድ ሰኔ 4 ቀን 2009 ዓ.ም. በማዘጋጃ ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ በዕለቱ መግለጫው እስከተሰጠበት ቀን ድረስ ያሉትን ሒደቶችና አፈጻጸሞች የሚያሳይ ሪፖርት አቶ ኤፍሬም አቅርበዋል፡፡በሪፖርቱ መሠረት የቆሼ ተጎጂዎችን ለዕለትና በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን ሀብት ለማሰባሰብ አስተዳደሩ በከፈተው የድጋፍ ማሰባሰቢያ የገቢ ሒሳብ፣ እስከ ሰኔ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ የተሰበሰበው 94,805,936.84 ብር  መድረሱ፣ በዓይነት ግምታቸው 7.5 ሚሊዮን የሚደርስ የምግብ፣ የመጠጥ፣ የአልባሳትና የቤት ቁሳቁስ በገቢ ሞዴል መሰብሰቡ፣ በዓይነት ከተሰበሰቡ 2,031,731.49 ብር የሚገመቱ የንፅህና መጠበቂያና የተለያዩ ግብዓቶች ለፓኬጁ ተጠቃሚዎች እስከ ሰኔ 2 ቀን 2009 ዓ.ም. መሠራጨታቸው፣ መንግሥትም በሚሊዮን የሚቆጠር አስተዳደራዊ ወጪዎችን ማውጣቱ በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡ ዝርዝር መረጃው ወደፊት ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ተብሏል፡፡ ለአደጋው ተጋላጭ ለሆኑ 98 አባወራዎች ምትክ ቦታ መዘጋጀቱን፡፡ የይገባኛል ጥያቄ ካለባቸው ሁለቱ በስተቀርም ለ96 ሰዎች እስከ ቅዳሜ ሰኔ 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ርክክብ መደረጉን፣ የካርታ ሥራም እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የ18 ወራት የቤት ኪራይ እንዲከፈላቸው በተወሰነው መሠረትም የአምስት ወራት የቤት ኪራይ ቅድሚያ ክፍያ መፈጸሙን፣ ቀሪው በዚህኛው ሳምንት ከሰኞ ጀምሮ ከካሳ ግምቱ ጋር እንደሚከፈላቸው አቶ ኤፍሬም አብራርተዋል፡፡ ለካሳ ግምት ክፍያ የከተማ አስተዳደሩ 48 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚያደርግ፣ ይህም ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ክፍያው እንደሚፈጸም አክለዋል፡፡በአሥራ ስድስቱ የሕጋዊ ይዞታ ባለቤቶች የይገባኛል ጥያቄና ሌሎች አከራካሪ ነገሮች ከተነሳባቸው ከሦስቱ ውጪ፣ ለ13 ሰዎች ከ17.8 ሚሊዮን ብር በላይ ተከፍሏል ብለዋል፡፡ ለአሥራ ሦስት ሕጋዊ ይዞታ ባለቤቶች ጎጆ የወጡና አብረው ሲኖሩ ለነበሩ ልጆች ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የጋራ ሕንፃ ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል፡፡ የኮንዶሚኒየም ቤት እንደ ደረሳቸው ጥቆማ ከቀረበባቸው አንድ ግለሰብ በስተቀር ለ12ቱ የቁሳቁስ መተኪያ፣ የሞት ካሳ፣ የቤት ኪራይና ለመሠረታዊ የምግብ ፍጆታ የሚውል ሁለት ሚሊዮን ሁለት ሺሕ ብር መከፈሉን በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል፡፡ ለጋራ መኖሪያ ቤቱ ግንባታ የተመደበው በጀት አንሶ ከተገኘ እንደሚጨመር አቶ ኤፍሬም አስረድተዋል፡፡‹‹የአንድ ዓመት የቤት ኪራይ ለ13 ሰዎች ሰጥተናል፡፡ ስለዚህም ግንባታው እስኪያልቅ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ሊታገሱን ይገባል፡፡ ክረምት እንደመሆኑ ግንባታ ሊያስቸግረን እንደሚችል እንገምታለን፡፡ በጉዳዩ ላይ ባለሙያዎችን እያነጋገርን ነው፡፡ በተባለው ጊዜ ግንባታው ተጠናቆ ወደ ቤታቸው መግባት ካልቻሉ ተጨማሪ የቤት ኪራይ ክፍያ ይኖራል፤›› ብለዋል፡፡የሕጋዊ ይዞታ ተከራይ ለነበሩ ለ54 አባወራዎች የ10/90 የኮንዶሚኒየም ግዢ የሚሆን አራት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃያ ሺሕ ብር መከፈሉን፣ ለዘጠኝ አባወራዎችም ለሞት ጉዳት፣ ለቁሳቁስ መተኪያና ለመሠረታዊ ምግብ ፍጆታ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ አንድ ሺ አምስት መቶ ብር ክፍያ መፈጸሙን፣ ለ26 አባወራዎች ደግሞ ሦስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃምሳ አንድ ሺሕ ብር ክፍያ ከዚህኛው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ ወደ ባንክ ደብተራቸው እንደሚገባ ተነግሯል፡፡ ቀሪዎቹ አሥራ ዘጠኝ አባወራዎች የይገባኛል ጥያቄ የተነሳባቸውና በመጣራት ላይ ያሉ መሆናቸውን ሪፖርቱ ያትታል፡፡በሕገወጥ መንገድ የላስቲክና የጭቃ ቤት ሠርተው ይኖሩ ከነበሩ 102 አባወራዎች መካከል ለስድስቱ የ10/90 የኮንዶሚኒየም ቤት ግዥ የሚሆን አራት መቶ ሰማንያ ሺሕ ብር ወጪ መደረጉ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ ለሞት ካሳ፣ ለምግብ ፍጆታና ለቁሳቁስ መተኪያም  ለ70 አባወራዎች ሁለት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺሕ ሰባት መቶ ብር ለክፍያ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡ ክፍያው እስከ መጪው ዓርብ ድረስ እንደሚፈጸም ተመልክቷል፡፡ መረጃ ያላሟሉ 23 አባወራዎች መረጃ እስኪያሟሉ እየተጠበቁ እንደሚገኙ፣ ቀሪዎቹ ሦስት አባወራዎች ግን እንደማይገባቸው በመረጋገጡ ከፓኬጁ ተጠቃሚነት እንዲወጡ መደረጉ ታውቋል፡፡በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡ 115 ዜጎች መካከል የ101 ቀብር ማስፈጸሚያ የሚሆን አንድ ሚሊዮን አሥር ሺሕ ብር ወጪ የተደረገ ቢሆንም፣ ለአሥራ አራት ቤተሰቦች ክፍያው ገና አልተፈጸመም፡፡ ለዚህም በቤተሰብ መካከል የተነሳው የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት መሆኑን፣ የተሟላ መረጃ እስኪቀርብ ገንዘቡ ለክፍያ ዝግጁ ሆኖ መቀመጡን አቶ ኤፍሬም ገልጸዋል፡፡ የአካባቢው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በተመለከተም በፓኬጁ የተቀመጠላቸውን ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚያስችሏቸው ሒደቶች ላይ እየሠሩ እንደሚገኝ በሪፖርቱ ተካቷል፡፡ ‹‹እኛ ተመልሰን ወደ ቆሼ መግባት አንፈልግም፡፡ መንግሥት ሊያደራጀንና ሠርተን የምናድርበትን ነገር ማግኘት እንፈልጋለን፤›› ያሉት የቆሼ ተጎጂዋ ወይዘሮ ፈጣን ምላሽ እንደሚያስፈልግ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡‹‹ኮንዶሚኒየም እንደ ደረሰው እንደ ማንኛውም ዜጋ የማጠናቀቂያ ሥራውን ጨርሰው ነው መግባት ያለባቸው፤›› በማለት አቶ ኤፍሬም ኮንዶሚኒየም የደረሳቸው ቤቱን የማስጨረስ ኃላፊነቱ የራሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡በዕለቱ የቆሼ ተጎጂዎች ያሰሙትን ቅሬታ በተመለከተ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የተላለፈው ዘገባ የተሳሳተና ያነጋገሯቸውም ሰዎች በፓኬጁ ያልተካተቱ መሆናቸውን አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡ ሪፖርተር ቦታው ድረስ በመሄድ በማዕከሉ ተጠልለው የነበሩና አደጋው በደረሰበት ቆሼ የሚኖሩ ሰዎችን አነጋግሮ መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ ተከስቶ በነበረው የቆሻሻ መደርመስ 115 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡ በዙሪያው ይኖሩ የነበሩ 592 የሚሆኑ ሰዎች የአደጋው ሰለባ ነበሩ፡፡ በአደጋው ቤት ንብረታቸውን አጥተዋል፡፡ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳትም ተዳርገዋል፡፡ በአደጋው ለተጎዱ ሰዎች በመንግሥት፣ በሕዝቡና በተለያዩ ተቋማት ርብርብ መልሶ ለማቋቋም ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.ethiopianreporter.com/content/%E1%8B%A8%E1%89%86%E1%88%BC-%E1%89%B0%E1%8C%8E%E1%8C%82%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%88%9B%E1%89%8B%E1%89%8B%E1%88%9A%E1%8B%AB-%E1%8D%93%E1%8A%AC%E1%8C%85-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8B%AB%E1%8B%A9-%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%8A%95%E1%8B%AB%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%88%98%E1%8C%93%E1%89%B0%E1%89%B1-%E1%89%B0%E1%8C%88%E1%88%88%E1%8C%B8
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
946380fae38425b926cf7669b154eaaa
48ee7d32d6292d09eb485f30aa4e483c
በደቡብ አፍሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከግማሽ ሚሊዮን አለፈ
የጤና ሚኒስትሯ ዚዌሊኒ ምክሂዝ እንዳሉት በአገሪቷ ቅዳሜ ዕለት ብቻ 10 ሺህ 107 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ቁጥሩን 503 ሺህ 290 አድርሶታል። እስካሁን 8 ሺህ 153 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ አህጉር ከሚገኙ አገራት ክፉኛ በቫይረሱ የተጎዳች ሲሆን በአገሪቷ የተመዘገበው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም በአህጉሩ ከተመዘገበው ግማሽ ያህሉን ነው ተብሏል። አገሪቷ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥርም አሜሪካ ፣ ብራዚል፣ ሩሲያና ሕንድን ተከትላ በአለም አቀፉም በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በአገሪቷ ያለው የሟቾች ቁጥርም ይፋ ከተደረገው የላቀ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ። የደቡብ አፍሪካ የጤና ባለሥልጣናት በፕሪቶሪያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ጠቅሰው የወረርሽኙ ሥርጭት በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሆነ አስጠንቅቀዋል። ከአጠቃላይ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሦስተኛ የሚበልጠው በአገሪቷ የንግድ ማዕከል ጋውተንግ የተመዘገበ ሲሆን ሌሎች ግዛቶችም የወረርሽኙ ማዕከል ሆነዋል ብለዋል። ደቡብ አፍሪካ የወረርሽኙን ሥርጭት ለመግታት በሚያዝያና ግንቦት ወር ላይ ጥብቅ የሆነ የእንቅስቃሴ ገደብ ጥላ ነበር። እነዚህ ገደቦች ሰኔ ወር ላይ ቀስ በቀስ መላላት የጀመሩ ቢሆንም የወረርሽኙ ስርጭት እንደገና መስፋፋቱን ተከትሎ የአልኮል ሽያጭን ጨምሮ ሌሎች ገደቦች ደግሞ ባለፈው ወር ጀምሮ እንደገና ተጥለዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ለመጭዎቹ 15 ቀናት በሥራ ላይ እንደሚቆይ ተነግሯል። በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመር በሆስፒታሎች ላይ መጨናነቅ የፈጠረ ሲሆን የጤና ባለሙያዎች መዳከማቸውንና የጤና አገልግሎቱም እጅግ የተዳከመ መሆኑን ቢቢሲ በምርመራው አረጋግጧል። ባለፈው ወር ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ለኮቪድ -19 ታማሚዎች 28 ሺህ የሆስፒታል አልጋዎች መዘጋጀታቸውን ተናግረው፤ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የዶክተሮችና ነርሶች እጥረት እንዳለባቸው ተናግረው ነበር። ባለፈው ሳምንትም የዓለም ጤና ድርጅት የደቡብ አፍሪካ ልምድ በአህጉሯ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አመላካች ነው ሲል ማስጠንቀቁ ይታወሳል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
fc8d0fb90418ef0e06b54e938b188e1f
6e25cd31015489263d111b414b975f58
​ሪፖርት | የሸገር ደርቢ ከአሰልቺ ጨዋታ ጋር ያለ ጎል ተጠናቋል
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአዲስ አካሄድ ከተጀመረ በኃላ ለ37ኛ ጊዜ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ 11:00 ላይ ጨዋታቸውን አድርገው ከቀዝቃዛ እንቅስቃሴ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።ከጨዋታው መጀመር በፊት የአዲስ አበባ ስታድየም እጅግ ያማረ በነበረው የሁለቱ ቡድኖች ደጋፊዎች ድባብ ፣ በክለቦቹ ትላልቅ አርማዎች እና ዝማሬዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ ደምቆ ታይቷል። የዳኛው ፊሽካ ከመሰማቱ በፊትም በስታድየሙ የተገኘው ተመልካች የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በአንድነት በመዘመር ለነበረው ድባብ ሌላ ውበት ጨምሮለታል።ቅዱስ ጊዮርጊስ ኤሌክትሪክን ከረታበት ስብስብ የቀኝ መስመር የአጥቂ ክፍል ላይ ጋዲሳ መብራቴን በበኃይሉ አሰፋ ብቻ በመቀየር በተመሳሳይ መልኩ በ4-3-3 አቀራረብ ጨዋታውን ጀምሯል። ለውጦች ተበራክተው የታዩበት ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ዓዲግራት ላይ ከተሸነፈው ቡድን ውስጥ አለማየው ሙለታን በበረከት ይስሀቅ የቀየረ ሲሆን በአሰላለፍ እና በተጨዋቾች ቦታ ላይ በርካታ ለውጦችን በማድረግ በ4-2-3-1 አሰላለፍ ወደሜዳ ገብቷል። በዚህም አስራት ቱንጆን ከአጥቂ ጀርባ የተሰለፈ ሲሆን ቡድኑ ኤልያስ ማሞን ወደኃላ ገፍቶ በጥልቅ አማካይነት ሚና ተጠቅሟል። ከዚህ ውጪ ከጉዳት የተመለሰው አስቻለው ግርማም ከአማኑኤል ዮሀንስ ቀድሞ ጨዋታውን ጀምሯል።የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ሁለት ተመሳሳይ ቡድኖችን ያሳየን ነበር። ሁለቱም  መሀል ሜዳ ላይ የኳስ ቁጥጥርን ለማግኘት ሲራኮቱ ቢታይም እጅግ በተጠጋጋው የተጨዋቾች አቋቋማቸው መሀል ሜዳው ተጨናንቆ አንዳቸውም በጥሩ የኳስ ፍሰት እና ቅብብል ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል መድረስ ሳይችሉ ቀርተዋል። በተለይም የመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች እጅግ የተቀዛቀዙ ነበሩ። ጨዋታው የመጀመሪያ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ያስተናገደውም 21ኛው ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ሳኑሚ በቀኝ የሳጥኑ ጠርዝ በኩል ይዞ የገባውን ኳስ ሞክሮ ሮበርት ሲያድንበት ነበር። ከዚህ ውጪ በመጠኑ ወደ ተቃራኒ ሜዳ በመግባት የተሻሉ የነበሩት ኢትዮጵያ ቡናዎች 13ኛው ደቂቃ ላይ በአስራት ቱንጆ በቀኝ መስመር በኩል የፈጠሩት ዕድል ፣ የ6ኛ ደቂቃ የሳሙኤል ሳኑሚ እና የ43ኛው ደቂቃ የኤልያስ ማሞ የርቀት ሙከራዎች ጨምሮ የሚጠቀሱ ነበሩ። ቅዱስ ጊዮርጊሶች 24ኛው ደቂቃ ላይ በሀይሉ አሰፋ ከርቀት አክርሮ መቷት በግቡ አግዳሚ ለጥቂት ከወጣችው ሙከራ ውጪ በጥሩ የማጥቃት ፍሰት በቡናዎች ሳጥን ውስጥ የተገኙት የመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ ላይ ነበር። በዚህም አብዱልከሪም ኒኪማ መሀል ሜዳ ላይ አስናቀ ሞገስንን ኳስ አስጥሎ ለበሀይሉ ካሳለፈለት በኃላ በሀይሉ ከአሜ ጋር ተቀባብሎ ወደ ውስጥ ለመግባት የሞከረው ኳስ በቡና ተከላካዮች ተጨርፎ ወጥቶበታል። በአጠቃላይ ቡድኖቹ ለመጫወት በሞከሩበት አኳኋዋን ንፁህ የግብ ዕድል መፍጠር አለመቻላቸው በግልፅ የታየ ነበር። እንቅስቃሲያቸውም ነፍስ ዘርቶበት አስፈሪ ሲሆን ይታይ የነበረው ቅብብላቸው ከተጨናነቀው የመሀል ክፍል ወጥቶ ወደ መስመሮች በሚሄድበት ወቅት ነበር።ሁለተኛው አጋማሽ የጀመረበት የጨዋታ ፍጥነት ምናልባትም ከመጀመሪያው የተሻለ ፉክክርን ሊያሳየን ነው የሚል ተስፋን በብዙዎች ዘንድ ያሳደረ ነበር። 46ኛው ደቂቃ ላይ ኢብራሂማ ፎፋና ከግራ መስመር ያሻማውን ኳስ ምንተስኖት በግንባሩ ከሞከረ ከሁለት ደቂቃዎች በኋላ በሌላኛው የሜዳው ክፍል አስቻለው ግርማ በግራ መስመር ይዞ የገባውን ኳስ ሞክሮ ሮበርት አደኖበታል። ይህ ከሆነ ከአንድ ደቂቃ በኃላ ደግሞ በቀኝ መስመር በረጅሙ የተሻገረለት ኳስ በሀይሉ አሰፋ ከቅርብ ርቀት ኳሱ መሬት ሳይወርድ ለማግባት ሞክሮ ስቷል። ከነዚህ ሙከራዎች በኃላ ግን ጨዋታው ቀስ በቀስ ወደ ነበረበት የተቀዛቀዘ መንፈስ ተመልሷል። አልፎ አልፎ በሚታዩ እንቅስቃሴዎች የቅዱስ ጊዮርጊስ የቀኝ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና የግራ መስመሮች የተሻለ ጫና መፍጠሪያነት ሲያገለግሉ ቢታዩም አሁንም ንፁህ የግብ ዕድል ግን ማግኘት አልተቻላቸውም። 67ኛው ደቂቃ ላይ የረዘመን ኳስ ሀሪሰን ከግብ ክልሉ ወጥቶ በሚገባ ሳያርቀው አብዱልከሪም ኒኪማ አግኝቶ ወደግብ ሲሞክር አክሊሉ አያናው ያወጣበት እንዲሁም 66ኛው ደቂቃ ላይ ቶማስ ስምረቱ ከኤልያስ ማሞ የተነሳን ቅጣት ምት በግንባሩ ሞክሮ ወደውጪ የወጣበት አጋጣሚዎች ብቻ ትኩረት የሳቡ ነበሩ። ከነዚህ ውጪ ሮበርትም ሆኑ ሀሪሰን እምብዛም ሳይጨነቁ ጨዋታው ተገባዷል። በጨዋታው መገባደጃ ላይ ኢ/ዳኛ በአምላክ ተሰማ 4 ደቂቃዎችን ከጨመሩ በኃላ በስቴድየሙ ሰዐት መሰረት ሰከንዶች ሲቀሩት የጨዋታውን ማብቂያ ፊሽካ በማሰማታቸው መሀል ሜዳ ላይ የቅጣት ምት አግኝተው የነበትሩ ቅዱስ ጊዮርጊሶች የመምታት ዕድል ባለማግኘታቸው ደጋፊዎች ተቃውሞ አሰምተዋል። በመጨረሻም ቡድኖቹም በአመቱ ለሁለተኛ ጊዜ ነጥብ ተጋርተው የወጡበትን ውጤት አስመዝግበዋል።የሸገር ደርቢ በቅርብ አመታት የተጠባቂነቱን ያህል ተመልካቹን የሚመጥን እንቅስቃሴ እየታየበት አይገኝም። በተከታታይ ከተደረጉ 5 ጨዋታዎችም ሶስቱ ያለ ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።ም/አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ” ጨዋታው ሁለት አይነት መልክ አለው።  በመጀመሪያው አጋማሽ እኛ በጣም ቀርፋፋ ነበርን። በሁለተኛው አጋማሽ ግን የተሻለ ለመንቀሳቀስ ሞክረናል። ነገር ግን በሙሉ ጨዋታው የሚገባንን ያህል ተጫውተናል ብዬ አላስብም። ”አሰልጣኝ ሀብተወልድ ደስታ“ጨዋታውን ለመቆጣጠር ሙሉ ለሙሉ ጥረት አድርገናል ማለት ይቻላል። የተሻለ ጨዋታም ተጫውተናል። ውጤቱም ይገባን ነበር። ሆኖም የጨዋታው አጋጣሚ ያሳየንን ነገር ተቀብለናል።”
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/31903
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
1af71c03eeb229f9d94a802e3acd9333
09fe8b538084bef67e43767f68f490ad
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ ሥራ እያደገ መጥቷል – ዚያድ ራድ አልሁሴን
ኮሚሽኑ  ከጊዜ  ወደ  ጊዜ  የሚያከናውነው ሥራ እያደገ መምጣቱን  የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ  መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዚያድ ራድ አልሁሴን ገለጹ ።ኮሚሽነር ዚያድ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ዋና ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር ጋር በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ በጄኔቫ ባደረጉት ውይይት ወቅት   በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝን ፣ እየተወሰዱ ስላሉ የሰብዓዊ መብት እርምጃዎችና   የኮሚሽኑ ክንውኖች በተመለከተ  ገለጻ ተደርጎላቸዋል ።ከፍተኛ ኮሚሽነር ዚያድ ራድ ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር ጋር ከተወያዩ በኋላ እንደገለጹት በኢትዮጵያ በስብዓዊ መብት  ጥሰት ምርመራ ሥራ ፣ በማረሚያና ፖሊስ ጣቢያዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝን  ለመሻሻል  የተሠራው ሥራ  ከጊዜ ወደ ጊዜ  እየላቀ መጥቷል ብለዋል ።በአገሪቱ  የተለያዩ የፖለቲካ  ፓርቲዎች የምርጫ  ሥርዓት ሁሉንም የፖለቲካ  ፓርቲዎች  ሊያግባባ በሚችል ሁኔታ ለማሻሻል የተጀመረው ሥራ  በበጎበት የሚጠቀስ መሆኑን  ኮሚሽነሩ አያይዘው ገልጸዋል ።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ዋና ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዛብሔር በበኩላቸው በአገሪቱ  በቅርቡ የተከሰተውን  ቀውስ ለማርገብና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ  ከጥር  2010 ጀምሮ  7ሺህ 200 የሚሆኑ ታራሚዎች እንዲለቀቁ መደረጋቸውን ተናግረዋል ።ቀደም ሲል በአማራ፣  በኦሮሚያና ደቡብ  ክልሎች  አንዳንድ ቦታዎች የተከሰቱ  ግጭቶች ላይ ምርመራ  ተደርጎ  ለፓርላማ  ሪፖርት  መደረጉንም  ጭምር  ዶክተር አዲሱ  አስረተድተዋል ።    የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን   የጀመራቸውን  መልካም ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል  እንዳለበት  አመልክተዋል ።    
ፖለቲካ
https://waltainfo.com/am/29700/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
a23716d1cfe8443455fe8e2dae25ea7e
6a10820582a7fcc99032f03f4704eaa7
ዛምቢያ 2017: የኢትዮጵያ U-20 ብሄራዊ ቡድን የመልስ ጨዋታውን ነገ ያደርጋል
ዛምቢያ ለምታሰናዳው የአፍሪካ ከ20 ዓመት ዋንጫ ለማለፍ በሚደረገው ማጣርያ የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የጋና አቻውን አዲስ በተገነባው የኬፕ ኮስት ስታዲየም ነገ ይገጥማል፡፡ብሄራዊ ቡድኑ ከማክሰኞ ጀምሮ በጋና የሚገኝ ሲሆን ወደ ጋና ከማቅናቱ በፊት ከማሊ ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 5-0 ተረትቷል፡፡ብላክ ሳተላይትስ በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት የጋና ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በመጀመሪያው ዙር ያጋጠማቸውን ሽንፈት ለመቀልበስ ወደ ሜዳ እንደሚቡ ተነግሯል፡፡በጋና ፕሪምየር ሊግ ለኩማሲው ክለብ አሻንቴ ኮቶኮ በውድድር ዓመቱ ድንቅ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው አጥቂው ዳዉዳ መሃመድ ጨዋታውን አሸንፈው ወደ ቀጣይ ዙር ማለፍ አላመማቸውን እንደሆነ ተናግሯል፡፡ “በመጀመሪያው ዙር ስለተጋጣሚያችን የነበረን መረጃ እምብዛም ነበር፡፡ ከጨዋታው በኃላ የኢትዮጵያን ጠንካራ እና ደካማ ጎን ለማወቅ ችለናል፡፡ ስንዘጋጅ የነበረው የኢትዮጵያ ድክመትን እንዴት መጠቀም እንችላለን የሚለው ላይ ነበር፡፡“እግርኳስ ስለሆነ ማንኛውም ነገር ሊያጋጥም ይችላል፡፡ እኔ ላለገባ እችላለው ኳስ አመቻችቼ ላቀብል እችላለው ዋናው ቁም ነገር ጋናን ወደ ቀጣዩ ዙር ማሳለፍ ነው፡፡”ዳዉዳ በክለብ ጨዋታ ያሳየው ብቃት በብሄራዊ ቡድኑ መድገም እንደሚፈልግም ጨምሮ ገልጿል፡፡ “ጠንክሬ ልምምዶችን እየሰራው ነው፡፡ በክለብ የነበረኝን ብቃት ወደ ብሄራዊ ቡድን ማምጣት እፈልጋለው” ብሏል፡፡የብላክ ሳተላይትስ አሰልጣኝ መስኡድ ዲዲ ድራማኒ ዳዉዳን ለአዲስ አበባው ጨዋታ ማካተታቸውን ተከትሎ ከኮቶኮ ክለብ ሃላፊዎች ከፍተኛ ትችት ሲደርስባቸው ነበር፡፡ ዲዲ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ከመምጣታቸው በፊት ኮቶኮን ለሁለት የጋና ፕሪምየር ሊግ አሸናፊነት አብቅተዋል፡፡ረዳት አሰልጣኙ ያው ፕሪኮ በበኩሉ ቡድኑ አዲስ አበባ ላይ የሰራቸውን ስህተቶች ላለመድገም ወደ ሜዳ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን  በመጀመሪያው ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ በአሜ መሃመድ ሁለት ግቦች 2-1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡(መረጃውን ለሶከር ኢትዮጵያ ያደረሰው የጋና ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የሚዲያ ሃላፊ ፍሬድሪክ አቼምፖንግ ነው)
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/12472
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
edabb5b7745ff8075593853eb0aebcfc
8ea0572a3fe62a1fe1ec41fc45e312f5
በከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ ላይ ማሻሻያ ተደረገ
አዲስ አበባ፡- የከባድ ጭነት ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት አጀንሲ አስታወቀ፡፡የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጅሬኛ ሂርጳ ትናንት በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የከተማዋን ትራፊክ እንቅስቃሴ ለማሳለጥና አሁን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡በተሻሻለው መመሪያ መሠረትም፤ ማንኛውም የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ከጠዋቱ 12፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት እና ከቀኑ ከ10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ካለው ጊዜ ውጪ መንቀሳቀስ የሚፈቅድ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በዚህም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በከተማዋ ውስጥ መዘዋወርና ማንኛውንም አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡በተጨማሪም፤ ቅዳሜ፤ እሁድና የበዓል ቀናት ማንኛውም የጭነት ተሽከርካሪ ያለምንም መንቀሳቀሻ ፍቃድ በየትኛውም ሰዓት ወደ ከተማዋ መግባትም ሆነ መንቀሳቀስ፤ እንዲሁም ዕቃ የመጫንና የማራገፍ ተግባር ማከናወን እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም፤ የከተማዋ ትራፊክ ፖሊስና የደንብና ቁጥጥር አካላት የተደረገውን ማሻሻያ በመረዳት እንደወትሮው ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ በከተማዋ ውስጥ ሰላማዊና ምቹ የሆነ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር ጥረት እንዲያደርጉ ዋና ዳሬክተሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ኤጀንሲው የመንገድ አጠቃቀም ሥርዓት የሚያሻሽል የጭነት፣ ማሽነሪዎችና መሰል ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 03/2011 መነሻ በማድረግ በከተማዋ የጭነት ተሽከርካሪዎች የሚፈጥሩትን ተፅዕኖ ለመቀነስ መመሪያ አዘጋጅቶ ከሰኔ 30/2011 ዓ.ም ጀምሮ በተግባር ላይ ማዋሉ ይታወሳል፡፡አዲስ ዘመን መስከረም 30
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=20480
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
f6a43b406079e2f34e4733f1197837ee
0e8b4f7e6dfec2b6d39b2a5036c0fcae
በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ መሆኑን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ኮሮና ቫይረስ፡ በዓለም ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሆነ\nወረርሽኙን ለመግታት ለሚደረገው ትንቅንቅም ጨለም ያለ ዜና ነው ተብሏል። እስካሁን ባለው መረጃ 53ሺ ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል፤ 210 ሺ ሰዎች ደግሞ እንዳገገሙ የዩኒቨርስቲው መረጃ ጠቁሟል። •በአማራ ክልል በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎችን ለመለየት ክትትል እየተደረገ ነው •ኢትዮጵያ፡ ሁለት ሰዎች ከኮቪድ-19 መዳናቸው ተገለፀ በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ቀዳሚ በሆነችው አሜሪካ በትናንትናው እለት መጋቢት 24፣ 2012 ዓ.ም አንድ ሺ 169 ሰዎች ሞተዋል። ለሰው ልጅ ጠንቅ የሆነው ኮቪድ- 19 የተከሰተው ከሶስት ወራት በፊት በቻይና፣ ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ ነው። የ34 አመቱ ዶክተር፣ ዶ/ር ሊ ዌንሊያንግ ቫይረሱን አስመልክቶ ለሌሎች የህክምና ባለሙያዎች ቢያስጠነቅቅም በምላሹ ግን የፖሊስ ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲደርሰው ሆኗል። ዶክተሩም በውሃን ከተማ በቫይረሱ የታመሙ ሰዎችን ሲንከባከብ ህይወቱን ተነጥቋል። •በኮሮናቫይረስ የወረርሽኝ 'ዘመን' ተስፋ የሚሰጡ 5 ነገሮች •በአማራ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የትምህርት ተቋማት ለመጠለያነት ተዘጋጁ ምንም እንኳን ከዩኒቨርስቲው የተገኘው መረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ጥር ከአንድ ሚሊዮን ትንሽ ከፍ ያለ ቢሆንም ቁጥሩ ግን ከዚያ በላይ ነው ተብሏል። ምክንያቱም ከአመዘጋገብ ስርዓት ጋር ተያይዞ ክፍተቶች በመታየታቸው ነው፤ በባለፈው ወር በበሽታው የተያዙ መቶ ሺ ሰዎችን ለመመዝገብ ከአንድ ወር በላይ ጊዜን ወስዷል። ከዚህ ቁጥር ውስጥ ሩብ የሚሆነው በአሜሪካ የተከሰተ ሲሆን ግማሽ የሚሆነው ደግሞ በአውሮፓ ያለውን ቁጥር ያሳያል። በትናንትናው ዕለት በስፔን ባለፉት ሃያ አራት ሰዓታት ብቻ 950 ሰዎች ሞተዋል። ከጣልያን በመቀጠል ብዙ ሰዎችን በኮሮናቫይረስ ባጣችው ስፔን፤ የምጣኔ ሃብት መዳሸቅ እያጋጠማት ሲሆን 900 ሺ የሚሆኑ ሰዎችም ስራቸውን አጥተዋል ተብሏል። በአሜሪካም በትናንትናው ዕለት 6.6 ሚሊዮን ሰዎች ስራቸውን በማጣታቸው የጥቅማጥቅሞች ይገባኛል ጥያቄዎች ቀርበዋል።
UNK
null
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/xlsum_amharic_summarization
dd7621ebc6826af4150b2731a289ca60
af8c313b28a79e1516d572dff8fe51e3
የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የሩጫ ስፖርት ኮከብ ኦስካር ፒስቶሪየስ
የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የሩጫ ስፖርት ኮከብ ኦስካር ፒስቶሪየስ የሴት ጓደኛውን በመግደል ወንጀል መጀመሪያ ላይ የተሰጠው የእሥራት ፍርድ ከእጥፍ በላይ የሚረዝም አዲስ ፍርድ ተሰጥቶታል።የደቡብ አፍሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችሎት ዛሬ ዓርብ በሰጠው ውሳኔ እስካሁን በእሥር ያሳለፈው ጊዜ ታስቦ አሥራ ሦስት ዓመት ከአምሥት ወር እንዲታሰር ፈርዶበታል።ዓቃቤ ሕግ የጠየቀው አሥራ አምስት ዓመት እንዲታሠር ነበር። ሁለት እግሮቹ የተቆረጡት የአካል ጉዳተኞች ኦሎምፒክ ሻምፒየን ፒስቶሪየስ ሪቫ ስቲንካምፕን በመግደሉ መጀመሪያ የተሰጠው የሥድስት ዓመት እሥራት ፍርድ በአስደንጋጭ ሁኔታ የቀለለ ነው ብሏል ።
ዓለም አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/south-african-court-doubles-pistorius-sentence-11-24-2017/4135249.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
c0f53e77cda4483f73e9cb24b12ace67
0e43198b3e900ba5a8d0c46b775b38dd
ሐሰተኛ የፓርኪንግ ደረሰኞች በኤጀንሲው ሥራ ላይ ጫና ፈጥሮበታል
አዲስ አበባ፡- በፓርኪንግ ሥራ ላይ ተሰማርተው ሐሠተኛ ደረሰኞች የሚጠቀሙ ነአካላት በኤጀንሲው ሥራ ላይ ጫና እየፈጠ ሩበት መሆኑንና መንግሥትን የሚገባውውን ገቢ እያሳጣው መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር ትራፊክና ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ። የፓርኪንግ ልማት አስተዳደር ዳይሬክተር ወይዘሮ ማዕርነት ገብረፃዲቅ በተለይም ለዝግጅት ክፍሉ እንደገለፁት፤ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ተደራጅተው በፓርኪንግ ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላት ሐሰተኛ ደረሰኞችን በማዘጋጀት አግባብነት የጎደለው ተግባር እያከናወኑ ነው። በዚህም የተነሳ በኤጀንሲው ሥራ ላይ ጫና ከማሳደሩም በላይ መንግሥት ማግኘት የሚገባው ን ገቢ እያሳጡ መሆኑን አብራርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ማስጠንቀቂያዎች ሲሰጧቸው ፈቃደኛ አለመሆንና የማስፈራራት ሙከራ እንደሚያደርጉም ገልፀዋል። ይህም ሥራውን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ ነው ብለዋል። ዳይሬክተሯ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት 500 ወጣቶች በፓርኪንግ ሥራ የተሰማሩ ሲሆን 50 ማህበራትንም አቅፈዋል፤ ለወጣቶችም ሰፊ የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በቂ ባይሆንም በከተማዋ ዘመናዊ የፓርኪንግ ሥርዓት ለመተግበር ‹‹ስማርት ፓርኪንግ›› የተሰኙ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ነው። ቀደም ሲል በመገናኛ አካባቢ የተገነቡ ስማርት ፓርኪንጎች በአንድ ጊዜ እስከ 200 ተሽከርካሪ እንደሚ ያስተናግዱም ጠቁመዋል። ችግሩን ለማቃለል ሲባልም በቀጣይ በከተማዋ ውስጥ በተመረጡና ከማስተር ፕላኑ ጋር የተናበቡ 70 የሚሆኑ ቦታዎች ላይ ዘመናዊ የፓርኪንግ ግንባታዎችን ለማከናወን ታቅዷል። በአሁኑ ወቅት ዘመናዊ ፓርኪንግ ሥራ ዎች ባለመከናወናቸው መንገዶች የፓርኪንግ አገልግሎት እየሰጡ ነው። መንገዶቹን ከፓሪክንግ ነፃ ለማድረግ ቢታቀድም ካለው ችግር አኳያ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም። በተለይም የፓርኪንግ እጥረት እና የሚመለከታቸው አካላት ትብብር አናሳ መሆን ችግሩን እንዳባባሰው ወይዘሮ ማዕርነት ገልፀዋል። ስማርት ፓርኪንጎችን ለማልማት ከመንግሥት ባሻገር ባለሃብቱ እንዲያለማ አመቺ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ በቀጣይ በከተማዋ 10 ቦታዎች ላይ በጋራ የማልማት ውጥን መኖሩን አብራርተዋል። በዚህም ረገድ ባለሃብቱ በንቁ ሁኔታ እንዲ ሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል። ከዚህም ባሻገር ዘመናዊ የፓርኪንግ ሥርዓት በከተማዋ ውስጥ እንዲስፋፋና ህገ ወጥ አሠራሮች እንዲቃለሉ የመገናኛ ብዙሃን ግንዛቤ በመፍጠርና ህግ አስከባሪዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲ ወጡም ዳይሬክተሯ ጠይቀዋል።አዲስ ዘመን ቅዳሜ ህዳር 6/2012ክፍለዮሐንስ አንበርብር
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=22632
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
ef692125b37e3966db511d307a2e494e
ac28d574fd7b89fac4045adb0b0b4bf8
የአውሮፓ ህብረትና ብሪታኒያ የንግድ ስምምነት ላይ ለመድረስ ውይይታቸውን ዳግም ሊጀምሩ ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረትና ብሪታኒያ ከፍቺ በኋላ በሚኖረው የንግድ ሂደት ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ ያቋረጡትን ውይይት በብራሰልስ ሊጀምሩ ነው።ብሪታኒያ እና የአውሮፓ ህብረት በአሳ የማስገር መብት እና በንግድ ውድድር ህግ ላይ ያላቸው ልዩነት እንደቀጠለ መሆኑ ይነገራል።ብሪታኒያ ከህብረቱ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ አሁንም ጊዜ እንዳለ ስትገልፅ በአውሮፓ ህብረት በኩል ይህ ተስፋ ብዙም የለም።ከዚህ ጋር ተያይዞም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌይን እና ጠቅላይ የብሪታንያው ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ ካልደረሱ ህብረቱ እና ብሪታኒያ በምርቶች ላይ ቀረጥ መጣል እና የድንበር ቁጥጥር እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል።የኮሚሽኑ ዋነኛ ተደራዳሪ ማይክል ባርነር ለአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች በድርድሩ የልዩነት ነጥቦች ዙሪያ ማብራሪያ መስጠታቸውን ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።
ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.fanabc.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8b%8d%e1%88%ae%e1%8d%93-%e1%88%85%e1%89%a5%e1%88%a8%e1%89%b5%e1%8a%93-%e1%89%a5%e1%88%aa%e1%89%b3%e1%8a%92%e1%8b%ab-%e1%8b%a8%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%8b%b5-%e1%88%b5%e1%88%9d/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
3f0a880c332a690473df081e42949663
06a5c1a57485d58312dc32378df50e62
ቅድመ ዳሰሳ | ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
የሊጉ የረጅም ጊዜ የግንኙነት ታሪክ ያላቸው ቡድኖችን የሚያገናኘውን የነገ ጨዋታ የተመለከቱ ጉዳዮችን አንስተናል።ሀዋሳ ከተማ ደካማ አጀማመሩን ከማቅናት ባለፈ ለቀጣይ ሳምንታት የሚሆን የስነ ልቦና ስንቅ የሚሸምትበት አልያም የውጤት እጦቱን የሚያባብስበትን ጨዋታ ነገ የሚያደርግ ይሆናል። ቡድኑ የተሻለ ልምድ አላቸው የሚባሉ ተጫዋቾቹን ይዞ ወደ ሜዳ መግባት በቻለበት የጊዮርጊሱ ጨዋታም ተዳክሞ ታይቷል። የኋላ መስመሩ ለፈጣን አጥቂዎች የተጋለጠ ሆኖ መታየቱ ደግሞ እንደነገው ዓይነት ጨዋታዎች ላይ መቸገሩን እንዳይቀጥል የሚያሰጋ ሆኗል። መሀል ሜዳ ላይም በተጋጣሚ የአማካይ ክፍል የሚወሰድበት ብልጫ ፈጣኖቹን የፊት አጥቂዎች ያለ በቂ ዕድል ሲያስቀራቸው ይታያል። አልፎ አልፎ የሚገኙ መልካም ዕድሎችንም ወደ ግብ ለመቀየር አለመቻሉ ከኋላ ኳስ የሚመሰርተው የነገ ተጋጣሚው በራሱ ሜዳ ላይ የሚሰራቸውን ስህተቶች በመጠቀም ረገድ ዕንቅፋት ሊሆንበት ይችላል። በሌላ በኩል በሦስተኛው ሳምንት የቡድኑ ጨዋታ በመስመር አጥቂነት ዮሀንስ ሴጌቦ ያሳየው እንቅስቃሴ ለአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ቡድን ተስፋን የሚጭር ነው። በማጥቃት መስመሩ ላይ የዮሃንስ በልበ ሙሉነት ከተከላካዮች ጋር የመጋፈጥ እንዲሁም በቀጥታ ሙከራዎችን የማድረግ ድፍረት መስፍን ታፈሰም ለነገ የሚደርስ ከሆነ ቡድኑ ፊት ላይ የተሻለ ለውጥ ሊያሳይ እንደሚችል ይጠበቃል።ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን ያሳካው ኢትዮጵያ ቡና በዋንጫ ፉክክር ውስጥ እንደሚዘልቅ የሚያሳይበትን ድል ለማግኘት ሀዋሳን ይገጥማል። በአወዛጋቢው የድሬዳዋ ጨዋታ አሸንፎ መውጣት የቻለው ኢትዮጵያ ቡና ወሳኝ ተጫዋቾቹን በጉዳት አጥቶም ሦስት ነጥቦችን ማስካቱ በበጎ ጎኑ የሚታይ ነው። በአንፃራዊነት ደከም ብለው ከታዩ ቡድኖች መካከል የሆነው ሀዋሳ ከተማን መግጠሙ አሸንፎ የመውጣት ግዴታ ውስጥ ስለሚከተው ግን ጨዋታውን በጫና ውስጥ ሆኖ ሊያደርግ ይችላል። በድሬዳዋው ጨዋታ ኳስ ከኋላ መስርቶ ሲወጣ የሚፈጠርበትን ጫና በመቅረፉ ረገድ እንደቀደሙት ጨዋታዎች ያልነበረው የቡድኑ የመሀል ክፍል በአንፃሩ ከመስመር ተከላካዮች ጋር የሚከውናቸው ቅብብሎች ክፍተቶችን ሲያስገኙለት ታይቷል። ለነገው ተጋጣሚውም መሀል ላይ ተጫዋቾችን በርከት አድርጎ ለጨዋታው ሊቀርብ መቻሉ በቡና በኩል ተመሳሳይ ግብረ መልስ እንድንጠብቅ የሚያደርግ ነው። በሌላ በኩል ፊት ላይ የሀብታሙ ታደሰ ወደ ግብ አስቆጣሪነቱ መምጣት ወደ መጨረሻ ዕድልነት ተቀይረው የሚባክኑ ካሶችን ውጤት ላይ በማዋሉ በኩል ለቡድኑ ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል። በዚህ ላይ የአቡበከር ናስርን ግልጋሎት በሙሉ ጤንነት የሚያገኝ ከሆነ የቡድኑ የፊት መስመር ስልነት እንደሚጨምር ይታሰባል።በጨዋታው ሀዋሳ ከተማ በጊዮርጊሱ ጨዋታ ያልነበረው ምኞት ደበበን ከጉዳት መልስ ሲያገኝ በኮቪድ ምክንያት በቡድኑ ውስጥ ያልነበሩ ሁለት ተጫዋቾችም አገግመውለታል። በሌላ በኩል የቡድኑ ቁልፍ አጥቂ መስፍን ታፈሰ እና ተባረክ ኢፋሞ መድረስ አጠራጣሪ ሲሆን ሀብታሙ መኮንን በጉዳት አለልኝ አዘነ በቅጣት ከኃይቆቹ ስብስብ ውጪ ናቸው። ተመስገን ካስትሮን በቅጣት በሚያጣው የኢትዮጵያ ቡና ቡድን ውስጥ ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን ፣ ሚኪያስ መኮንን እና ኢብራሂም ባዱ በጉዳት ምክንያት ከነገው ጨዋታ ውጪ ናቸው። አቤል ማሞ ፣ ወንድሜነህ ደረጀ እንዲሁም የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች አቡበከር ናስር ከጉዳት መመለስ ለቡና መልካም ዜና ሆኗል።እርስ በእርስ ግንኙነት– ሊጉ በአዲስ ፎርማት ከተጀመረበት 1990 ጅምሮ ሳይወርዱ የቆዩት ሁለቱ ቡድኖች ከየትኛውም ቡድን በበለጠ 42 ጊዜ ተገናኝተዋል።– የእርስ በእርስ ውጤታቸው በመሀላቸው ያለውን የፉክክር ሚዛናዊነት የሚያሳይ ነው። በእስካሁኑ የ42 ጊዜ ግንኙነታቸውም በ16 አጋጣሚዎች አቻ ተለያይተዋል። ኢትዮጵያ ቡና 14 ሀዋሳ ደግሞ 12 ጊዜ ድል አስመዝግበዋል።– በጥቂት አጋጣሚዎች ካልሆነ በቀር ጎል የማያጣው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ 95 ጎሎች ሲቆጠሩበት ኢትዮጵያ ቡና 52 ጊዜ ኳስ እና መረብን በማገናኘት የበላይ ነው። ሀዋሳ ከተማ ደግሞ ሦስት የፎርፌ ግቦችን ጨምሮ 43 ግቦችን ማስመዝገብ ችሏል።ግምታዊ አሰላለፍሀዋሳ ከተማ (4-3-3)ሜንሳህ ሶሆሆዳንኤል ደርቤ – ምኞት ደበበ – ላውረንስ ላርቴ – ደስታ ዮሃንስሄኖክ ድልቢ – ጋብርኤል አህመድ – ኤፍሬም ዘካሪያስኤፍሬም አሻሞ – ብሩክ በየነ – ዮሀንስ ሴጌቦኢትዮጵያ ቡና (4-3-3)ተክለማሪያም ሻንቆኃይሌ ገብረትንሳይ – ወንድሜነህ ደረጄ – አበበ ጥላሁን – አስራት ቱንጆታፈሰ ሰለሞን – ዓለምአንተ ካሳ – አማኑኤል ዮሃንስአቤል ከበደ – ሀብታሙ ታደሰ – አቡበከር ናስር
ስፖርት
https://soccerethiopia.net/football/62596
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
63715925db5c89fdbbdce0d93ee40e34
afd1ca09ff7b6cce831a422b9f82faeb
ጁንታው ከመከላከያ ዘርፎ ለጥፋት ዓላማ ይጠቀምባቸው የነበሩ መሳሪያዎች ተጠግነው ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ናቸው
ጌትነት ተስፋማርያምጁንታው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ዘርፎ ለጥፋት ዓላማው ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ መሳሪያዎች ተጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ላይ መሆናቸው ተገለጸ። የምዕራብ ግንባር የጥገና ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ተስፋዬ እንደገለጹት፤ ጁንታው ከመከላከያ ሰራዊት ዘርፎ ለጥፋት ዓላማው ሲጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ የሀገር ሀብቶች ከየመንገዱ እየተሰበሰቡ ተጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ላይ ናቸው። እንደ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ገለጻ፤ ጁንታው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ሲከፍት ታንኮች፣ መድፎች እና በርካታ ከባድ መሳሪያዎችን ዘርፏል። ከባድ መሳሪያዎቹን ከዘረፈ በኋላ ይዞ ለመዋጋት ቢያስብም በመከላከያ ሰራዊቱ ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ እና በአየር ኃይል ኢላማቸውን የጠበቁ እርምጃዎች ምክንያት መሳሪያዎቹን እየጣለ ሊፈረጥጥ ግድ ሆኖበታል። አንዳንድ መሳሪያዎቹን በከፊል ሲያወድም የተቀሩትን ግን በየአስፓልት ዳሩ እና በየጫካው አስቀምጦ እግሬ አውጪኝ ብሏል። ከሃዲው ቡድን ከመከላከያ ሰራዊቱ የደረሰበትን እርምጃ መቋቋም ባለመቻሉ ከሽሬ አንስቶ እስከ ሽራሮ እና ተንቤን ድረስ በየመንገዱ ያንጠባጠባቸው ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያየ አቅም ያላቸው መድፎች፣ ሎቤዶች እና ቢኤም መሳሪያዎች ተጓጉዘው ወደሽሬ የጥገና ማዕከል እየገቡ ይገኛሉ ያሉት ሌተናል ኮሎኔል አባተ፣ የጥገና ባለሙያዎችም መሳሪያዎቹን በመፈተሽ ዳግም ወደስራ ለማስገባት በመረባረብ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በርካታ ከባድ መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎችም ከጥገናቸው በኋላ የተሳካ ሙከራ ተደርጎባቸው ወደስራ መመለሳቸውን ሌተናል ኮሎኔል አባተ ተስፋዬ ተናግረዋል። ለመሳሪያዎቹ ጥገና አስፈላጊው ዝግጅት እና የመለዋወጫ አቅርቦት በሀገር ውስጥ መኖሩን የገለጹት ሌተናል ኮሎኔል አባተ፤ የመከላከያ ሰራዊቱ ንብረቶችን አጠቃላይ የጥገና ስራ ሙሉ በሙሉ በኀገር ውስጥ ባለሙያዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ጁንታው አስቀድሞ ለጥፋት ዓላማው ዝግጅት በማድረጉ ከባድ መሳሪያዎችን የሚጠግኑ ባለሙያዎችንም ከሰራዊቱ ጋር አፍኖ መውሰዱን አስታውሰው፤ መከላከያ ሰራዊት ባደረገው ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ ባለሙያዎቹን ከጁንታው ቡድን ነጻ ማውጣት መቻሉንም ገልጸዋል። አሁን ላይ ከተለያዩ ከተሞች የተሰባሰቡ የሰራዊቱ ባለሙያዎች አገልግሎቱን በተሳካ ሁኔታ በመስጠት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። እንደ ሌተናል ኮሎኔል አባተ ገለጻ፤ ጁንታው ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ከፈጸመ የሰሜን እዝ የሰራዊቱ ንብረት የሆኑ በርካታ ከባድ መሳሪያዎችን ዘርፎ መውሰዱ ይታወሳል። ከባድ መሳሪያዎቹንም ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ለጥቂት ቀናት ህዝብ እና ሀገር ለማሸበር ሲጠቀምባቸው ቆይቷል። በመከላከያ ሰራዊት በቅንጅተ በወሰዱት እርምጃ መሳሪያዎቹ ተጠግነው ዳግም ለአገልግሎት መብቃታቸው የመልሶ ግንባታ እና የማደራጀት ስራዎች በተሳካ ሁኔታ በመከናወን ላይ ናቸው። ሌተናል ኮሎኔል አባተ እንደገለጹት፤ ጁንታው በሀገር ሀብትና ጉልበት የተሰሩ መንገዶችን ሲቆፍርባቸው የነበሩ ዶዘሮች እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እንዳይበላሹ የጥበቃ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። በጁንታው የተበላሹ መንገዶችም ጊዜያዊ ጥገና ተደርጎላቸው ከባድ ተሽከርካሪዎች የሚፈለግባቸው ግዳጅ እየተወጡ ይገኛል።አዲስ ዘመን ታህሳስ 6/2013
ሀገር አቀፍ ዜና
https://www.press.et/Ama/?p=37380
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
8573f6f84efd8cb84db2bf31ced78178
683629b907c058e09e17ece47090ca98
ምርጫ ቦርድ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሰረዘ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማለትም የመላው ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን እና የሲዳማ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን መሰረዙን አስታውቋል።ቦርዱ በታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሰረት ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዲያሟሉ ከተጠየቁት መካከል የሚከተሉት አራት ፓርቲዎች መስፈርቱን እንዳሟሉ አስታውቋል።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://waltainfo.com/am/%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-%e1%89%a6%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%88%98%e1%88%b5%e1%8d%88%e1%88%ad%e1%89%b6%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%8b%ab%e1%88%8b%e1%88%9f%e1%88%89-%e1%88%81%e1%88%88%e1%89%b5-%e1%8b%a8/
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
fdf7423415f0f7415670bee6430e36b6
87f0318b9c8f5ebe0b98ed8791742e21
ሥሜት ምንድ ነው? .. ከልክ ያለፈ ሥሜት፣ ሃሳብና አንድምታዎቹ
ሃኪምዎን ይጠይቁ፥ በሰው ልጅ የተፈጥሮ ሥሜት፣ ምንነት። ጠባይና የስነ ልቦና ጤና - አለፍ ብሎም ከጤናማው ምሕዋር ውጭ የሚታዩ ሁኔታዎችን የሚመረምር አዲስ ተከታታይ ቅንብር ነው።የአንጎልና የሥሜትን ቁርኝት፤ ስለ አንድ ነገር ያለን ወይም በውስጣችን ያደረ “ከልክ ያለፈ” ወይም “የተጋነነ” ሥሜት በማሕበረሰብ ደህንነት ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተፅዕኖ የሚመለከቱ አወያይ ጭብጦችም ይመለከታል።ለጥያቄዎቹ ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን፥ የዘወትር የፕሮግራሙ ተባባሪ፤ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የሜዮ ክሊኒክ የነርቭና የአዕምሮ ህክምና ልዩ ባለሞያና በህክምና ትምህርት ቤቱ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ ናቸው።
ሀገር አቀፍ ዜና
https://amharic.voanews.com//a/understandin-emotions-and-implications-with-prof-yonas-geda-voa-alula-kebede-may-07-2019/4912701.html
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
f97ff74cc9621af913ca6412e5c72311
8a2b557b69fa81e5cbbfd277ee0b4a8e
ኮሮና እና አለማችን በሳምንቱ
  ቁጥሩ ማሻቀቡን ቀጥሏል...መሽቶ በነጋ ቁጥር አለም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የደረሱባትን የተለያዩ ጥፋቶች የሚገልጹ እጅግ አስደንጋጭና ተስፋ አስቆራጭ ቁጥሮችን መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡አንዳች መላ ሳይገኝለት በአለም ዙሪያ በስፋት መሰራጨቱን የቀጠለው ኮሮና ቫይረስ እስካለፈው ሐሙስ አመሻሽ ድረስ በመላው አለም በሚገኙ 211 አገራትና ግዛቶች ውስጥ ከ3,249,792 በላይ ሰዎችን ሲያጠቃ ከ229,442 በላይ የሚሆኑትንም ለሞት እንደዳረገ ተነግሯል፡፡በቫይረሱ የተጠቁባት ዜጎቿ ቁጥር በሳምንቱ በሚሊዮን መቆጠር በጀመረባት አሜሪካ እስካለፈው ሐሙስ አመሻሽ 1,067,382 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ፣ ከ61,849 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ለሞት መዳረጋቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ከአሜሪካ በመቀጠል ስፔን 239,639፣ ጣሊያን 203,591፣ ፈረንሳይ 166,420፣ እንግሊዝ 165,221 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁባቸው ቀዳሚዎቹ አምስት የአለማችን አገራት ሆነዋል፡፡ከ61,849 በላይ ሰዎች ከሞቱባት አሜሪካ በመቀጠል፣ ጣሊያን በ27,682፣ እንግሊዝ በ26,097፣ ስፔን በ24,543፣ ፈረንሳይ በ24,087 የሟቾች ቁጥር እንደ ቅደም ተከተላቸው በርካታ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ለሞት የተዳረጉባቸው ቀዳሚዎቹ አምስት የአለማችን አገራት መሆናቸውንም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ግማሹ የአለማችን ሰራተኛ ስራ ሊያጣ ይችላልበመላው አለም ከሚገኙ ሰራተኞች ግማሹ ወይም ከ1.5 ቢሊዮን በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ቀውስ ጋር በተያያዘ የሚተዳደሩበትና ኑሯቸውን የገቢ ምንጫቸው ሊደርቅና ለከፋ ኑሮ ሊዳረጉ እንደሚችሉ የአለም የሰራተኞች ድርጅት አስጠንቅቋል፡፡በኮሮና ሳቢያ ክፉኛ ተጎጂ ይሆናሉ ተብለው ከሚጠበቁት ሰራተኞች መካከል መደበኛ ባልሆነው ዘርፍ፣ በምርትና በምግብ አገልግሎቶች ኢንዱስትሪዎች ተቀጥረው የሚሰሩ እንደሚገኙበት የገለጸው ድርጅቱ፣ ኮሮና በተከሰተበት የመጀመሪያው ወር ብቻ መደበኛ ባልሆነው ዘርፍ የሚሰሩ 2 ቢሊዮን ሰዎች ገቢያቸው በአማካይ በ60 በመቶ ያህል መቀነሱንም አስታውሷል፡፡አፍሪካ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠር ማዕከል ባወጣው መረጃ መሰረት እስካለፈው ሐሙስ አመሻሽ ድረስ በ52 የአፍሪካ አገራት ከ35,371 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲጠቁ፣ የሟቾች ቁጥር ደግሞ ከ1,534 አልፏል፤ ከህመሙ ያገገሙት ደግሞ ከ11,727 በላይ ደርሰዋል፡፡እስካለፈው ረቡዕ ድረስ ከ5 ሺህ 42 በላይ ሰዎች ባይረሱ የተጠቁባት ግብጽ በአህጉሩ ብዙ ሰዎች የተጠቁባት ቀዳሚዋ አገር ሆና የተቀመጠች ሲሆን፣ ደቡብ አፍሪካ ከ4 ሺህ 996 በላይ፣ ሞሮኮ 4 ሺህ 246፣ አልጀሪያ ከ3ሺህ 649 በላይ፣ ካሜሮን 1 ሺህ 705 ሰዎች የተጠቁባቸው ተከታዮቹ የአፍሪካ አገራት መሆናቸው ተነግሯል፡፡ከአፍሪካ አገራት በኮሮና ቫይረስ ሟቾች ቁጥር አልጀሪያ በ437 በቀዳሚነት ስትቀመጥ፣ ግብጽ በ359፣ ሞሮኮ በ163፣ ደቡብ አፍሪካ በ93፣ ካሜሩን በ58 ይከተላሉ ተብሏል፡፡በናይጀሪያ ከ40 በላይ የህክምና ባለሙያዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸውን የዘገበው ዴይሊ ሞኒተር፣ ከዚህ ቀደም 3 የህክምና ባለሙያዎች በኮሮና ሳቢያ ለሞት መዳረጋቸውንና ይህም ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን አገራዊ ጥረት እያሰናከለው እንደሚገኝ ገልጧል፡፡የጊኒ ቢሳኡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑኖ ጎሜዝ ናቢያም እና ሶስት የካቢኔ አባላት በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ባለፈው ማክሰኞ በተደረገላቸው መረጋገጡ የተዘገበ ሲሆን፣ ከአለማችን እጅግ ግዙፍ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች አንዱ የሆነውና ከ220 ሺህ በላይ ስደተኞች የሚገኙበት የኬንያው ዳባብ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ከፍተኛ ስጋት ከሰሞኑ ዝግ መደረጉንና ምንም ሰው እንዳይገባና እንዳይወጣ መታገዱን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡የኡጋንዳ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ስለኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በሚል እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ዶላር ወስደው እንደነበር ያስታወሰው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ከሰሞኑ ግን አባላቱ የወሰዱትን 2.6 ሚሊዮን ዶላር ያህል አጠቃላይ ገንዘብ በአስቸኳይ እንዲመልሱ በፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ መታዘዛቸውን ዘግቧል፡፡በዚህ የጭንቅ ወቅት ባልተገባ ሰበብ የህዝብ ገንዘብ የተቀበሉትን የምክር ቤቱ አባላት “ህሊና የለሾች” ሲሉ የተቹት ፕሬዚዳንት ሜሴቬኒ በአንጻሩ እሳቸው ከሚያገኙት መደበኛ ወርሃዊ ደመወዝ ግማሹን ለኮሮና መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች በስጦታ እንደሚያበረክቱ አስታውቀዋል፡፡ኬንያውያን በበኩላቸው ለኮሮና ወረርሽኝ የተመደበውን 37 ሺህ ዶላር ያህል የህዝብ ገንዘብ የጤና ሚኒስትር ሰራተኞች ለሻይ ቡና እና ለሞባይል ካርድ መግዣ እያዋሉት ነው በሚል በማህበራዊ ድረገጾች ከፍተኛ ተቃውሞ በማሰማት ላይ እንደሚገኙ ኦልአፍሪካን ኒውስ ዘግቧል፡፡የዛምቢያ መንግስት ኮሮና ቫይረስን በቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቁልፍ ሚና ለሚጫወቱ የህክምና ባለሙያዎች የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጥ ማስታወቁ ተዘግቧል፡፡በማዳጋስካር መዲና አንታናናሪቮ ዜጎች ከቤታቸው ውጭ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ሁሉ የፊት ጭምብል እንዲያደርጉ የሚያስገድድ መመሪያ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፣ ጭምብል ሳያደርጉ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ዜጎች መንገዶችን በማጽዳት እንደሚቀጡ ተዘግቧል፡፡1 ሚ. ያልተፈለጉ እርግዝናዎች፤ 15 ሚ. የቤት ውስጥ ጥቃቶችከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በመላው አለም እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ከቤት እንዳይወጡ መታገዳቸው 1 ሚሊዮን ያህል ያልተፈለጉ እርግዝናዎች እንዲከሰቱ እንዲሁም የቤት ውስጥ ጥቃቶች በ20 በመቶ ያህል እንዲጨምሩ ሰበብ ሊሆን እንደሚችል ተመድ አስጠንቅቋል፡፡አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው 114 የአለማችን አገራት 44 ሚሊዮን ያህል ሴቶች ኮሮና በሚፈጥራቸው ቀውሶች ሳቢያ የእርግዝና መከላከያዎችን ላያገኙ እንደሚችሉና ይህም ከ1 ሚሊዮን በላይ ያልተፈለጉ እርግዝናዎች ሊያስከትል እንደሚችል የጠቆመው ድርጅቱ፣ 13 ሚሊዮን ልጃገረዶች በግዳጅ ወደ ትዳር ሊገቡ፣ 2 ሚሊዮን ሴት ህጻናት ግርዛት ሊፈጸምባቸው እንደሚችልም አስታውቋል፡፡ከኮሮና የቤት ውስጥ መዋል ገደቦች በኋላ በበርካታ የአለማችን አገራት የቤት ውስጥ ጥቃት አቤቱታዎች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን ጠቅሶ ሰዎች ለሶስት ወራት ያህል ከቤት ውስጥ እንዳይወጡ መታገዳቸው በአለማቀፍ ደረጃ ተጨማሪ 15 ሚሊዮን የቤት ውስጥ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ ሊያደርግ እንደሚችል የጠቆመው ተቋሙ፣ ይህም በተለይ በሴቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አመልክቷል፡፡“ሰላሳ አራቱ”ዙሪያ ገባው አለም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ጭንቅ ውስጥ በወደቀበት በዚህ የመከራ ወቅት፣ እስከ ትናንት በስቲያ ድረስ ቫይረሱ ድንበራቸውን አልፎ ያልገባባቸው 34 የአለማችን ሉዑዋላዊ አገራትና ግዛቶች እንዳሉ ሮይተርስ አስነብቧል፡፡በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ከተሰጣቸው 247 የአለማችን አገራትና ግዛቶች መካከል እስካለፈው ሚያዝያ 12 ቀን ድረስ ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የተረጋገጡት አገራት 213 መሆናቸውን ያስታወሰው ሮይተርስ፣ ከእነዚህ አገራትና ግዛቶች መካከል በኮሮና ቫይረስ ሰዎች ለሞት የተዳረጉባቸው 162 መሆናቸውንም አክሎ ገልጧል፡፡እስከተጠቀሰው ዕለት ድረስ አንድም ሰው በቫይረሱ እንዳልተጠቃባቸው ከተነገሩት 34 አገራትና ግዛቶች መካከል ኮሞሮስ፣ ሌሴቶ፣ ተርኬሚኒስታንና የሶሎሞን ደሴቶች እንደሚገኙበት የጠቆመው ዘገባው፣ ያም ሆኖ ግን አንድም ሰው በቫይረሱ አልተያዘም ማለት ቫይረሱ ወደ አገራቱ አልገባም ማለት እንዳልሆነ አመልክቷል፡፡ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች እንዳሉ ካስታወቁ በኋላ በሂደት ቫይረሱን ማጥፋት መቻላቸውንና ነጻ መሆናቸውን ያወጁ አምስት የአለማችን አገራትና ግዛቶች አንጉሊያ፣ ግሪንላንድ፣ የካረቢያን ደሴቶች፣ የመን፣ ሴንት ባርትስና ሴንት ሉሲያ መሆናቸውንም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡ አሜሪካየአለም ቀንድ የሆነው የአሜሪካ ኢኮኖሚ ዕድገት በመጀመሪያው ሩብ አመት የ4.8 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱንና ይህም ካለፉት አስር በላይ አመታት ወዲህ እጅግ የከፋው ነው መባሉን የዘገበው ብሉምበርግ፣ አንዳንድ ባለሙያዎችም የኢኮኖሚ እድገቱ በመጪዎቹ ሶስት ወራት ከ30 በመቶ እና ከዚያ በላይ ሊቀንስ እንደሚችል መተንበያቸውን አመልክቷል፡፡በአሜሪካ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ለስራ አጥነት የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ከ30 ሚሊዮን በላይ መድረሱንና ይህም በአገሪቱ ታሪክ እጅግ ከፍተኛው ቁጥር እንደሆነ ዘገባው ገልጧል፡፡ከኮሮና መስፋፋት ጋር በተያያዘ የእንቅስቃሴ ገደብና የስራ መቀዛቀዝ ሳቢያ በ2020 የመጀመሪያው ሩብ አመት የቻይና ኢኮኖሚ እድገት በ6.8 በመቶ መቀነሱን ያስታወሰው ዘገባው፣ የጀርመን መንግስት በበኩሉ በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቀው የ6.3 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ቅናሽ ሊገጥመው እንደሚችል ባለፈው ረቡዕ ማስታወቁንም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ በመጀመሪያው ሩብ አመት ሽያጬ በ26 በመቶ የቀነሰበትና 17 ቢሊዮን ዶላር ያጣው የአሜሪካው የአውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ በቅርቡ ከደረሰበት ቀውስ እና ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በተፈጠረበት የስራ መቀዛቀዝ ሳቢያ 15 ሺህ የሚደርሱ ሰራተኞችን ከስራ ገበታቸው እንደሚያሰናብት ከሰሞኑ ይፋ አድርጓል፡፡“የኮሮና ፖለቲካ”ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ቻይናን ተጠያቂ ሲያደርጉ የሰነበቱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ረቡዕ ደግሞ፣ በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ ከአሜሪካ የእጇን ታገኛለች ሲሉ የዛቱባትን ቻይና በቀጣዩ ምርጫ ሽንፈትን እንድጎነጭላት አሳር መከራዋን እያየች ነው ሲሉ መክሰሳቸውን ሮይተርስ ተዘግቧል፡፡አለም ስለወረርሽኙ ቀድሞ እንዲያውቅ አላደረገችም በሚል በወነጀሏትና ቀደም ብለው የንግድ ጦርነት ባወጁባት ቻይና ላይ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የራሳቸውን እርምጃ እንደሚወስዱ የተናገሩት ትራምፕ፣ ቻይና እኔ እንድሸነፍላትና ዲሞክራቱ ጆ ባይደን እንዲያሸንፍ የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም፤ ይህ ግን በፍጹም የሚሆን አይደለም ምክንያቱም አሜሪካውያንን ማንን እንደሚመርጡ ጠንቅቀው ያውቃሉ ሲሉም ተናግረዋል ትራምፕ፡፡በሌላ በኩል ደግሞ ከኮሮና ጋር በተያያዘ አለማቀፍ ምርመራ እንዲካሄድ አበክራ ስትጠይቅ የነበረችው አውስትራሊያ፣ ከሰሞኑም ኮሮና ቫይረስ መቼ፣ የት፣ እንዴት እንደተቀሰቀሰ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ በድጋሜ ጥሪ ማቅረቧ ተዘግቧል፡፡የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ኮሮና በምን መልኩ እንዲህ አለምን ሊያጥለቀልቅ እንደቻለ በተጨባጭ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ትክክለኛ የምርመራ ውጤት ከገለልተኛ አካል መቅረቡ ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ ቢናገሩም፣ በአውስትራሊያ የቻይና አምባሳደር በበኩላቸው ነገሩ በገለልተኛ አካል ይጣራ መባሉን ለቃውመውታል፤ አልፎ ተርፎም አገራቸው የአውስትራሊያን ምርቶች ከመግዛት ልትታቀብ እንደምትችል ማስፈራሪያ ቢጤ ጣል አድርገዋል፡፡በሌላ ዜና ደግሞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ኩባውያን የህክምና ዶክተሮችን ለኮሮና ህክምና ድጋፍ እንዲሰጧቸው ፈቅደው ወደ ግዛታቸው በማስገባታቸው ሳቢያ ደቡብ አፍሪካን እና ኳታርን መተቸታቸው ተዘግቧል፡፡ኮሚኒስቷ ኩባ ከወረርሽኙ የራሷን ትርፍ ለማጋበስ የምትለፋ አገር ናትና የእሷን ዶክተሮች መቀበላችሁ አይበጃችሁም ወደመጡበት ብትሸኙዋቸው ይሻላችኋል ሲሉ ምክር መለገሳቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡አስደንጋጭ ቁጥሮች - የ“ሬምዴስቪር” ተስፋኢንተርናሽናል ሪስኪዩ ኮሜቴ የተባለው አለማቀፍ ተቋም ባለፈው ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ ኮሮና ቫይረስ በአለማችን 34 አገራት ውስጥ ብቻ 1 ቢሊዮን ያህል ሰዎችን ሊያጠቃና 3.2 ሚሊዮን ሰዎችነም ለሞት ሊዳርግ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ ተቋሙ ያወጣውን መግለጫ ጠቅሶ ቪኦኤ እንደዘገበው፣ ኮሮና ቫይረስ አፍጋኒስታን፣ ሶርያና የመንን ጨምሮ በቀውስ አዙሪት ወይም በጦርነት ውስጥ በሚገኙ 34 አገራት ውስጥ የሚደርሰውን ጥፋት ለመቀነስ ሁሉም ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ፣ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ባለፈው ሐሙስ ማለዳ ከወደ አሜሪካ የተሰማው በጎ ዜና በብዙዎች ልብ ውስጥ የተስፋን ብርሃን የፈነጠቀ ስለመሆኑ በስፋት እየተነገረ ነው፡፡አሜሪካውያን ተመራማሪዎች በላሰንት መጽሄት ላይ ያወጡትን መረጃ ጠቅሶ ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፣ “ሬምዴስቪር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የምርምር ውጤት በ15 ቀን ይታዩ የነበሩትን የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ወደ 11 ቀን ዝቅ እንደሚያደርግ የተነገረ ሲሆን፣ በሆስፒታሎች ያለውን ጫና በመቀነስ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይጠበቃል፡፡ከዚህ በፊት የኢቦላ ቫይረስ ተጠቂዎችን ለማከም በአገልግሎት ላይ ይውል እንደነበር የተነገረለት “ሬምዴስቪር”፣ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች የኮሮና ቫይረስ አይነቶች ህክምና በእንስሳት ላይ ተሞክሮ አመርቂ ውጤት ማሳየቱም ተዘግቧል፡፡“የሚፈቱ” አገራትና ከተሞች ተበራክተዋልከኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋት ጋር በተያያዘ የእንቅስቃሴ ገደብና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ጨምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን ወስደው የነበሩ በርካታ የአለማችን አገራትና ከተሞች ተግባራዊ ሲያደርጓቸው የቆዩዋቸውን እርምጃዎች ማቋረጣቸውንና ይህም የችኮላ እርምጃ ተብሎ በብዙዎች እየተተቸ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡የስራ አጡ ቁጥር በእጅጉ ይጨምራል ተብሎ መነገሩን ተከትሎ በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ተዘግተው የነበሩ የንግድ ተቋማት ወደ ስራ መመለሳቸውን የዘገበው ሮይተርስ፣ በስፔን ካለፈው እሁድ ጀምሮ አንዳንድ ጠንካራ ቁጥጥሮችን ያላላች ሲሆን፣ ለወራት በቤታቸው ውስጥ ታጉረው የነበሩ የአገሪቱ ህጻናት በወላጆች ድጋፍ ከቤት ወጥተው መንቀሳቀስ መጀመራቸውን አመልክቷል፡፡በቱኒዝያ ተዘግተው የነበሩ የምግብና የግንባታ ዘርፎች በከፊል መከፈት የጀመሩ ሲሆን፣ ግማሽ ያህሉ የአገሪቱ የመንግስት ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡በፖላንድ ተቋርጦ የቆየው መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴ በመጪው ሳምንት እንደሚጀመር እንዲሁም የተዘጉ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱ የተነገረ ሲሆን፣ ጣሊያን አንዳንድ ፋብሪካዎችን እንደምትከፍት፣ ናይጀሪያ ከነገ በስቲያ ጀምሮ የመንግስት መስሪያ ቤቶችንና ባንኮችን እንደምትከፍት አስታውቀዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ዜና
https://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=25319:%E1%8A%AE%E1%88%AE%E1%8A%93-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%88%9B%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%B3%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%89%B1&Itemid=212
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification
2370fd5efd7df9ab30358b68779cd48e
09af8a13d566e4be39e4b91a9b94d821
የኢትዮጵያና የኤርትራ ምሁራን በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ተወያዩ
የኢትዮጵያና የኤርትራን ሕዝብ የወደፊት ግንኙነት በተመለከተ ከሁለቱ አገሮች የተወከሉ ምሁራን በአዲስ አበባ ውይይት አካሂደዋል፡፡‹‹የሰላም መዝሙር ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ሕዝቦች›› በሚል መሪ ቃል ሐሙስ ኀዳር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በሐርመኒ ሆቴል በተካሄደው ውይይት ላይ፣ ኤርትራን በመወከል ከአውሮፓ የመጡና በአዲስ አበባ የሚኖሩ ምሁራን ተገኝተዋል፡፡ በውይይቱም የሁለቱን አገሮች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የገቱ ጉዳዮች ተነስተው ተመክሮባቸዋል፡፡የሁለቱን አገሮች ምሁራን ውይይት ፕሮፌሰር መድኃኔ ታደሰ የመሩ ሲሆን፣ ‹‹የሁለቱን ሕዝቦች ግንኙነት ሊያሻክሩ የሚችሉ ጉዳዮች አሹለው እየመጡ ስለሆነ፣ ምሁራን በጋራ ተግባብተው ለመጪው ትውልድ አንድ የሆነን ሕዝብ ማስረከብ አለባቸው፤›› ብለዋል፡፡በኢትዮጵያ በኩል ያዕቆብ ኃይለ ማርያም (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲ ምሁራንና የሚዲያ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር፡፡ የሁለቱን አገሮች ምሁራን የጋራ ውይይት ያዘጋጀው ‹‹ሰለብሪቲ ኢቨንትስ›› የተባለ ድርጅት ሲሆን፣ በቀጣይም የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች አንድነት የሚያጠናክሩ ሰፊ ሕዝባዊ ውይይቶች ለማዘጋጀት መታቀዱ ታውቋል፡፡
ፖለቲካ
https://www.ethiopianreporter.com/article/3235
https://huggingface.co/datasets/rasyosef/amharic-news-category-classification